Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 24 November 2012 13:14

የግጥም ጥግ

Written by 
Rate this item
(6 votes)

መለየት
ብዙ ጊዜ አጠናሁ፤
ብዙ ጊዜ ወደቅሁ፤
ሌላ ብዙ ጊዜ፣ ሌላ ብዙ ጥናት፤
ዛሬም ነገም እዛው ተመሳሳይ ስህተት፡፡
ደግሞ ሌላ ጥናት በቃላት መራቀቅ፤
እንደገና መውደቅ፤
‘ሴት’ን እና ‘ሴክስ’ን ለይቶ አለማወቅ፡፡


የሊፍቱ ቅሬታ
ከህንጻ ተገጥሜ፣
ባገለገልኩበት፣ የእስካሁን ዘመኔ፣
እንደንቁ ሎሌ፣ እንደትጉ አገልጋይ፣
እያልኩ እታች እላይ፤
ያውም ተሸክሜ፣
ሰባት ስምንት ሰው በአንድ ጊዜ አዝዬ፤
በተሰመረልኝ በዛች ቀጭን መስመር ሽቅብ እወጣለሁ፣
ቁልቁል እወርዳለሁ፤
ታዲያ አሁን አሁን በዚህ እገረማለሁ፤
ምን ፍጥነት ቢኖረኝ፣
ምን ጉልበት ብሰንቅ፣
ከፍታዬ ታጥሩዋል በያዘኝ ህንጻ ልክ፤
እናም የሚገርመኝ፣
የኔ ከፍታና ፍጥነት፣ ጉልበት ሚወሰነው፣
ስንት ዘመን ሙሉ በማይነቃነቅ በቆመ ህንጻ ነው፡፡
አንድነት ግርማ

Read 7011 times

Latest from