Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 17 November 2012 12:24

ተንቀሳቃሽ የኢትዮጵያ ቅርሶች ነን

Written by 
Rate this item
(3 votes)

እስቲ ከልጅነትህ እንጀምር…
የተወለድኩት እዚሁ አዲስ አበባ ሽሮ ሜዳ አካባቢ ነው፡፡ በፀሐይ ጮራ አንደኛ ደረጃ ት/ቤትና በምኒሊክ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ነው የተማርኩት፡፡ የባህል ውዝዋዜና ዳንስ የጀመርኩት ምኒሊክ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የ7ኛ ክፍል ተማሪ እያለሁ ሲሆን በቀበሌ ኪነት ውስጥም ነበርኩኝ፡፡ ዛሬ እንግዲህ 27 ዓመቴ ነው፡፡ ሽሮ ሜዳ (ቀበሌ 08) የባህል ቡድን ነበረ፡፡ እኔ ደግሞ በጣም ሙዚቃ እወድ ነበር፡፡ አንድ የሠፈር ጓደኛዬ ካልሄድን ብሎ ገፋፋኝና ሄድን፡፡ የእኔ ፍላጐት እንኳን ዳንስ ነበር፡፡ ልጆቹ ግን የወሎ፣ የጐንደር፣ የጐጃምና የሐረር ኦሮሞ የባህል ውዝዋዜ ነው የሚሰሩት፡፡ እኔ ደግሞ እነዚያን ውዝዋዜዎች አላውቃቸውም፡፡ እኔ መደነስ መጨፈር ነበር የምወደው፡፡ ሆኖም የባህል እንቅስቃሴውም አላስቸገረኝም፤ እንደውም ቶሎ ተዋሃደኝ፡፡ አርቲስት ሰለሞን መንግሥቴ የተባለ ህፃናትና ወጣቶች ቲያትር ቤት የሚሰራ ልጅ አውቅ ነበር፡፡ በሱ አማካኝነት ቲያትር ቤት የመሄድ አጋጣሚ ተፈጠረ፡፡ ህፃናትና ወጣቶች ቲያትር ቤት እንድገባ የረዳኝ በኢቲቪ ይተላለፍ ለነበረ የህፃናት ፕሮግራም መታጨቴ ነው፡፡ “ትንሹ ሙዚቀኛ” በሚል ርዕስ ድራማ ሰርተናል፡፡

ለድራማው ስንለማመድ የተመለከቱን የህፃናትና ወጣቶች ትያትር ቤት ባለሙያዎች ለምን ቲያትር ቤት አትመጡም አሉን፡፡ 
አምስት ሆነን ቦታውን እያጠያየቅን ወደ ትያትር ቤቱ ሄድን፡፡ ከዛም ሙሉ ገበየሁን አገኘነው፡፡ “እስኪ ሞክሩ” አለን፡፡ በደንብ ሰራንለት፡፡ ከአምስታችን ውስጥ ውስጥ ሶስታችን ቀጠልን፡፡ ከሶስታችን አብርሃም የተባለው ዛሬ ትልቅ ባለሞያ ሆኗል፡፡ በ1990 ዓ.ም ነበር ህፃናትና ወጣቶች ትያትር ቤት የገባነው፡፡ ከት/ቤት ሰዓታችን ውጭ የባህል ውዝዋዜን ለመማር እንጥር ነበር፡፡ በ1995 ዓ.ም ከህፃናትና ወጣቶች ትያትር ወጥተን ወደ ሌሎች ትያትር ቤቶች የመሄድ ሃሳብ መጣ፡፡
በህፃናትና ወጣቶች ቲያትር ቤት ስትሰሩ ስንት ይከፈላችሁ ነበር?
በየወሩ ሃያ ሃያ ብር ይሰጠን ነበር፡፡ ደሞዝ ሳይሆን እንደማበረታቻ ነው፡፡ የትራንስፖርት ተብሎ ነበር የሚሰጠን፡፡ እዚያ ሳለን የበርካታ ብሔር ብሔረሰቦችን ውዝዋዜ ሰርተናል፡፡ ብዙ ህፃናት እኛን ለማየት ይመጡ ነበር፡፡ እኔን በጓሮ መጥተው ይጨብጡኛል፣ ከረሜላ ይሰጡኝ ነበር - “ጐበዝ!” እያሉ፡፡ የሚገርመው ግን በዛ እድሜያችንም ሆነን የሃገራችንን ባህላዊ ውዝዋዜ እንዴት እናሳድግ በሚል ሌት ተቀን ከልብ በመነጨ ስሜት እንሰራ ነበር፡፡
ከህፃናትና ወጣቶች ትያትር ቤት በኋላስ?
ጐርመስ ያልን ሲመስለን ወደ ሃገር ፍቅር አቀናንን፡፡
መጀመሪያ ያገኘነው አብዮትን ነው፡፡ የቤቱ ምርጥ የባህል ተወዛዋዥ ነበር፡፡ ምናልባት አሁን ሲያነበው ይስቅ ይሆናል፡፡ በወቅቱ የባህል ውዝዋዜና አሰልጣኝ ኪዳኔ ምስጋናው ነበር፡፡ ከሶስት ጓደኞቼ ጋር ነበር የሄድነው፡፡
ትንንሽ ስለነበርን አያስገቡንም በሚል መጨነቃችን አልቀረም፡፡ እንደፈራነው አልቀረም፡፡ ኪዳኔ “በጣም ትንሽ ናችሁ እኮ” ሲለን አውቄ ተንጠራራሁ - ረዥም ለመምሰል፡፡ ጓደኞቼም እኔን ተከትለው ተንጠራሩ፡፡ ሁኔታችንን አይቶ ገባውና በጣም ሳቀ፡፡ ከዛም እንድንገባ ፈቀደልን፡፡
በገባን በሳምንት ጊዜ ውስጥ እኔ በሳምንት አምስት መድረክ ነበረኝ፡፡ ሀገር ፍቅር አምስት ዓመት ስሰራ ከአቶ ሙሉ ገበየሁ ጋር ንግግር አልነበረንም፡፡ ጠዋት ጠዋት ወደ ቢሮ ሲገባ ግን ልምምድ ወደማደርግበት ክፍል ገብቶ ሰላም ሳይለኝ አይቶኝ ይወጣ ነበር፡፡ በጣም ነበር የሚገርመኝ፡፡ በቅርቡ ግን መለሰልኝ፡፡ “ጥሩ ሞያተኛ እንዲሆን ስለምፈልግና የሚከታተለኝ ሰው አለ ብሎ እንዲያስብ ነው” ብሏል (ሳቅ)
ሀገር ፍቅር በስንት ብር ደሞዝ ተቀጠርክ?
347 ብር ነበር እኔ ስቀጠር፡፡ በቲያትር ቤቱ የነበሩ ሞያተኞች በስራዬ በጣም ደስተኞች ነበሩ፡፡ በዕድሜና በሰውነት ከሁሉም ትንሽ እኔ ስለነበርኩ የሚሰጠኝ ልብስ እየሰፋኝ እቸገር ነበር፡፡ ስለዚህ በቀበቶ ታስሮ እንዲጠብ ይደረጋል፡፡ ከሁለት ዓመት በኋላ ቋሚ ሠራተኛ መሆኔን የሚገልጽ ደብዳቤ ደረሰኝ፡፡ የሚገርመው ግን ሁለት ዓመት ስሰራ ጊዜያዊ ሠራተኛ መሆኔን አላውቅም ነበር፡፡
ስራውን ከልቤ ስለምወደው ይሄን ይሄን አላስበውም፡
ያኔ ህልምህ ምን ነበር?
የራሴን የባህል ቡድን ማቋቋም እፈልግ ነበር፡፡ በሞያው ማደግ፣ ህፃናትን ሰብስቤ የራሴ ነገር መመስረት ነበር ህልሜ፡፡
ህልምህን እንዴት አሳካኸው?
የሙዚቃና የውዝዋዜ ፍላጐት ያላቸው ብዙ ህፃናት ወደ ቲያትር ቤት ይሄዱና የሚፈለጉት ጥቂት ህፃናት ስለሆኑ ይመለሱ ነበር፡፡ እናም ክረምት ላይ ሄጄ 37 ልጆች መረጥኩ፡፡ በ1999 ዓ.ም “የተመስገን ልጆች” በሚል ስያሜ ለሶስት ወር ካሰለጠንኳቸው በኋላ ሲመረቁ ለ1 ሰዓት ከ5 ደቂቃ አንዴም ሳያርፉ የውዝዋዜ ትርዒት አሳዩ፡፡
ለምታሰለጥናቸው ልጆች የዕድሜ ገደብ ነበረው?
ትንሹ ዕድሜ 9 ዓመት፤ ትልቁ 16 ዓመት ነበር፡፡
እኛ ያሰለጠናቸው ልጆች ዛሬ በተለያዩ መድረኮች ይታያሉ፡፡ አላማዬ እነዚህን ልጆች አሰልጥኖ መበተን ሳይሆን በትልልቅ መድረኮች ባህላችንን እንዲያስተዋውቁ ማድረግ ነው፡፡ ባለፈው ለደቡብ አፍሪካ የዓለም ዋንጫ ለመጓዝ ታጭተን ነበር፤ ግን ሳንሄድ ቀረን፡፡ ቢሳካ ኖሮ የኢትዮጵያን ብሔር ብሔረሰቦች ውዝዋዜና ድንቅ ባህል በሚያስገርም ትዕይንት ልንሠራው ተዘጋጅተን ነበር፡፡
“የተመስገን ልጆች” ዓላማ ምንድነው?
የኢትዮጵያን ባህላዊ ውዝዋዜ በአለማቀፍ ደረጃ ማስተዋወቅና ተወዳጅ ማድረግ ነው፡፡ ዛሬም ትናንትም የተነሳንበት አላማ የኢትዮጵያን ባህል በአለማቀፍ ደረጃ ማስተዋወቅ ነው፡፡ ተሰጥኦና ፍላጐቱ ላላቸው ህፃናት መድረክ እየሰጠን ነው፡፡ በነገራችን ላይ ዛሬ የተመስገን ልጆች በቁጥር በርክተን መቶ ሰማኒያ ደርሰናል፡፡
ህፃናት “የተመስገን ልጆች”ን ሲቀላቀሉ በምን መስፈርት ነበር?
የመጀመሪያዎቹን ሳሰለጥን ምንም አይነት መስፈርት አልነበረም፡፡ ያላቸውን ተሰጥኦ በማየት ነው 37 ልጆች የመረጥኩት፡፡ በእኛ ቡድን ውስጥ መቀጠል ለሚፈልጉ ግን መስፈርቶች አበጀን፡፡ የማይማር ልጅ እኛ ቡድን ውስጥ አይካተትም፡፡ በየጊዜው የትምህርት ውጤታቸውን እንዲያመጡ ይጠየቁ ነበር፡፡ የተማሩ አርቲስቶች እንዲሆኑ ነበር የምንፈልገው፡፡
አሁን በትምህርታቸው ምን ደረሱ?
አንደኛዋ ልጄ ጅጅጋ ዩኒቨርስቲ የ2ኛ ዓመት ተማሪ ናት፡፡ ዘንድሮ ደግሞ ወልቂጤ ዩኒቨርስቲ የደረሳት አለች፡፡
ሌላዋ በአካውንቲንግ በዲፕሎማ ተመርቃ አሁን ደግሞ ለዲግሪ መርሃ ግብር ተመዝግባለች፡፡ አንደኛው ልጄ በኤሌክትሮኒክስ ተመርቋል፡፡ ተፈሪ መኮንን የሙዚቃ ተማሪ የሆነ ልጅም አለኝ፡፡ ሁሉም ትምህርታቸውን እየተማሩ ነው ያሉት፡፡
ፕሪፓራቶሪ የሚማሩም አሉ፡፡ ከስራው ጋር እንዳይጋጭባቸው በትምህርት ሰዓት ልምምድ አያደርጉም፡፡ እኛም አናበረታታም፡፡ ውጤታቸው አንሶ ከተገኘም ከቡድኑ ይታገዳሉ፡፡
እርስ በርስ ግንኙነታችሁ ምን ይመስላል?
ደስ የሚል ፍቅር አለን፡፡ እንከባበራለን፡፡ ብዙ ችግር ቢኖርብንም እስከ አሁን አብረን ጠልቀናል፡፡
ትልቅ ራዕይ ይዘን ስለተነሳን ከእግዚአብሔር ጋር እየሠራን ነው፡፡ ብዙ ሰዎች በኢትዮጵያ እንዲማረኩ እንተጋለን፡፡ እኛ የኢትዮጵያ ተንቀሳቃሽ ቅርስ ነን ብለን እናስባለን፡፡
እስካሁን ምን ሰራችሁ?
በርካታ ስራዎችን ሰርተናል፡፡ የጉራጌ ቴሌቶን ላይ በሚሌኒየም አዳራሽ ስራችንን አቅርበናል፡፡ በሸራተን አዲስ፣ በሂልተን፣ በአሊያንስ ኢትዮ ፍራንሲስም ሰርተናል፡
የእናቶች ቀን ሲከበር በኢምፔሪያል ሆቴል፣ በገተ ኢንስቲቱዩት፣ በጣሊያን የባህል ማዕከልና በብሔራዊ ቲያትር እንዲሁ በርካታ ስራዎችን አቅርበናል፡፡
ባላገሩ እና ጉራጊኛ ዘፈን ላይ ከአብርሃም ወልዴ ጋር ሰርተናል፡፡ የነፃነት መለሰ “ባይ ባይ” የሙዚቃ ክሊፕ ላይ ተጫውተናል፡፡ በነገራችን ላይ ክሊፑ የተዋጣለት ስራ ነበር፡፡
ሥራችሁን ስትሰሩ ፈተናና እንቅፋት የሆነባችሁ ምንድነው?
የተመስገን ልጆች የራሱ የሆነ የስልጠና ቦታ እንኳን የለውም፡፡ ሰው ግቢ ውስጥ ያጠናንበት ጊዜ አለ፡፡
በገንዘብ እስከ አሁን ድረስ ያን ያህል ተጠቃሚዎች አይደለንም፡፡
እኔም ብሆን እንደዛው ነው፡፡ ስራ ተሰርቶ የሚገኘው ገንዘብ የራሱ ወጪዎች አሉት፡፡ የባህል ልብሶችና ጫማ ማሰራት በጣም ውድ ስለሆነ የምናገኘውን ገንዘብ በሙሉ ለዚያ ነው የምናውለው፡፡
ወደፊት ምን አሰብክ…?
የባህል ጥናት ለመጀመር ዝግጅት ላይ ነኝ ያለሁት፡፡
የጥናት ፈቃድ ደብዳቤ አለኝ፡፡ የብሔር ብሔረሰቦች እንቅስቃሴና አጠቃላይ የውዝዋዜ ገጽታ ምንጫቸው ምንድን ነው? ለምሳሌ በደስታ ጊዜ ነው በሀዘን ጊዜ፤ ልጆች ናቸው ወይንስ አረጋውያን? በባህል ውዝዋዜ ወቅት የሚለበሱ አልባሳት ትርጉማቸው ምንድነው? ብዙ ያልተመለሱ ጥያቄዎች አሉ፡፡ እነዚህን ነገሮች ለማጥናት እፈልጋለሁ፡፡ ለምሳሌ በትግርኛ ባህላዊ ጭፈራ ላይ ለምንድነው እየዞሩ የሚጨፍሩት? ለምንድን ነው ወላይተኛ ላይ ወገባቸውን የሚንጡት? ዶርዝኛ ጦራቸውን ይዘው ወደ ላይ የሚዘሉትስ? የእነዚህን ጥያቄዎች መልሶች በጥናት በማግኘት ለቀጣዩ ትውልድ ለማስቀመጥ እፈልጋለሁ፡፡ የእኛን ባህሎች እኛ ተቀምጠን ሌሎች መጥተው ለምንድን ነው የሚያጠኑልን፡፡
ከዚህም በተረፈ “የተመስገን ልጆች” ሶስት ፎቅ ያለው ሁለገብ ህንፃ ለማስገንባት ዲዛይኑን አሠርተን ጨርሰናል፡፡ ህፃናትና ወጣቶች የሚዝናኑበት፣ መጽሐፍ የሚያነቡበት፣ ስፖርት የሚሠሩበት፣ ፊልም የሚያዩበት ይሆናል፡፡
ስለዳንሶቻችንንና ባህሎቻችን በደንብ የሚማሩበትና የሚያውቁበት የዳንስ ዲፓርትመንት አለው፡፡ ኢትዮጵያ የባህል ውዝዋዜ ማዕከል የላትም፡፡ ያንን ማዕከል ለማስገንባትም ቦታ እንዲፈቀድልን እንፈልጋለን፡፡ ህዝቡ ሃሳባችንን ተረድቶን ለልጆቻችንና ለልጅ ልጆቻችን ትልቅ ጥቅም አለው ብሎ ሊደግፈን ይገባል፡፡
በቅርቡ ለመስራት ያሰባችሁት አዲስ ነገር አለ?
ብዙ ክሊፖች ላይ ስሜ ይታያል፡፡ ኬሮግራፊና ዳይሬክቲንግ እየሰራሁ ነው፡፡ ግጥምና ዜማ እንዲሁም የራሴንም ዘፈን እሰራለሁ፡፡ አሁን የባህል ዳንስ ላይ ያተኮረ ፊልም እየሠራን ነው፡፡ “ዳንስ ቴራፒ” የሚል ነው፡፡
ፊልሙ የባህል ዳንስ እንዴት የልጆቼንና የእኔን ህይወት እንደቀየረ የሚያሳይ ነው፡፡ ፊልማችን ከአንድ ዓመት በኋላ በጥሩ ሁኔታ ተሰርቶ ለዕይታ ይቀርባል፡፡
የትምህርት ደረጃህ?
በእኛ ጊዜ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት እስከ 10ኛ ክፍል ስለነበር ያንን አጠናቅቄአለሁ፡፡
ራሴን በሙዚቃ ሙያ ለመቃኘትና በትምህርት ለማዳበር ጀርመን ሀቡርግ የዳንስ ት/ቤት ለ6 ወር ለመማር በዝግጅት ላይ እያለሁ ለደቡብ አፍሪካ የዓለም ዋንጫ 30 ልጆችን ይዤ ለመጓዝ ታጨሁ፡፡
ሆኖም የደቡብ አፍሪካ ጉዞ ሳይሳካ ቀረ፡፡ የጀርመን ጉዞዬም በዛው ቀረ፡፡ አሁን ግን ተመልሼ ለመሄድ እየተዘጋጀሁ ነው፡፡
በአሁኑ ጊዜ ገቢህ ምንድን ነው?
በቶቶት የባህል አዳራሽ ሙሉ የባህል ባንዱ የእኔ ነው፡፡ ክሊፖች ዳይሬክት አደርጋለሁ፡፡ ኬሮግራፊ እሰራለሁ፡፡
አንዳንድ ዝግጅቶች ላይ ልጆቼን ይዤ እሰራለሁ፡፡ በዝግጅቱ ላይ መደነስ ካለብኝ እደንሳለሁ፡፡
ካሰለጠንካቸው ልጆች ትልቅ ቦታ የደረሱ አሉ?
አዎ፡፡ በቲያትር ቤቶች የተቀጠሩና ውጪ አገር ድረስ እየሄዱ የባህል ውዝዋዜ የሚሠሩ ወደ አምስት ልጆች አሉኝ፡፡
እስቲ ከልጅነትህ እንጀምር…
የተወለድኩት እዚሁ አዲስ አበባ ሽሮ ሜዳ አካባቢ ነው፡፡ በፀሐይ ጮራ አንደኛ ደረጃ ት/ቤትና በምኒሊክ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ነው የተማርኩት፡፡ የባህል ውዝዋዜና ዳንስ የጀመርኩት ምኒሊክ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የ7ኛ ክፍል ተማሪ እያለሁ ሲሆን በቀበሌ ኪነት ውስጥም ነበርኩኝ፡፡ ዛሬ እንግዲህ 27 ዓመቴ ነው፡፡ ሽሮ ሜዳ (ቀበሌ 08) የባህል ቡድን ነበረ፡፡ እኔ ደግሞ በጣም ሙዚቃ እወድ ነበር፡፡ አንድ የሠፈር ጓደኛዬ ካልሄድን ብሎ ገፋፋኝና ሄድን፡፡ የእኔ ፍላጐት እንኳን ዳንስ ነበር፡፡
ልጆቹ ግን የወሎ፣ የጐንደር፣ የጐጃምና የሐረር ኦሮሞ የባህል ውዝዋዜ ነው የሚሰሩት፡፡ እኔ ደግሞ እነዚያን ውዝዋዜዎች አላውቃቸውም፡፡ እኔ መደነስ መጨፈር ነበር የምወደው፡፡ ሆኖም የባህል እንቅስቃሴውም አላስቸገረኝም፤ እንደውም ቶሎ ተዋሃደኝ፡፡ አርቲስት ሰለሞን መንግሥቴ የተባለ ህፃናትና ወጣቶች ቲያትር ቤት የሚሰራ ልጅ አውቅ ነበር፡፡ በሱ አማካኝነት ቲያትር ቤት የመሄድ አጋጣሚ ተፈጠረ፡፡ ህፃናትና ወጣቶች ቲያትር ቤት እንድገባ የረዳኝ በኢቲቪ ይተላለፍ ለነበረ የህፃናት ፕሮግራም መታጨቴ ነው፡፡ “ትንሹ ሙዚቀኛ” በሚል ርዕስ ድራማ ሰርተናል፡፡
ለድራማው ስንለማመድ የተመለከቱን የህፃናትና ወጣቶች ትያትር ቤት ባለሙያዎች ለምን ቲያትር ቤት አትመጡም አሉን፡፡
አምስት ሆነን ቦታውን እያጠያየቅን ወደ ትያትር ቤቱ ሄድን፡፡ ከዛም ሙሉ ገበየሁን አገኘነው፡፡ “እስኪ ሞክሩ” አለን፡፡ በደንብ ሰራንለት፡፡ ከአምስታችን ውስጥ ውስጥ ሶስታችን ቀጠልን፡፡ ከሶስታችን አብርሃም የተባለው ዛሬ ትልቅ ባለሞያ ሆኗል፡፡ በ1990 ዓ.ም ነበር ህፃናትና ወጣቶች ትያትር ቤት የገባነው፡፡ ከት/ቤት ሰዓታችን ውጭ የባህል ውዝዋዜን ለመማር እንጥር ነበር፡፡ በ1995 ዓ.ም ከህፃናትና ወጣቶች ትያትር ወጥተን ወደ ሌሎች ትያትር ቤቶች የመሄድ ሃሳብ መጣ፡፡
በህፃናትና ወጣቶች ቲያትር ቤት ስትሰሩ ስንት ይከፈላችሁ ነበር?
በየወሩ ሃያ ሃያ ብር ይሰጠን ነበር፡፡ ደሞዝ ሳይሆን እንደማበረታቻ ነው፡፡ የትራንስፖርት ተብሎ ነበር የሚሰጠን፡፡ እዚያ ሳለን የበርካታ ብሔር ብሔረሰቦችን ውዝዋዜ ሰርተናል፡፡ ብዙ ህፃናት እኛን ለማየት ይመጡ ነበር፡፡ እኔን በጓሮ መጥተው ይጨብጡኛል፣ ከረሜላ ይሰጡኝ ነበር - “ጐበዝ!” እያሉ፡፡ የሚገርመው ግን በዛ እድሜያችንም ሆነን የሃገራችንን ባህላዊ ውዝዋዜ እንዴት እናሳድግ በሚል ሌት ተቀን ከልብ በመነጨ ስሜት እንሰራ ነበር፡፡
ከህፃናትና ወጣቶች ትያትር ቤት በኋላስ?
ጐርመስ ያልን ሲመስለን ወደ ሃገር ፍቅር አቀናንን፡፡
መጀመሪያ ያገኘነው አብዮትን ነው፡፡ የቤቱ ምርጥ የባህል ተወዛዋዥ ነበር፡፡ ምናልባት አሁን ሲያነበው ይስቅ ይሆናል፡፡ በወቅቱ የባህል ውዝዋዜና አሰልጣኝ ኪዳኔ ምስጋናው ነበር፡፡ ከሶስት ጓደኞቼ ጋር ነበር የሄድነው፡፡
ትንንሽ ስለነበርን አያስገቡንም በሚል መጨነቃችን አልቀረም፡፡ እንደፈራነው አልቀረም፡፡ ኪዳኔ “በጣም ትንሽ ናችሁ እኮ” ሲለን አውቄ ተንጠራራሁ - ረዥም ለመምሰል፡፡ ጓደኞቼም እኔን ተከትለው ተንጠራሩ፡፡ ሁኔታችንን አይቶ ገባውና በጣም ሳቀ፡፡ ከዛም እንድንገባ ፈቀደልን፡፡
በገባን በሳምንት ጊዜ ውስጥ እኔ በሳምንት አምስት መድረክ ነበረኝ፡፡ ሀገር ፍቅር አምስት ዓመት ስሰራ ከአቶ ሙሉ ገበየሁ ጋር ንግግር አልነበረንም፡፡ ጠዋት ጠዋት ወደ ቢሮ ሲገባ ግን ልምምድ ወደማደርግበት ክፍል ገብቶ ሰላም ሳይለኝ አይቶኝ ይወጣ ነበር፡፡ በጣም ነበር የሚገርመኝ፡፡ በቅርቡ ግን መለሰልኝ፡፡ “ጥሩ ሞያተኛ እንዲሆን ስለምፈልግና የሚከታተለኝ ሰው አለ ብሎ እንዲያስብ ነው” ብሏል (ሳቅ)
ሀገር ፍቅር በስንት ብር ደሞዝ ተቀጠርክ?
347 ብር ነበር እኔ ስቀጠር፡፡ በቲያትር ቤቱ የነበሩ ሞያተኞች በስራዬ በጣም ደስተኞች ነበሩ፡፡ በዕድሜና በሰውነት ከሁሉም ትንሽ እኔ ስለነበርኩ የሚሰጠኝ ልብስ እየሰፋኝ እቸገር ነበር፡፡ ስለዚህ በቀበቶ ታስሮ እንዲጠብ ይደረጋል፡፡ ከሁለት ዓመት በኋላ ቋሚ ሠራተኛ መሆኔን የሚገልጽ ደብዳቤ ደረሰኝ፡፡ የሚገርመው ግን ሁለት ዓመት ስሰራ ጊዜያዊ ሠራተኛ መሆኔን አላውቅም ነበር፡፡
ስራውን ከልቤ ስለምወደው ይሄን ይሄን አላስበውም፡
ያኔ ህልምህ ምን ነበር?
የራሴን የባህል ቡድን ማቋቋም እፈልግ ነበር፡፡ በሞያው ማደግ፣ ህፃናትን ሰብስቤ የራሴ ነገር መመስረት ነበር ህልሜ፡፡
ህልምህን እንዴት አሳካኸው?
የሙዚቃና የውዝዋዜ ፍላጐት ያላቸው ብዙ ህፃናት ወደ ቲያትር ቤት ይሄዱና የሚፈለጉት ጥቂት ህፃናት ስለሆኑ ይመለሱ ነበር፡፡ እናም ክረምት ላይ ሄጄ 37 ልጆች መረጥኩ፡፡ በ1999 ዓ.ም “የተመስገን ልጆች” በሚል ስያሜ ለሶስት ወር ካሰለጠንኳቸው በኋላ ሲመረቁ ለ1 ሰዓት ከ5 ደቂቃ አንዴም ሳያርፉ የውዝዋዜ ትርዒት አሳዩ፡፡
ለምታሰለጥናቸው ልጆች የዕድሜ ገደብ ነበረው?
ትንሹ ዕድሜ 9 ዓመት፤ ትልቁ 16 ዓመት ነበር፡፡
እኛ ያሰለጠናቸው ልጆች ዛሬ በተለያዩ መድረኮች ይታያሉ፡፡ አላማዬ እነዚህን ልጆች አሰልጥኖ መበተን ሳይሆን በትልልቅ መድረኮች ባህላችንን እንዲያስተዋውቁ ማድረግ ነው፡፡ ባለፈው ለደቡብ አፍሪካ የዓለም ዋንጫ ለመጓዝ ታጭተን ነበር፤ ግን ሳንሄድ ቀረን፡፡ ቢሳካ ኖሮ የኢትዮጵያን ብሔር ብሔረሰቦች ውዝዋዜና ድንቅ ባህል በሚያስገርም ትዕይንት ልንሠራው ተዘጋጅተን ነበር፡፡
“የተመስገን ልጆች” ዓላማ ምንድነው?
የኢትዮጵያን ባህላዊ ውዝዋዜ በአለማቀፍ ደረጃ ማስተዋወቅና ተወዳጅ ማድረግ ነው፡፡ ዛሬም ትናንትም የተነሳንበት አላማ የኢትዮጵያን ባህል በአለማቀፍ ደረጃ ማስተዋወቅ ነው፡፡ ተሰጥኦና ፍላጐቱ ላላቸው ህፃናት መድረክ እየሰጠን ነው፡፡ በነገራችን ላይ ዛሬ የተመስገን ልጆች በቁጥር በርክተን መቶ ሰማኒያ ደርሰናል፡፡
ህፃናት “የተመስገን ልጆች”ን ሲቀላቀሉ በምን መስፈርት ነበር?
የመጀመሪያዎቹን ሳሰለጥን ምንም አይነት መስፈርት አልነበረም፡፡ ያላቸውን ተሰጥኦ በማየት ነው 37 ልጆች የመረጥኩት፡፡ በእኛ ቡድን ውስጥ መቀጠል ለሚፈልጉ ግን መስፈርቶች አበጀን፡፡ የማይማር ልጅ እኛ ቡድን ውስጥ አይካተትም፡፡ በየጊዜው የትምህርት ውጤታቸውን እንዲያመጡ ይጠየቁ ነበር፡፡ የተማሩ አርቲስቶች እንዲሆኑ ነበር የምንፈልገው፡፡
አሁን በትምህርታቸው ምን ደረሱ?
አንደኛዋ ልጄ ጅጅጋ ዩኒቨርስቲ የ2ኛ ዓመት ተማሪ ናት፡፡ ዘንድሮ ደግሞ ወልቂጤ ዩኒቨርስቲ የደረሳት አለች፡፡
ሌላዋ በአካውንቲንግ በዲፕሎማ ተመርቃ አሁን ደግሞ ለዲግሪ መርሃ ግብር ተመዝግባለች፡፡ አንደኛው ልጄ በኤሌክትሮኒክስ ተመርቋል፡፡ ተፈሪ መኮንን የሙዚቃ ተማሪ የሆነ ልጅም አለኝ፡፡ ሁሉም ትምህርታቸውን እየተማሩ ነው ያሉት፡፡
ፕሪፓራቶሪ የሚማሩም አሉ፡፡ ከስራው ጋር እንዳይጋጭባቸው በትምህርት ሰዓት ልምምድ አያደርጉም፡፡ እኛም አናበረታታም፡፡ ውጤታቸው አንሶ ከተገኘም ከቡድኑ ይታገዳሉ፡፡
እርስ በርስ ግንኙነታችሁ ምን ይመስላል?
ደስ የሚል ፍቅር አለን፡፡ እንከባበራለን፡፡ ብዙ ችግር ቢኖርብንም እስከ አሁን አብረን ጠልቀናል፡፡
ትልቅ ራዕይ ይዘን ስለተነሳን ከእግዚአብሔር ጋር እየሠራን ነው፡፡ ብዙ ሰዎች በኢትዮጵያ እንዲማረኩ እንተጋለን፡፡ እኛ የኢትዮጵያ ተንቀሳቃሽ ቅርስ ነን ብለን እናስባለን፡፡
እስካሁን ምን ሰራችሁ?
በርካታ ስራዎችን ሰርተናል፡፡ የጉራጌ ቴሌቶን ላይ በሚሌኒየም አዳራሽ ስራችንን አቅርበናል፡፡ በሸራተን አዲስ፣ በሂልተን፣ በአሊያንስ ኢትዮ ፍራንሲስም ሰርተናል፡
የእናቶች ቀን ሲከበር በኢምፔሪያል ሆቴል፣ በገተ ኢንስቲቱዩት፣ በጣሊያን የባህል ማዕከልና በብሔራዊ ቲያትር እንዲሁ በርካታ ስራዎችን አቅርበናል፡፡
ባላገሩ እና ጉራጊኛ ዘፈን ላይ ከአብርሃም ወልዴ ጋር ሰርተናል፡፡ የነፃነት መለሰ “ባይ ባይ” የሙዚቃ ክሊፕ ላይ ተጫውተናል፡፡ በነገራችን ላይ ክሊፑ የተዋጣለት ስራ ነበር፡፡
ሥራችሁን ስትሰሩ ፈተናና እንቅፋት የሆነባችሁ ምንድነው?
የተመስገን ልጆች የራሱ የሆነ የስልጠና ቦታ እንኳን የለውም፡፡ ሰው ግቢ ውስጥ ያጠናንበት ጊዜ አለ፡፡
በገንዘብ እስከ አሁን ድረስ ያን ያህል ተጠቃሚዎች አይደለንም፡፡
እኔም ብሆን እንደዛው ነው፡፡ ስራ ተሰርቶ የሚገኘው ገንዘብ የራሱ ወጪዎች አሉት፡፡ የባህል ልብሶችና ጫማ ማሰራት በጣም ውድ ስለሆነ የምናገኘውን ገንዘብ በሙሉ ለዚያ ነው የምናውለው፡፡
ወደፊት ምን አሰብክ…?
የባህል ጥናት ለመጀመር ዝግጅት ላይ ነኝ ያለሁት፡፡
የጥናት ፈቃድ ደብዳቤ አለኝ፡፡ የብሔር ብሔረሰቦች እንቅስቃሴና አጠቃላይ የውዝዋዜ ገጽታ ምንጫቸው ምንድን ነው? ለምሳሌ በደስታ ጊዜ ነው በሀዘን ጊዜ፤ ልጆች ናቸው ወይንስ አረጋውያን? በባህል ውዝዋዜ ወቅት የሚለበሱ አልባሳት ትርጉማቸው ምንድነው? ብዙ ያልተመለሱ ጥያቄዎች አሉ፡፡ እነዚህን ነገሮች ለማጥናት እፈልጋለሁ፡፡ ለምሳሌ በትግርኛ ባህላዊ ጭፈራ ላይ ለምንድነው እየዞሩ የሚጨፍሩት? ለምንድን ነው ወላይተኛ ላይ ወገባቸውን የሚንጡት? ዶርዝኛ ጦራቸውን ይዘው ወደ ላይ የሚዘሉትስ? የእነዚህን ጥያቄዎች መልሶች በጥናት በማግኘት ለቀጣዩ ትውልድ ለማስቀመጥ እፈልጋለሁ፡፡ የእኛን ባህሎች እኛ ተቀምጠን ሌሎች መጥተው ለምንድን ነው የሚያጠኑልን፡፡
ከዚህም በተረፈ “የተመስገን ልጆች” ሶስት ፎቅ ያለው ሁለገብ ህንፃ ለማስገንባት ዲዛይኑን አሠርተን ጨርሰናል፡፡ ህፃናትና ወጣቶች የሚዝናኑበት፣ መጽሐፍ የሚያነቡበት፣ ስፖርት የሚሠሩበት፣ ፊልም የሚያዩበት ይሆናል፡፡
ስለዳንሶቻችንንና ባህሎቻችን በደንብ የሚማሩበትና የሚያውቁበት የዳንስ ዲፓርትመንት አለው፡፡ ኢትዮጵያ የባህል ውዝዋዜ ማዕከል የላትም፡፡ ያንን ማዕከል ለማስገንባትም ቦታ እንዲፈቀድልን እንፈልጋለን፡፡ ህዝቡ ሃሳባችንን ተረድቶን ለልጆቻችንና ለልጅ ልጆቻችን ትልቅ ጥቅም አለው ብሎ ሊደግፈን ይገባል፡፡
በቅርቡ ለመስራት ያሰባችሁት አዲስ ነገር አለ?
ብዙ ክሊፖች ላይ ስሜ ይታያል፡፡ ኬሮግራፊና ዳይሬክቲንግ እየሰራሁ ነው፡፡ ግጥምና ዜማ እንዲሁም የራሴንም ዘፈን እሰራለሁ፡፡ አሁን የባህል ዳንስ ላይ ያተኮረ ፊልም እየሠራን ነው፡፡ “ዳንስ ቴራፒ” የሚል ነው፡፡
ፊልሙ የባህል ዳንስ እንዴት የልጆቼንና የእኔን ህይወት እንደቀየረ የሚያሳይ ነው፡፡ ፊልማችን ከአንድ ዓመት በኋላ በጥሩ ሁኔታ ተሰርቶ ለዕይታ ይቀርባል፡፡
የትምህርት ደረጃህ?
በእኛ ጊዜ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት እስከ 10ኛ ክፍል ስለነበር ያንን አጠናቅቄአለሁ፡፡
ራሴን በሙዚቃ ሙያ ለመቃኘትና በትምህርት ለማዳበር ጀርመን ሀቡርግ የዳንስ ት/ቤት ለ6 ወር ለመማር በዝግጅት ላይ እያለሁ ለደቡብ አፍሪካ የዓለም ዋንጫ 30 ልጆችን ይዤ ለመጓዝ ታጨሁ፡፡
ሆኖም የደቡብ አፍሪካ ጉዞ ሳይሳካ ቀረ፡፡ የጀርመን ጉዞዬም በዛው ቀረ፡፡ አሁን ግን ተመልሼ ለመሄድ እየተዘጋጀሁ ነው፡፡
በአሁኑ ጊዜ ገቢህ ምንድን ነው?
በቶቶት የባህል አዳራሽ ሙሉ የባህል ባንዱ የእኔ ነው፡፡ ክሊፖች ዳይሬክት አደርጋለሁ፡፡ ኬሮግራፊ እሰራለሁ፡፡
አንዳንድ ዝግጅቶች ላይ ልጆቼን ይዤ እሰራለሁ፡፡ በዝግጅቱ ላይ መደነስ ካለብኝ እደንሳለሁ፡፡
ካሰለጠንካቸው ልጆች ትልቅ ቦታ የደረሱ አሉ?
አዎ፡፡ በቲያትር ቤቶች የተቀጠሩና ውጪ አገር ድረስ እየሄዱ የባህል ውዝዋዜ የሚሠሩ ወደ አምስት ልጆች አሉኝ፡፡

Read 6225 times Last modified on Saturday, 17 November 2012 12:55