በአጠቃላይ በጀታቸው 183 ሚሊዮን ዶላር የወጣባቸው አምስቱ ፊልሞች ባለፉት 10 ዓመታት በመላው ዓለም ያስገቡት ከ675 ሚሊዮን ዶላር በላይ ነው፡፡ ሬዚዳንት ኢቪል ሬትሪቢውሽን አስቀድሞ ከነበረው የፊልሙ 4ኛ ክፍል በመጀመርያ ሳምንት ገቢው የተሻለ ዲያሬክተሩ የፊልሙን 6ኛ ክፍል ለመስራት አሁን መታየት የጀመረው ዘ ሬዘዳንት አቭል ሬትሪቢውሽን በገቢ የሚኖረው ስኬት እንደሚያነሳሳው ተናግሯል፡፡ በሬዚዳንት ኢቭል ፊልሞች መሪ ተዋናይነት ስኬታማ የሆነችው የ36 ዓመቷ ሚላ ጆቮቪች በ5ኛው ክፍል ያገኘችውን ልምድ ውብ ስትል ገልፃዋለች፡፡ ሚላ ጆቨቪች በዩክሬን ኪዬቭ የተወለደችውና በ5 ዓመቷ ከቤተሰቧ ጋር ወደ ኒውዮርክ ተሰድዳ አሜሪካዊ ዜግነቷን ያገኘች ናት፡፡ ሚላ ጆቮቪች ከትወና ሙያዋ ባሻገር በሙዚቃ ተጨዋችነት፤ በሞዴል እና በፋሽን ስራዎቿ ስኬታማ ሆና እስከ 31 ሚሊዮን ዶላር ሃብት ያካበተች ናት፡፡