Wednesday, 14 October 2026 06:46

የውባንቺ ፕሮጀክት ፆታዊ ጥቃትን በኪነ ጥበብ ለመታገል ታላቅ ፌስቲቫል ሊያካሂድ ነው

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

ብለብሎ ሩዥ ፋውንዴሽን (BBRF) ከእንግሊዙ “ካዙም አርትስ” ጋር በመተባበር “ለምን ዝም አላችሁ?” በሚል መሪ ቃል በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ፆታዊ ጥቃቶችን ለመታገልና ማኅበረሰቡን ለማንቃት ያለመ ግዙፍ የኪነ ጥበብ ፌስቲቫል ሊያካሂድ ዝግጅቱን አጠናቋል።

ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ታዳጊዎች ባለፈው ዓመት ክረምት ጀምሮ በሞባይል ፎቶግራፊ፣ በቴአትር፣ በሙዚቃ እና በዳንስ ሲሰለጥኑ ቆይተው፣ ማኅበረሰቡን ለለውጥ የሚያነሳሱ የፈጠራ ሥራዎቻቸውን ለሕዝብ ለማቅረብ መዘጋጀታቸው ታውቋል።

የፌስቲቫሉ ዋና ዋና መርሃ ግብሮች ጥቅምት 7 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡30 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር አዳራሽ በሚቀርቡ ሙዚቃዊ ድራማዎች፣ ሥነ ግጥሞች እና የዳንስ ትርዒቶች ይጀምራል። በመቀጠልም ከጥቅምት 8 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ በአዲስ አበባ ፒያሳ (በአሮጌው ፖስታ ቤት በሚገኘው Creative Hub የፎቶ ኤግዚቢሽን ማዕከል) በታዳጊዎች የተነሱ የሞባይል ፎቶግራፎች ለ15 ቀናት ለሕዝብ ክፍት ሆኖ ይቆያል።

በተጨማሪም ማኅበረሰቡን በንቃት ለማሳተፍ የ#ውባንቺ ማኅበራዊ ሚዲያ ውድድር ተዘጋጅቷል፤ ተሳታፊዎች የሴቶችን ፆታዊ ጥቃት ለማስቆም መልዕክት የሚያስተላልፉ ፎቶግራፎችን በ#ውባንቺ ሃሽታግ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በማጋራት ለተዘጋጀው ልዩ የገንዘብ ሽልማት መወዳደር ይችላሉ።

አዘጋጆቹ የውባንቺ ፕሮጀክት ታዳጊዎች በጥበብ አማካኝነት ማኅበራዊ ለውጥ ለማምጣት ያላቸውን አቅም እንደሚያሳይና ለተጎጂዎች ድምፅ ለመሆን ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል።

የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas

Read 7523 times