Print this page
Saturday, 22 September 2012 12:41

ለ5ኛው ሬዚዳንት ኢቭል ገበያው ቀንቶታል

Written by  girumsport@gmail.com
Rate this item
(0 votes)

ባለፈው ሰሞን በ50 ዓለም አቀፍ የገበያ መዳራሻዎች ለዕይታ የበቃው “ዘ ሬዚዳንት ኢቭል፡ ሬትሪቢውሽን” በቦክስ ኦፊስ የገቢ ደረጃውን እየመራ ነው፡፡ ፊልሙ የ ዘ ሬዚዳንት ኢቭል ተከታታይ ፊልሞች 5ኛው ምእራፍ ሲሆን  በ65 ሚሊዮን ዶላር በጀት ተሰርቷል፡፡ ለእይታ በበቃባቸው የመጀመርያዎቹ ሶስት ቀናት በሰሜን አሜሪካ 21.1 ሚሊዮን ዶላር ሲገኝበት በመላው ዓለም ገቢው 71 ሚሊዮን ዶላር ደርሷል፡፡ሚላ ጆቮቪች የፊልሙ መሪ ተዋናይ ስትሆን የትዳር አጋሯ የሆነው ፖል ደብሊው ኤስ አንደርሰን ከሬዚዳንት ኢቭል 5 ፊልሞች  የመጀመርያውን አራተኛውንና የአሁኑን አምስተኛ ክፍል ዲያሬክት አድርጓል፡፡

በአጠቃላይ በጀታቸው 183 ሚሊዮን ዶላር የወጣባቸው አምስቱ ፊልሞች ባለፉት 10 ዓመታት በመላው ዓለም ያስገቡት ከ675 ሚሊዮን ዶላር በላይ ነው፡፡  ሬዚዳንት ኢቪል ሬትሪቢውሽን አስቀድሞ ከነበረው የፊልሙ 4ኛ ክፍል በመጀመርያ ሳምንት ገቢው የተሻለ ዲያሬክተሩ የፊልሙን 6ኛ ክፍል ለመስራት አሁን መታየት የጀመረው ዘ ሬዘዳንት አቭል ሬትሪቢውሽን በገቢ የሚኖረው ስኬት እንደሚያነሳሳው ተናግሯል፡፡ በሬዚዳንት ኢቭል ፊልሞች መሪ ተዋናይነት ስኬታማ የሆነችው የ36 ዓመቷ ሚላ ጆቮቪች በ5ኛው ክፍል ያገኘችውን ልምድ ውብ ስትል ገልፃዋለች፡፡ ሚላ ጆቨቪች በዩክሬን ኪዬቭ የተወለደችውና በ5 ዓመቷ ከቤተሰቧ ጋር ወደ ኒውዮርክ ተሰድዳ አሜሪካዊ ዜግነቷን ያገኘች ናት፡፡ ሚላ ጆቮቪች ከትወና ሙያዋ ባሻገር በሙዚቃ ተጨዋችነት፤ በሞዴል እና በፋሽን ስራዎቿ ስኬታማ ሆና እስከ 31 ሚሊዮን ዶላር ሃብት ያካበተች ናት፡፡

 

 

 

Read 2605 times Last modified on Saturday, 22 September 2012 12:47