Tuesday, 29 September 2026 08:20

የ17 ቢ. ዶላሩ የምስራቅ አፍሪካ ግዙፍ ፕሮጀክት ሊጀመር ነው

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የአፍሪካ ቁጥር አንድ ባለጸጋ አሊኮ ዳንጎቴ በምስራቅ አፍሪካ ትልቁን የ17 ቢሊዮን ዶላር የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ በኬንያ ላሙ ከተማ ሊገነባ ነው። ግዙፍ የግንባታ ማሽነሪዎችን የጫነው «ኤምቪ ዳ ያንግ» መርከብ ላሙ ወደብ መድረሱን ተከትሎ፣ የፋብሪካው የመሰረት ድንጋይ መጣል ስነ-ሰርዓት ከሁለት ቀን በኋላ ይካሄዳል። በዝግጅቱ ላይ የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ እና አሊኮ ዳንጎቴ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በቀን 700,000 ባርሬል ድፍድፍ ዘይት የማቀነባበር አቅም ይኖረዋል ተብሎ የታቀደው ይህ ማጣሪያ፣ ወደ 60,000 የሚጠጉ የስራ እድሎችን ይፈጥራል። ፕሮጀክቱ የምስራቅ አፍሪካን የኢኮኖሚ ገጽታ እና የኢነርጂ አቅርቦት በእጅጉ ይለውጠዋል ተብሎ ከፍተኛ ግምት ተሰጥቶታል።

Read 1055 times