Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 29 September 2012 10:07

ጁዲ ከፍተኛውን የቲቪ ክፍያ ታገኛለች

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ጀጅ ጁዲ የሚባለውን የፍርድ ቤት ሾው የምታቀርበው ጁዲ ሼሊንደን በአሜሪካ የቲቪ ኢንዱስትሪ ከፍተኛውን ክፍያ በማግኘት እንደምትመራ ዘ ቢዝነስ ኢንሳይደር አመለከተ፡፡በተለያዩ የቴሌቭዥን ጣቢያዎች ላይ በአይዶል እና የታለንት ሾው ዝግጅቶች ዳኝነት፤ በፍርድቤት ሾው አዘጋጅነትና እንዲሁም በዜና እና ልዩ ፕሮግራሞች መሪነት እና አቅራቢነት የሚሰሩ ባለሙያዎች በሚያገኙት ክፍያ በአሜሪካ የመዝናኛ ኢንዱስትሪ በሆሊውድ ካሉ ምርጥ ተዋናዮች ብልጫ እንዳላቸው ዘገባው አትቷል፡፡የጀጅ ጁዲ የፍርድ ቤት ሾው አቅራቢ በ45 ሚሊዮን ዶላር ክፍያዋ መሪነቱን እንደያዘች የገለፀው ዘ ቢዝነስ ኢንሳይደር የቀድሞው የአሜሪካን አይዶል ዳኛ እና አሁን በራሱ ኤክስ ፋክተር የተባለ የተስጥኦ ማፈላለጊያ ሾው የሚሰራው እንግሊዛዊው ሲሞን ኮዌል 40 ሚሊዮን ዶላር በመከፈል ሁለተኛ ደረጃ ላይ ነው ብሏል፡፡ በአሜሪካ የቴሌቭዥን ኢንዱስትሪ ከፍተኛ ዘመን በማገልገል የሚታወቀውና ዘንድሮ በሲቢኤስ የሚያስተላልፈው ‹ሌት ናይት ሾው› የማቅረቡን ውል ለሁለት ዓመት ያሳደሰው ዴቨድ ሌተርማን 31 ሚሊዮን ዶላር በመከፈል 3ኛ ደረጃ ይዟል፡፡ በቴሌቭዥን ስራዎች ከፍተኛ ክፍያ በመማረክ በርካታ የመዝናኛው አንዱስትሪ ዝነኞች ከሆለውድ እየኮበለሉ ናቸው የሚለው ዘ በዝነስ አንሳይደር ማርያ ኬሪ እና ብሪትኒ ስፒርስን በምሳሌነት ጠቅሷቸዋል፡፡

በአሜሪካን አይዶል ዳኝነት ለመስራት የተሾመችው ማርያ ኬሪ 1 ሚሊዮን ዶላር ተከፍሏት 6ኛ ደረጃ ስትወስድ በኤክስ ፋክተር ላይ ዳኛ ሆና የተመደበችው ብሪትኒ ስፒርስ ደግሞ በ16 ሚሊዮን ዶላር ክፍያ 8ኛ ደረጃ ተሰጥቷታል፡፡ በአሁኑ ወቅት የሆሊውድ ምርጥ ተዋናዮች ለአንድ ፊልም ስራ የሚከፈላቸው ከ10  ሚሊዮን ዶላር አይበልጥም፡፡የ69 ዓመቷ ጁዲ ሼሊንደን በጥብቅና እና በዳኝነት ሙያ ብቻ ሳይሆን በቴሌቭዥን ስብዕናዋ እና በአደራዳሪነት ተግባሯ በመላው አሜሪካ የምትከብር ሴት ናት፡፡ በዳኝነት በተለይ በቤተሰብ ጉዳዮች ላይ ባተኮረ የህግ ሙያዋ ለ25 ዓመታት ያገለገለችው ጁዲ በፍርድ ቤት የቶክ ሾው ዝግጅቷ ስትሰራ17 ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ በሲቢኤስ ቻናል ላለፉት ሶስት ዓመታት እያንዳንዱ የ22 ደቂቃዎች የጀጅ ጁዲ ሾው ከ9 ሚሊዮን በላይ ተመልካች በሰሜን አሜሪካ እያገኘም ቆይቷል፡፡

 

 

 

Read 4354 times Last modified on Saturday, 29 September 2012 10:11