Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 10 November 2012 13:51

ቴሌ የሞባይል አገልግሎት ማሻሻያ አደረገ ግለሰቦች የመስመር ሞባይል መጠቀም ይችላል

Written by 
Rate this item
(7 votes)

በአዲሱ አሰራር ደንበኞች ተጠቀሙም አልተጠቀሙም ይከፍሉት የነበረው ክፍያ የሚቀር ሲሆን ለተቋማት ብቻ ይፈቀድ የነበረው ባለመስመር ሞባይል ለግለሰቦች ተፈቅዷል፡፡ ባለካርድ ሞባይልን ወደ ባለመስመር፣ ባለመስመርን ወደ ባለ ካርድ መቀየርም ተፈቅዷል ያሉት አቶ አብዱራሂም፤ አምስትና ከዚያ በላይ ሠራተኞች ያሏቸው ድርጅቶች ለአገልግሎቱ ከተመዘገቡ (CUG) በተባለ መርሃግብር እርስ በርስ ለሚያደርጉት የሥልክ ጥሪ በደቂቃ 80 ሳንቲም ያህል የነበረው ወደ 30 ሳንቲም ዝቅ መደረጉንም ተናግረዋል፡፡ በአምስተኛው አይነት አገልግሎት 1174 በወር የከፈለ ደንበኛ፣ 2500 ደቂቃ የድምጽ ጥሪ፣ 350 የጽሑፍ መልእክት እና 50 ሜጋቢት የኢንተርኔት አገልግሎት ያገኛል፡፡

በዚሁ መሠረት “ቢዝነስ፣ ሞባይል 100” ተጠቃሚዎች በወር 52 ብቻ ከፍለው 100 ደቂቃ የስልክ ጥሪ፣ 30 የጽሑፍ መልእክት እና አምስት ሜጋቢትስ የኢንተርኔት አገልግሎት የሚያገኙ ሲሆን ቢዝነስ ሞባይል 250፣ 500 እና 1000 ሺህም ከ122 ብር እስከ 470 ብር ከፍለው ለየአይነቱ የተፈቀደውን አገልግሎት ያገኛሉ፡፡ ኢትዮ ቴሌኮም (ቴሌ) ከትናንት በስቲያ ጀምሮ አዲስ የሞባይል አገልግሎት ማሻሻያ ማድረጉን አስታወቀ፡፡ የድርጅቱ የውጭ ግንኙነት መምሪያ ሃላፊ አቶ አብዱራሂም አህመድ ለአዲስ አድማስ እንደገለፁት፤ “with in Business Mobile” በተሰኘውና የማስተዋወቂያ ፕሮግራሙ እስከ ጥር 23 በሚቆየው አዲሱ መርሃግብር ግዙፍ፣ መካከለኛ እና አነስተኛ የንግድ ተቋማት አምስት አይነት አገልግሎት የሚያገኙ ሲሆን አምስት እና ከዚያ በላይ ሠራተኞች ያሏቸው ተቋማት ለእርስ በርስ ሞባይል ጥሪ የአገልግሎቱን አዲስ መርሃ ግብር ለመቀላቀል ካሰቡ ከግማሽ በላይ ቅናሽ ይደረግላቸዋል፡፡ ለ “with in Business Mobile” ተጠቃሚዎች አገልግሎቱ ትላንት በስቲያ ጀምሮ ተለቋል፡፡

 

Read 8485 times Last modified on Saturday, 10 November 2012 13:56