Saturday, 13 August 2011 09:39

ፒያሳን እንዳየ“ትና አንዳነበብኳት

Written by  ጃሚ
Rate this item
(0 votes)

የአዲስአበባበርካታነባርሰፈሮችለልማትናለሕንፃግንባታፈርሰዋል፤እየፈረሱየሚገኙምአሉ፤ገና     ወደፊትየሚፈርሱምአሉ፡፡እንደነዶሮማነቂያናሠራተኛ ሰፈር ያሉት የፒያሳ ነባርሰፈሮችም ከአራት ኪሎ በመቀጠል ለመፍረስ ጊዜያቸውን እየጠበቁ ነው፡፡ ልክ እንደ አራት ኪሎና መርካቶ ሁሉ ፒያሳም በከፊል ፈርሳ ከመገንባቷ በፊት ውስጣዊ ገታዋን፣ የነዋሪዎቿን የሕይወት መስተጋብር እና ሌሎችም tእውነታዎች ለኛና ለቀጣይ ትውልዶች ዘላለማዊ የሚያደርግ መሐፍ ባሳለፍነው ሳምንት ተበርክቶላታል፡፡ ይኸው በጋዜጠኛ መሀመድ ሰልማን የተፃፈው መጽሐፍ ርእስ ..ፒያሳ.. ይሰኛል፡፡

ከጥቂት ዓመታት በፊት ደራሲና ጋዜጠኛ ዓለማየሁ ገላጋይ አራት ኪሎ ገና ሳትፈርስ ..አጥቢያ.. በተሰኘው ረጅም ልቦለድ መጽሐፉ አራት ኪሎን ለዘላለሙ ሕያው አድርጓታል፡፡ እነ ..አዝማሪ ሰፈር..፣ ..መጠበቂያ ሰፈር.. እና ሌሎችም የአራት ኪሎ ሰፈሮች አሁን ባይኖሩም በ..አጥቢያ.. ውስጥ አጠቃላይ ገታቸውንና ነዋሪዎቻቸው የኖሩት ህይወት ሥዕላዊ በሆነ መልኩ በጥልቀትና በስፋት ተከትቧል፡፡ ጋዜጠኛ ብርሃኑ ሰሙም ..ከእንጦጦ ሐሙስ ገበያ እስከ መርካቶ.. በሚለው መሐፉ ለመርካቶ ተመሳሳዩን አድርጓል፡፡ በብርሃኑ መጽሐፍ ውስጥ በጥልቀት የተገለፁት የንግድ መደብሮችና የመገበያያ ስፍራዎች አሁን በሕንፃዎች ቢተኩም የቀድሞ ሁኔታቸውን አሳይቶናል፡፡ መሐፍ ዘላለማዊ ሰነድ ነው የሚባለውም ከዚህ አንፃር ነው፡፡ መሐመድ ሰልማንም ..ፒያሳ.. በተሰኘው መጽሐፉ እንደ እጁ መዳፍ የሚያውቃትን ፒያሳ ከዚህ በፊት ባላስተዋልናት መልኩ ኢ-መደበኛ በሆነና ከዚህ ቀደም በ..አዲስ ነገር.. ጋዜጣ አንባቢያን ዘንድ በሚታወቅበት ውብ ቋንቋው ያስጐበኘናል፡፡ ለትረካው ስለ ፒያሳ ከዚህ በፊት ያልነበረንን ተጨማሪ አጉሊ መነር ይለግሰናል፡፡
ታላቁ ምሁር ገብረሕይወት ባይከዳኝ አንድ ፀሐፊ ሦስት ነገሮች ያስፈልጉታል ይላሉ፤ መርማሪ ልቦና፣ አስተዋይ አይንና ውብ ቋንቋ፡፡ ከነዚህ ውስጥ አንዱ ቢጐድል መጽሐፉ ስንኩል ይሆናል፡፡ ከዚህ በፊት በጋዜጣ ጽሁፎቹ ውስጥ እንዳስተዋልኩት በዚህ መጽሐፍም መሐመድ ሰልማን ከሥነ-ጽሑፍ ተሰጥኦው በተጨማሪ ሦስቱንም መታደሉን ተመልክቼያለሁ፡፡
ደራሲው ምስጋናው፣ መግቢያውንና መሿለኪያውን ሳይጨምር በ181 ገፆች አጠናቅሮ ለአንባቢያን ባቀረበው በዚህ መጽሐፉ ውስጥ አሥራ አምስት ታሪኮችን አካቷል፡፡ አብዛኞቹ ታሪኮች በ..አዲስ ነገር.. ጋዜጣ ላይ የቀረቡ ቢሆንም በመጽሐፉ መጀመሪያ ላይ ማህሙድ ጠብቂኝ በሚል ርእስ የቀረበውና ስለ ፒያሳ በጥልቀት የሚያወሳው ትረካ የመጽሐፉን ሰፊ ክፍል ይወስዳል፡፡ ይህን ትረካ በሸገር ኤፍኤምና በቪኦኤ አድማጮች በከፊል ተተርኮ ነበር፡፡ መሀመድ ሰልማን በመጽሐፉ ውስጥ ትረካውን የሚያስኬደው በተለመደ ዘዬው አንባቢውን ከአጠገቡ ያለ ያህል እያጫወተ (እያስጐበኘ) በሁለተኛ መደብ ነው፡፡
..ፒያሳ አንድ ሺህ አንድ መቶ ካፌዎች ያሉባት ቅመም የሆነች ሰፈር ናት፡፡ አንድ ሺህ አንድ መቶ ቆንጆ ልጃገረዶች ደግሞ በካፌዎቿ ውስጥ ተኮልኩለው ኮካ በ..ስትሮ.. ይጠጣሉ፡፡ ..ስትሮ.. ምን እንደሆነ ካላወቅክ የፒያሳ ልጅ አይደለህም ማለት ነው፡፡ ..ስትሮ.. በቆንጆ ልጅ ከንፈርና በቆንጆ ብርጭቆ መሀል የተሰራ የላስቲክ ድልድይ ነው፡፡
..ፒያሳ በካፌ ብዛት ..ከምስራቅ አፍሪካ አንደኛ ናት.. እኔ እንዳልመስልህ ይህን ያልኩት፤ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ነው እንዲያ ያለው፡፡ የአገሬ ቲቪ ብዙውን ጊዜ ሀቅ ህቅ የሚለው ቢሆንም ቅሉ ስለ ፒያሳ በተናገረው ግን አንዳችም እንዳልኳሸ እምላለሁ.....
መሀመድ በዚህ ትረካው የፒያሳን ካፌዎች፣ የተለያዩ ሰፈሮቿን፣ ሌሊቶቿን፣ ምግብ ቤቶችን፣ ቤርጐዎቿን፣ ቡቲኮቿን፣ የእምነት ማእከሎቿን፣ ሲኒማ ቤቶቿን፣ ኬክ ቤቶቿን፣ ሆቴሎቿን፣ ቡና ቤቶቿን እንዲሁም ቤተ-መፃህፍቷን ባማረ ቋንቋና ለዛ ይገልፃቸዋል፡፡ አጫጭር አረፍተ-ነገሮቹ፣ የሁለተኛ መደብ ትረካው፣ ኢ-መደበኛ የትረካ ቋንቋው፣ አዝናኝ አገላለፆቹና ልዩ እይታው አንባቢውን በምናብ ፒያሳ እንዲከትምና ትረካውን በከፍተኛ ጉጉት እንዲከታተል ያስገድዳሉ፡፡
መሐመድ ፒያሳን አስመልክቶ ያሉትን ጥሬ ሀቆችና ነባራዊ እውነታዎች እንደ ጋዜጠኛ ትዝብት እንዳሉ አያስቀምጣቸውም፡፡ በራሱ የቋንቋ ዘዬ  ፈጠራን በመጨመር የበለጠ ጉልበት፣ ለዛና ጣእምን ለአንባቢው እንዲለግሱ ያደርጋቸዋል፡፡ የሥነ-ጽሑፍ ባለሞያዎች ይህን አይነቱን ፈጠራ ኢ-ልቦለዳዊ ፈጠራ (creative non-fiction) ይሉታል፡፡ አንድ አስረጂ ከዚሁ ትረካ እንመልከት፡፡
..መቼ ለታ ዶሮ ማነቂያ ሄድኩ፡፡ ኪሴ ማፍሰስ ስለጀመረ ሰፈሩን ከሞሉት ማዘር ቤቶች ወደ አንዱ ጐራ አልኩኝ፡፡ ሁሉም የምግብ ዝርዝሮች የቤቱ ግድግዳ እየተፋቀ ተጽፈዋል፡፡ የምግቦቹ ዋጋ ከ10 ብር እንዳይዘል ከፍተኛ ጥንቃቄ ተደርጓል፡፡ ለምሳሌ ..ጥብስ 9 ብር ከ75 ሳንቲም.. ይላል፡፡ በዚህ ድንቅ ቤት ድንቅ ምሳ በልቼ ልወጣ ስል እንዲህ የሚል ጽሑፍ ከበሩ የውስጠኛው ክፍል አነበብኩ፡፡ ..ቅሬታዎን ለኛ፣ አድናቆትዎን ለጓደኛ!!.. በመጨረሻም ተመጋቢዎቹ ከመውጣታቸው በፊት ከተሰነጣጠቀው የቤቱ ግድግዳ ቀጭን እንጨት ሲመዙ አየሁ፡፡ ስቲኪኒ መሆኑ ነው፡፡ ሲሉ ሰምታ ዶሮ ታንቃ ሞተች!...
የሥነ ጽሑፍ አንዱ ግብ ተደራሲውን ማዝናናት ነው፡፡ በዚህ ረገድ መሀመድ ተሳክቶለታል፡፡ በዚህ የኑሮ ጣጣና ውጣ ውረድ መሃል አንባቢውን ለማዝናናት የተቸገረ አይመስልም፡፡ ማዝናናቱ እንዳለ ሆኖ ሁፎቹ መራር እውነታንና አስከፊ ገታን መቋታቸው አልቀረም፡፡ በፒያሳ የሕፃናት ሴተኛ አዳሪዎች እንደ አሸን መፍላት ከአስከፊ ገታዎች አንዱ ነው፡፡
.....ከትግራይ ሆቴል እስከ ጣይቱ ሆቴል ያለውን መንገድ ታውቀዋለህ? ይህ አጭር ጐዳና የያውን ረጅም ጉድ በዝርዝር ለመግለ እንደ መስቀል አደባባይ ሰፊ ብራና ቢገኝም የሚሞከር አይደለም፡፡ በያዘው የሴተኛ አዳሪዎች ብዛት ከምስራቅ አፍሪካ አንደኛ ሳይሆን አይቀርም፤ ከአዲሳባ ግን ከቺቺንያ ቀጥሎ ሁለተኛ እንደሆነ ስነግርህ ያለጥርጥር ነው፡፡ በዚህ ሰፈር ንጉሳቸውን እንደሚጠብቁ ሚኒስትሮች የመንገዱን ግራና ቀኝ ተሰልፈው የሚቆሙ ልጅ እግር ኮማሪቶች በየእለቱ ይወለዳሉ፡፡ ዳግም በየምሽቱ ቁጥራቸው ይጨምራል፡፡ ከየት ነው የሚፈጠሩት ልትል ትችላለህ፡፡ ሴቶቹ ..አራት ኪሎን..፣ ..አውቶብስ ተራን..፣ ..ጣልያን ሰፈርን.. ከመሰሉ ጐረቤቶች ወደ ፒያሳ ይፈልሳሉ፡፡ ስደት ወደ አረብ አገር ብቻ መስሎሃል? ወደ ፒያሳም ስደት አለ፡፡ ከነዚህ ጐረቤት ሰፈሮች አታለው የሚያመጧቸው ደግሞ እሳት የላሱ የፒያሳ ደላሎች ናቸው፡፡ እንዲህ ይሏቸዋል፤ ..ፒያሳ የሚባል አገር አለ፤ ወርቅ የሚታፈስበት፣ ባለፀጋ የሚኮንበት፣ ፓስፖርት አውጪና ወደ ፒያሳ ተሰደጂ፤ ለቤተሰቦችሽ ረብጣ የፒያሳ ዶላር ትልኪያለሽ.....
ደራሲው አዲስ አበባን ከነጉድፏ አሳምሮ የሚያውቃት ይመስላል፡፡ ጉድፎቿን ሲገልም ከአሪፍ ደራሲ እንደሚጠበቀው በተለየ እይታና አስተውሎት ነው፡፡ ይህን ለማረጋገጥ በመሐፉ ውስጥ ..ዶሮ ማነቂያ.. በሚለው ርእስ ስር ጥቂት መስመሮችን ማንበብ ይበቃል፡፡
..የትም ሰፈር ከዋናው አስፋልት ጀርባ ጉድ እንጂ ሌላ የለም፡፡ ጉዱን የጋረዱት ፎቆች ናቸው... ለመሆኑ ኢትዮጵያ ውስጥ የፎቅ ጥቅም በስንት እንደሚከፈል ታውቃለህ? በሁለት ካልክ ትክክል ነህ፡፡ የመጀመሪያው የፎቁ ባለቤት ብዙ መስታወት እንዳለው ማስመስከር ሲሆን ሁለተኛውና ዋነኛው ግን ከፎቁ ጀርባ ያለውን ሰፈር ገመና መሸፈን ነው፡፡ ይህ ካልገባህ ሂድ አምባሳደር፣ ሂድ ቦሌ፡፡ የአገርህ ቴሌቪዥን የሚኮራባቸው እነ ..ሸራተን..፣ እነ ..ደምበል..፣ እነ ..ጌቱ ኮሜርሻል..፣ እነ ..አበሩስ..፣ እነ ..ሜጋ.. ጀርባ ማንም ሳያይህ ግባ ትበረግጋለህ፡፡ ከዚያን እለት ጀምሮ ፎቆቹን ታከብራለህ፡፡ ፎቆቹ ለአገርህ የዋሉት ውለታ እየታሰበህ እንባህ በአይንህ ግጥም ይላል.....
መሐመድ ሰልማን አሁን ኑሮውን በፈረንሳይ እንዳደረገው ስመ-ጥሩ የቼክ ሪፐብሊክ ደራሲ ሚላን ኩንዲራ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁነቶችን በፌዝ፣ በቧልትና በስላቅ የማቅረቡን ዘይቤ በዚህ መጽሐፉ ተከትሏል፡፡ ስለ ኢቴቪ (..ኢቴቪና ተዛማጅ ትዝታዎቼ..)፣ በአዲሱ ትውልድ ዘንድ አማርኛችን ስለተጋረጠበት ከፍተኛ ፈተና (..የኤደንና የሜላት አማርኛ..)፣ በርካታ ተማሪና ሠራተኛ የኑሮ ውድነቱን ለመቋቋም በቋሚነት ስለሚታደምባቸው (ረከስ ባለ ዋጋ ምግብን ስለሚያቀርቡ) ቤቶች (..ማዘር ቤቶች..፣ የመመረቂያ ጽሑፎችን በክፍያ ስለሚያዘጋጁ ..ምሁራን.. (..የመመረቂያ ሁፎች ጥቁር ገበያ..)፣ የጉዞ ማስታወሻዎችና ሌሎችም ሁፎቹን በዚህ መጽሐፉ ውስጥ አካቷል፡፡መጽሐፉN በወፍ በረር የቃኘሁበትን ዳሰሳዬን ደራሲው ለፒያሳ ሰዋዊ ሰብእናን አላብሶ በገለፀበት ማራኪ አንቀ §BÝ””..የፒያሳ ሆድ ካስቴሌ ነው፡፡ የፒያሳ ሀብት ወርቅ ቤቶቿ ናቸው፡፡ የፒያሳ ጆሮ ዳላስ ነው፤ የፒያሳ አይን ሲኒማ አምፔር ነው፤ የፒያሳ መልክ ውብ ሴቶቿ ናቸው፡፡ የፒያሳ የራስ ቅል ማዘጋጃ ቤት ነው፡፡ የፒያሳ ጭንቅላት ማን ነው?
..ወዳጄ ሆይ! በፒያሳ ውብ ጫማና ልብስ ብትሽቀረቀር፣ ካስቴሌ ሄደህ ከርስህን ብትሞላ፣ አምፒየር ሴት ሸጉጠህ ኋላ ወንበር ላይ ብትወሸቅ፣ ፒሳ ኮርነር ብትነጠፍ፣ በባቅላባ ጣእም እጅህን ብትቆረጥም፣ በኤንሪኮ ኬክ ብትንሳፈፍ፣ ለክሪያዚስ ጐጆ ኬክ ብትስገበገብ፣ በኡመር ኻያም ሩባያት ግጥም ብትሰክር፣ ማህሙድ ጋ ልጅቷን ጥበቃ በጭንቅላትህ ብትተከል፣ በዳላስ ሙዚቃ ብትመሰጥ፣ በሰንሻይን ሻምፓኝ ብትራጭ፣ የብሔራዊ ሎተሪ ዝሆን ቢደርስህ፣ የዶሮ ማነቂያን ቁርጥ ብትዘነጥል፣ ጭንቅላት ባዶ ከሆነ ምን ዋጋ አለው?..
..ጭንቅላትም ልክ እንደሆድህ ምግብ እንደሚፈልግ ታውቃለህ፡፡ ለዚህ ፒያሳ ..ብሪቲሽ ካውንስል አለልህ፤ ነበረልህ፡፡ ዛሬ ስልጣን መሰይጠን ነው ብለው በስደት ሆነው አገርህን በእውቀት ከሚያሾሯት ኢትዮጵያውያን የሚበዙት ጭንቅላታቸውን የት የኮተኮቱት ይመስልሃል? በብሪቲሽ ካውንስል ቤተ-መፃህፍት ነው.....

 

Read 3503 times Last modified on Saturday, 13 August 2011 09:45