Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 18 August 2012 12:34

ስለ አቡነ ጳውሎስ ምን ተባለ?

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

“መታሰር ማለት ያለመፈታት አይደለም”

- የብፁዕ ወቅዱስ ዶ/ር አቡነ ጳውሎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ

“… በምድር መከራ ተከበን በህይወት ፈተና ተጨንቀን ባለንበት ሰዓት ከሌሎች የሃይማኖት መሪዎች ጋር በመሆን በምህረት እንድንፈታ ከተጐጂ ቤተሰቦችና ከመንግስት ጋር በመተባበር እንቅስቃሴ መጀመሩን በሰማንበት ጊዜ ትልቅ ተስፋ ያገኘንበት ቀን ሆኗል፡፡ በፈጣሪ በታዘዘው መሠረት ወደኋላ ለበቀል እንዳናስብና እንዳናይ ተመክረናል፡፡ ካለፈው ሁሉ የሚመጣው እንደሚበልጥ አሳውቆናል፡፡ የሞተው አላዛር በጌታ ፈቃድና የድምፁ ጥሪ መቃብር ንዶ ዳግም ተወልዶ አፈር ከለበሰበት ጉድጓድ እንደወጣ ሁሉ ይህ ምድራዊ ተአምር እኛንም በተመለከተ ተፈፀመ ዳግማዊ አልአዛር አድርጐናል፡፡

ሁሉም የአዳም ልጅ በሰላም በፍቅር በመቀራረብ በመተሳሰብና በአንድነት ክርና ድር ተሳስሮ ይኖር ዘንድ የማያባራ ትምህርትና ምክር የሚሰጥባት ኢትዮጵያ ውስጥ ታስረን፤ በተማርነው ተምረን፣ በተገነዘብነው ሰርተን፣ ውጤት ባስመዘገብነው ተሳስተን፣ በተፀፀትነው አዝነን፣ በርህራሄ ባገኘነው ለታላቅ ታላቅ መሪ ምስጋናችን የላቀ ነው፡፡ አትሞቱም ትማራላችሁ፤ አትሰቃዩም ትፈታላችሁ ብለው የምስራች ድምጽ ላሰሙን ወገኖቻችንና የመንግስት ሃላፊዎች ሁሉ እናመሰግናለን”

- ሌ/ኮሎኔል ደበላ ዲንሳ (የብ/ወ/ዶር/አቡነ ጳውሎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ 20ኛ ዓመት በዐለ-ሲመት ላይ ካደረጉት ንግግር የተወሰደ)

“… በወጣት መነኩሴነቴ ዘመን የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤትን እወደው ነበር፡፡ ምክር ቤቱ “ከብርቱ መጋረጃ” ጀርባ ሆኖ ቤተ-ክርስቲያናትን ለመርዳት ያደርጋቸው የነበሩ ጥረቶች ያስደንቁኝ ነበር፡፡  በፀረ አፓርታይድ ትግሉ ውስጥ ያለው ሚናም ይማርከኝ ነበር፡፡

በ1967 ናይሮቢ በሚደረገው የም/ቤቱ ጉባዔ ተገኝቼ ስመለስ የወቅቱ የኮሙኒስት መንግሥት ባለሥልጣናት አሰሩኝ፡፡ 7 ዓመት አቆይተው ሲፈቱኝ እንደገና የቤት ውስጥ እሥር ተከተለኝ፡፡

… የዓለም አብያተ-ክርስቲያናት ምክር ቤት በዓለም ላይ ተስፋ፣ ውይይትና መቻቻል በሚያስፈልግበት ቦታ ሁሉ እየሄደ አብያተ-ክርስቲያናቱን በመወከል ተጨባጭ መፍትሔ የሚሰጥ ነው፡፡ … በመወያየት ቁስል እናድናለን፣ ልብን እናሸንፋለን፣ የተስፋ ምልክት እናመጣለን፤ ብዬ አምናለሁ፡፡ … በአገሬ ከ3000 ዘመን ጀምሮ  በተከታታይ አይሁዳውያንና ክርስቲያኖች የኖሩባት አገር ናት፡፡ ዛሬ ቤተ-ክርስቲያናችን 45 ማሊዮን አማንያን አሏት፡፡ 50,000 ቤተ-ክርስቲያናት አሉ፡፡ በተጨማሪም፤ ለማሰብ ቢከብዳችሁም ልንገራችሁ፡- 500,000 ካህናትና ቀሳውስት አሉን፡፡ …

የዲሞክራሲ ተጠቃሚ ለመሆን ህዝቡ መብቱን ብቻ ሳይሆን ኃላፊነቱንም መረዳት ይኖርበታል፡፡ … ዲሞክራሲ  ከተጀመረ አንስቶ ጊዜው ቀላል አልነበረም፡፡

ብዙ አለመግባባቶችና ግጭቶች የነበሩበት ነው፡፡ ለህዝቡ አደራ የምለው በማይስማሙበት ላይ እንዲቻቻሉ፣ እና ትዕግሥት እንዲኖራቸው ነው! በበኩሌ እንደማየው ኢትዮጵያ እድገት ማሣየት እየጀመረች ናት፡፡ የልዩነት መኖር ህዝቡን በጋራ ከመሥራት አያግደውም የሚል ተስፋ አለኝ! …

እንደ የዓለም አብያተ-ክርስቲያናት ፕሬዚዳንት ሁላችንም የየገዛ ቤተ-ክርስቲያኖቻችን ዕውነተኛ ተወካዮች ልንሆን ይገባል፡፡ … አንዱን ዓለም ከሌላው የተሻለ ለማድረግ አይደለም የቆምነው፡፡ እኛ የቆምነው የዓለምን ህዝብ በሙሉ ለማገልገል ነው፡፡

/ አባ ጳውሎስ ከዓለም አብያተ-ክርስቲያናት ም/ቤት የህዝብ ግንኙነትና መረጃ ቡድን አስተባባሪ ከአለክሳንደር ቤሎፖፕስኪ ጋር ካደረጉት ቃለ-መጠይቅ የተወሰደ/

 

 

 

Read 6652 times Last modified on Saturday, 18 August 2012 12:39