Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 22 September 2012 12:51

ሚዩዚክ ሜይዴይ በዶ/ር ሙሴ መጽሐፍ ላይ ይወያያል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የመጽሐፍት ንባብን ለማበረታታት በየሁለት ሳምንቱ የመጻሕፍት ንባብ እና ውይይት እያደረገ ያለው ሚዩዚክ ሜይዴይ ኢትዮጵያ የዶ/ር ሙሴ ያዕቆብ ሥራ በሆነው “ሃያ አስራሁለቱ የፀለምት ቀጠሮ” ላይ እንደሚወያይ አስታወቀ፡፡ነገ ከቀኑ 8 ሰዓት አምስት ኪሎ በሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዘክር (ሙዚየም) አዳራሽ የሚካሄደውን የዚህን መፅሐፍ ውይይት ባለሙያው አቶ አስቻለው ከበደ የመነሻ ሀሳብ በማቅረብ እንደሚመሩት ድርጅቱ ገልጿል፡፡በተመሳሳይ መድረክና ሰዓት ሊካሄድ የነበረው የግጥም መፅሐፍ ውይይት፣ ዳሰሳ አቅራቢው አቶ እዝራ አብደላ ለሥራ ጉዳይ ወደ ውጭ ሀገር በመሄዳቸው መሰረዙን ሚዩዚክ ሜይዴይ ኢትዮጵያ ጠቁሟል፡፡ሚዩዚክ ሜይደይ ኢትዮጵያ ላለፉት ስምንት ዓመታት ከ200 በሚበልጡ የአማርኛ የተለያዩ ዘውጐች መፅሃፍት ላይ ውይይት አድርጓል፡፡

 

 

Read 4466 times Last modified on Saturday, 22 September 2012 13:10