Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 27 August 2011 13:02

ብላክቤሪ.. የራሱን አዲስ የሙዚቃ አገልግሎት መስጠት ሊጀምር ነው

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የብላክቤሪ ሞባይል ስልክ አምራች ..ሪሰርች ኢን ሞሽን.. (Research in Motion/RIM) በቅርቡ የራሱን የሙዚቃ አቅርቦት ለተጠቃሚዎቹ ማድረስ ሊጀምር እንደሆነ ዴሊሜል አስታወቀ፡፡ ..ብላክቤሪ ሜሴንጀር.. ወይም በአጭሩ “BBM” በመባል የሚታወቀውን የሞባይል ኔትዎርኩን ሲያሻሽል የቆየው ኩባንያው እንደ አፕል እና ጉግል አንድሮይድ (ኦፐሬቴንግ ሲስተም) ካሉ ተቀናቃኞቹ እኩል ለመራመድ የሚያስችሉትን አንዳንድ ማሻሻያዎች በማድረግ ላይ የሚገኝ ሲሆን አዲስ ለሚጀምረው የሙዚቃ ስትሪሜንግ አገልግሎትም እንደ ሶኒ ሚዩዚክ እና ዋርነር ሚውዚክ ግሩፕ ካሉ ታላላቅ የሙዚቃ እንዱስትሪዎች ጋር ድርድር እያደረገ እንደሆነ ታውቋል፡፡

አፕል አይክላውድ (icloud) የተባለውን የሙዚቃ ስቶር ከፍቶ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ትንሽ ሰንበትበት ያለ ሲሆን ብላክቤሪ ደግሞ እ.አ.አ. ከመስከረም 6 በኋላ ይጀምራል፡፡
የብላክቤሪ ሞባይል ስልክ ተጠቃሚዎች ኩባንያው አዲስ ከሚከፍተው ውስጥ (ክሊፕ አልባ) ሙዚቃዎችን እና ሌሎች ፋይሎችን ቀድተው መውሰድ የሚችሉ ሲሆን የተለያዩ የሙዚቃ አፕሊኬሽኖችንም ማግኘት ይችላሉ፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ አዲሱ የብላክቤሪ ኔትዎርኪንግ ሲስተም ፈጣን እና በዚያ ለሚደረጉ የተለያዩ የመረጃ ልውውጦች የሚጠይቀው ወጪም በጣም አነስተኛ በመሆኑ በተጠቃሚው ዘንድ ተቀባይነትን ሊያስገኝለት እንደሚችል የተነገረ ሲሆን በአዲሱ ቨርዥን ተጠቃሚዎች በአነስተኛ ወጪ የተለያዩ መልእክቶችን ከመቀባበል ባሻገር ዜናዎችን እና የቪዲዮ ጌም አፕሊኬሽኖችን ሁሉ ማግኘት ይችላሉ፡፡

 

Read 2995 times Last modified on Saturday, 27 August 2011 13:05