Tuesday, 22 September 2026 11:50

"ትግላችን ለህዝብ ነው" እያላችሁ፣ የህዝቡን መከራና ስቃይ አታብዙ!

Written by 
Rate this item
(2 votes)
ጦርነትን መሸከም የምንችልበት ትከሻ፣ የጦርነትን ውጤቶች ማስተናገድ የምንችልበት አቅም የለንም። የጦርነትን አስከፊነትና ውጤቱን ደጋግመን አይተነዋል። ምንም የተለዬ ነገር አላመጣልንም። በተለይ በእርስ በርስ ጦርነት ያተረፍነው ነገር የለም። ውጤቱ "ውሀ ቅዳ ውሀ መልስ" (vicious circle) ነው። ስለሆነም፣ የውጭ ወራሪ ኃይልን ለመከላከል ካልሆነ በስተቀር፣ ጦርነት እንደዋዛ የሚገባበት አማራጭ አይደለም።
ያሉብን ችግሮችና አለመግባባቶች ይታወቃሉ። ችግሮቻችንንና/አለመግባባቶቻችንን በመነጋገርና በሠላማዊ መንገድ መፍታት ይሻላል። አሁንም አልረፈደም፤ ቆም ብሎ በሰከነ መንፈስ ማሰብ ጉዳት የለውም። በአጉል እልህና ፍጥጫ የሚሆን የለም።
እባካችሁ ለህዝቡ እዘኑለት። ህዝቡ የኑሮ ውድነቱ የፈጠረበት ሸክም ትከሻውን አጉብጦታል። በዚህ ላይ ጦርነት ከተጨመረበት ችሎ መቆም ያቅተዋል። "ትግላችን ለህዝብ ነው" እያላችሁ፣ የህዝቡን መከራና ስቃይ አታብዙ። ሌላውን ተውትና፣ ለወጣችሁበት ማህበረሰብ ርህራኄ ይኑራችሁ!?
እኔ ሳስበው ስለሚዘገንነኝ ነው‼️
Mohammed Ali Mohammed-
Read 22897 times