Thursday, 17 September 2026 11:28

መንግስት ለምን ዝምታን መረጠ ?

Written by 
Rate this item
(0 votes)
የዛሬ 4 አመት አገር ሰላም በነበረበት ገዜ የነበረኝን እረጅም የእረፍት ጊዜ ኢትዮጰያን እየተዘዋወርኩ በመጎብኘት አሳልፌዋለሁ። ገጠመኞቼንም በጽሁፍ እና በመስል አካፍያችሗለሁ ። ዛሬ ግን አዋሳ እንኳን ለመሄድ ግዜው ያስፈራል።
ያን ጊዜ ጅማ ቦንጋ ሚዛን ተፈሪን አልፌ እስከ ቴፒ መርቲ ጋምቤላ ድረስ ሄጄ አይቼዋለሁ። ዛሬ ግን ወደእዛ ለመሄድ ድፍረቱም የለኝም። በየጊዜው የምሰማው ወሬ ያስፈራል። መንግስት ግን በዚህ ጉዳይ ላይ ለምን ዝምታን መረጠ ?
ተዘዋውሬ እንዳየሁት በየገጠሩ ያለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ደግ የዋህ ሰላማዊ ነው። ዘረኝነት ክፋት አያውቅም ። እንደገና ሰላም ሆኖ እንገናኝ ይሆን ?
ትዝ ይለኛል የዛሬ 4 አመት የታሕሳሰ ገብርኤልን ያከበርኩት አምቦን አልፎ ጉዳር ላይ የሚገኘው የገብርኤል ደብር ነበር። አምቦ ብዙ ምርጥ ሰወች ተዋውቄባታለሁ ። አንድ ቀን እንደገና የምመለሰብት አጋጣሚ ይፈጣራል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።
በምስሉ ላይ የሚታየው የአምቦ ኪዳነምሕረት ቤተክርስተያን የዛሬ አራት አመት ግንባታ ላይ ሆና የቀረጽኩት ነው። ዛሬስ ግንባታው ተጠናቆ ይሁን ? አንድ ቀን እንደገና የአምቦ ኪዳነምሕረትን እሳለማለሁ። ስለቴንም አስገባለሁ።
Eduardo Byrono
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Read 5843 times