Wednesday, 14 October 2026 09:14

ማንቼስተር ሲቲ ከፒኤስጂ

Written by 
Rate this item
(2 votes)

በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የ2ኛ ዙር መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት 9 ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡

በዚህም ምሽት 4 ሰዓት ላይ ማንቼስተር ሲቲ በሜዳው ኢትሃድ ከፒኤስጂ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ ይጠበቃል፡፡

በፕሪሚየር ሊጉ እስካሁን ያደረጋቸውን ጨዋታዎች በሙሉ ድል ያደረገው ማንቼስተር ሲቲ በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግም ያለመሸነፍ ጉዞውን ለማስቀጠል ወደ ሜዳ ይገባል፡፡

ማንቼስተር ሲቲ በመጀመሪያ ዙር የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ወደ ፖርቹጋል አቅንቶ በሃንድ ሁለት ግቦችን ፖርቶን ማሸነፉ ይታወሳል፡፡

ተጋጣሚው የወቅቱ የሻምፒየንስ ሊጉ አሸናፊ ፒኤስጂ በበኩሉ በመጀመሪያ ዙር የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ስሎቫን ብራቲስላቫን 6 ለ 1 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፉ አይዘነጋም፡፡

Read 1664 times