የእንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የስነ ጥበብ ትምህርት ክፍል በስዕልና ቅርጻ ቅርጽ ለሶስት ዓመት ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ያስመረቀ ሲሆን፤ በሚቀጥለው ሳምንት የተመራቂዎቹ ስራዎች ለእይታ ይቀርባሉ፡፡ የተማሪዎቹ የስዕልና የቅርፃ ቅርፅ ስራዎች በኮሌጁ አርት ጋለሪ ከመጪው ማክሰኞ ጀምሮ የሚቀርብበት ኤግዚቢሽን፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አቶ አሚን አብዱልቃድር በተገኙበት ተመርቆ ይከፈታል፡፡ ኮሌጁ ማንኛውም ህብረተሰብ ኤግዚቢሽኑን እንዲጐበኝ ጋብዟል፡፡