Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 16 July 2011 11:34

የህገወጥ ፊልሞች ኪሳራ በዝቷል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በህገጥ መንገድ ከኢንተርኔት ተሰርቀው በዓለም ዙሪያ ለገበያ የሚሰራጩ የፊልም ስራዎችና የሙዚቃ አልበሞች በዓለም የመዝናኛ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ያስከተሉት ኪሣራ አስደንጋጭ ደረጃ ላይ መድረሱን ..ዩ ኤስ ኤ ቱዴይ.. አስታወቀ፡፡ ከተለያዩ የመረጃ ምንጮች ያገኘናቸው ሪፖርቶች እንዳመለከቱት፤ በዓለም ዙሪያ በሚከናወነው የህገወጥ ፊልሞች የገበያ ስርጭት ሆሊዉድ በዓመት 25 ቢሊዮን ዶላር እየከሰረ ነው፡፡

በቦሊውድ ፊልሞች ገበያ ላይም 1 ቢሊዮን ዶላር ኪሣራ ደርሶበታል፡፡ በህገወጥ ፊልሞች ሽያጭ ከፍተኛ ኪሣራ የደረሰበት ..አቫተር.. የተባለው የጀምስ ካሜሮን ፊልም 2.7 ሚሊዮን ህገወጥ ቅጂ እንደተሸጠ ተጠቁሟል፡፡
ቢዮንሴ እስክስታ ወረደች
አሜሪካዊቷ የአር ኤንድ ቢክና የፖፕ ሙዚቃ ንግስት ቢዮንሴ ኖውልስ፤ ..4.. በተሰኘው አዲስ አልበሟ ውስጥ ..ራን ዘ ዋርልድ (ገርልስ).. የሙዚቃ ቪዲዮ ላይ እስክስታ መውረዷን የተለያዩ ዘገባዎች አወሱ፡፡ ከአራት ዓመት በፊት ለአዲስ ዓመት ክብረ በዓል ወደ ኢትዮጵያ መጥታ የነበረችው ቢዮንሴ፤ በሚሊኒዬም አዳራሽ ባቀረበችው ዝግጅት በእስክስታ ትከሻዋን ለመነቅነቅ ሞክራ እንደነበር ይታወሳል፡፡
በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ በተለቀቀው ..ራን ዘ ዋርልድ.. የሙዚቃ ቪዲዮ ላይ ትዕይንቱ ሲጀምር በጥቁር ፈረስ በረሃ ላይ እየጋለበች የምትታየው ቢዮንሴ፤ በሙዚቃው ጭብጥ መሠረት የሴቶች ጦር በመምራት ከወንዶች ሠራዊት ጋር የምታደርገው ፍልሚያ ከመጀመሯ በፊት እስክስታ ወርዳለች፡፡ ከተለቀቀ ሁለት ሳምንት የሆነው የቢዮንሴ አዲስ አልበም በአሜሪካ ብቻ ሽያጩ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ መድረሱን ለማወቅ ተችሏል፡፡

 

Read 6631 times Last modified on Saturday, 16 July 2011 13:27