Monday, 26 October 2026 16:25

በጀርመንና አየርላንድ የኢትዮጵያውያን አትሌቶች የድል ማዕበል

Written by 
Rate this item
(3 votes)

???? በፍራንክፈርት ማራቶን (ወንዶች)፦ አትሌት ጂራታ ሌሊሳ 2:05:26 በሆነ ሰዓት የግል ምርጥ ሰዓቱን በማሻሻል አንደኛ በመውጣት አሸንፏል፤ አትሌት አቤ ጋሻሁን 2:07:19 በሆነ ሰዓት 6ኛ ደረጃን ይዟል።

???? በፍራንክፈርት ማራቶን (ሴቶች)፦ አትሌት ዘይነባ ይመር 2:19:45 በሆነ ሰዓት የውድድሩ አሸናፊ ስትሆን፣ አትሌት በሪሃ ገ/ዮሐንስ (3ኛ)፣ አትሌት አሰለፍ አማረ (4ኛ)፣ አትሌት ስራነሽ ይርጋ (5ኛ)፣ አትሌት ምህረት ገመዳ (6ኛ) እና አትሌት ብርቄ በየነ (9ኛ) ደረጃን በመያዝ አስደናቂ የበላይነት አሳይተዋል።

???? በደብሊን ማራቶን (ወንዶች)፦ በአየርላንድ በተካሄደው ውድድር አትሌት አባይ አለሙ 2:10:29 በሆነ ሰዓት በመግባት በወንዶች ምድብ አንደኛ በመሆን አሸንፏል።

???? በደብሊን ማራቶን (ሴቶች)፦ አትሌት ዘነቡ ፍቅዳው 2:24:26 በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ የሴቶች ምድብ የደብሊን ማራቶን አሸናፊ ሆናለች።

የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas

Read 1058 times