-
1. ካልጀመርን መጨረስ አንችልም፦ ማንኛውም ትልቅ ጉዞ የሚጀምረው በአንዲት እርምጃ ነው። የመጨረሻውን ግብ ለማየት የመጀመሪያውን እርምጃ የመውሰድ ድፍረት ያስፈልጋል።
-
2. ኢንቨስት ባላደረግንበት ትርፍ አንጠብቅም፦ በጊዜ፣ በጉልበት፣ በእውቀት ወይም በገንዘብ ዘር ባልዘራንበት ቦታ ፍሬ መከርን መጠበቅ አይቻልም። የምናወጣው መስዋዕትነት የምናገኘውን ውጤት ይወስነዋል።
-
3. ሳንሞክር ስኬትን መጠበቅ አይቻልም፦ ውድቀትን ፈርቶ አለመሞከር አሁኑኑ መሸነፍን መቀበል ነው። የስኬት መጀመሪያው ውድቀትንም ጭምር ለመጋፈጥ ፈቃደኛ መሆን ነው።
-
4. ከትላንት ካልተማርን ማደግ አንችልም፦ ትላንትና የዛሬ አስተማሪችን ነው። የሰራነውን ስህተት ሳናርምና አዳዲስ ትምህርቶችን ሳንቀስም ተመሳሳይ ቦታ ላይ እንደተሽከረከርን እንቀራለን።
-
5. ሪስክ ሳንወስድ ማሸነፍ አንችልም፦ ከለምድንበት ምቾት (Zone of Comfort) ሳንወጣ የሚገኝ ትልቅ ስኬት የለም። ትልልቅ ድሎች የሚገኙት የታሰበበትንና የተሰላውን ስጋት (Calculated Risk) ለመውሰድ ሲደፈር ብቻ ነው።
Published in
ጥበብ

