የአዲስ አበባ ፖሊስ ሕገ-ወጥ የይለፍ ወረቀቶችን፣ ያለፈቃድ የተለጠፉ ጥቁር ስቲከሮችን እና የተለያዩ የትራፊክ ደንብ ጥሰቶችን በሚፈጽሙ ተሽከርካሪዎችና ሞተር ሳይክሎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር መጀመሩን አስታወቀ። ፖሊስ ባለፉት አንድ ሳምንት ብቻ ባደረገው አሰሳ ከ1,100 በላይ ተሽከርካሪዎች ላይ ሕጋዊ እርምጃ ወስዷል።
በዚህም መሠረት፡-
899 ሕገ-ወጥና ጊዜያቸው የረፈደ ስቲከር የያዙ፣
153 የደንብ ጥሰት የፈጸሙ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች፣ እንዲሁም
59 አፈር ጭነው መንገድ ያበላሹ ተሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ ተወስዷል። ፖሊስ ቁጥጥሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አሳስቧል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…

