Thursday, 27 August 2026 12:36

በቁጥጥር ስር የዋለው የሐሰተኛ ሰነዶች ማምረቻ ፋብሪካ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የአዲስ አበባ ፖሊስ ባደረገው ጥብቅ ክትትል በጉለሌ ክፍለ ከተማ አዲሱ ገበያ አካባቢ በህትመት ስራ ስም ተሸሽጎ የተለያዩ ሀሰተኛ ሰነዶችን ሲያዘጋጅ የነበረው ካሊድ አወል የተባለ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሏል። በንግድ ቤቱ ውስጥ በተደረገ ብርበራ የበርካታ የመንግስት ተቋማት የራስጌና የክብ ማህተሞች፣ የልደት ምስክር ወረቀቶች፣ የግብር ከፋይ ማስረጃዎች፣ የፖሊስ የፎረንሲክ ማስረጃዎች እና የተሽከርካሪ ምርመራ ሰነዶችን ጨምሮ ለህገ-ወጥ ድርጊቱ የሚውሉ 2 ዴስክቶፕ ኮምፒውተሮች፣ ፍላሾች እና ፕሪንተሮች በኤግዚቢትነት ተይዘዋል።

ፖሊስ በማስረጃ የተጠናቀረውን የምርመራ መዝገብ ለዐቃቤ ሕግ በመላክ በግለሰቡ ላይ ክስ መመስረቱን አስታውቋል። ሀሰተኛ ሰነዶችን ማዘጋጀትና ማሰራጨት በሀገር ምጣኔ ሀብት እና ደህንነት ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተፅዕኖ የሚያሳድር ወንጀል መሆኑን የገለጸው ፖሊስ፣ ህብረተሰቡ መሰል ህገ-ወጥ ድርጊቶችን በመገንዘብ ለህግ አካላት አሳልፎ በመስጠት የበኩሉን ኃላፊነት እንዲወጣ ጥሪ አቅርቧል።

የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas

Read 4519 times