Tuesday, 29 September 2026 08:37

ሚሊዮኖችን ያስዘነጠው አምባሳደር!

Written by 
Rate this item
(0 votes)
ኢትዮጵያ ውስጥ በሙሉ ልብስ ታዋቂና ዝነኛው ብራንድ አምባሳደር ነበር።
ከዚያ በፊት ከአስመራ "ሊያልፍ/Lialf" የሚባል ሙሉ ልብስ ይመጣ ነበር። ያ ግን በፋብሪካ ደረጃ አልነበረም። እኔም በወሬ ደረጃ ልጅ እያለሁ የሰማሁት እና ያነበብኩት እንጂ አልደረስኩበትም።
አምባሳደር እያለን በየዓመቱ ከ100,000 ልብስ በላይ እያለበስን አስመርቀናል፣ ሥራ አስይዘናል፣ ሞሽረናል። በዚህ ስሌት የአምባሳደር ልብስ ሚሊዮኖችን እንዳስዘነጠ ቢነገር እውነት ነው።
ሙሉ ልብስ ሁሉ ሱፍ አይደለም። ከልብስ ልብስ ይለያል። ጨርቁ፣ ስፌቱ፣ ክሩ፣ ከናማቻው፣ ክላፓው፣ እግር አወራረዱ፣ ...
በዚያው ቀጥለን ቢሆን ይሄኔ ዛምቢያ፣ ርዋንዳ፣ ዩጋንዳ፣ ቦትስዋና የኛ ገበያ ነበሩ።
እስኪ በአምባሳደር ሙሉ ልብስ የተመረቃችሁ፣ ያገባችሁ አለን በሉ።
_
የአምባሳደር ሙሉ ልብስ ገናና በነበረበት ዘመን የሽያጭ ቡድን መሪዎቹ በከፊል እነዚህ ነበሩ።
Get Toughe Zer
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Read 4670 times