Friday, 28 August 2026 17:06

ትራምፕ ራሳቸውን “የታላቆች ታላቅ” ብለው ሰየሙ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

አነጋጋሪ ጉዳዮችን በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ በማጋራት የሚታወቁት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ራሳቸውን እስካሁን አሜሪካንን ከመሩ ፕሬዝዳንቶች ሁሉ የላቁ መሆናቸውን ገለጹ።

የመጀመሪያዎቹን ጨምሮ በፈታኝ ሁኔታ ውስጥ አሜሪካንን የመሩ የ34 ፕሬዝዳንቶችን ምሥል በመደርደር የተለያዩ ደረጃዎችን የሰጡት ትራምፕ ራሳቸውን “ከሁሉም ያላቁ” አድርገው በማቅረብ መነጋገሪያ ሆነዋል።

በትሩዝ ማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ በአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች ታሪክ ራሳቸውን “የታላቆች ታላቅ” በሚለው ደረጃ ላይ በማስቀመጥ ሌሎቹን በተለያዩ ደረጃዎች “ደካማ” እስከሚል ፈርጀው ከእሳቸው ስር አስቀምጠዋቸዋል።

በርካቶቹን የአሜሪካ ቀደምት ፕሬዝዳንቶች ከዝርዝሩ ውስጥ ባለማካተትም ቦታ ነፍገዋቸዋል። ምናልባትም ያልተካተቱት “ደካማ” ከተባሉት በታች ያሏቸውን ሊሆን ይችላል።

ከአውሮፓውያኑ 1789 አሜሪካ 47 ፕሬዝዳንቶች ተፈራርቀው የመሯት ሲሆን፣ በትራምፕ የደረጃ ዝርዝር ውስጥ የተካተቱት ግን 34ቱ ብቻ ናቸው። የዓለማችን የዲሞክራሲ ተምሳሌት የምትባለውን አገር እስካሁን ሴት ፕሬዝዳንት አልመራቻትም።

ትራምፕ ከንጽጽር ያቀረቧቸውን ቀደምት ፕሬዝዳንቶች በስድስት ክፍል የመደቧቸው ሲሆን፣ ራሳቸውን “የታላላቆች ታላቅ”፣ እርሳቸውን የሚከተሉትን ደግሞ “ታላቅ”፣ ከዚያም “ለታላቅነት የቀረቡ”፣ “መካከለኛ”፣ “ከመካከለኛ በታች” እና ደካሞች” ብለዋቸዋል።

“ደካማ” ከሚለው ምድብ ስር ያካተቷቸው ከእሳቸው የቀደሙትን ባራካ ኦባማ እና ጆ ባይደንን እንዲሁም ጂሚ ካርተር፣ ዋረን ሃርዲንግ እና ኡሊሴስ ግራንት ይገኙበታል።

BBC-

የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas

Read 3023 times