Saturday, 22 August 2026 10:43

የአርጀንቲና እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና ተጫዋቾች ተቀጡ

Written by 
Rate this item
(0 votes)
ፊፋ በዓለም ዋንጫው ፍጻሜ ወቅት በተፈጠሩ የሥነ-ምግባር ችግሮች ሳቢያ በአርጀንቲና እግር ኳስ ፌዴሬሽን ላይ የ321 ሺህ ዶላር ቅጣት የጣለ ሲሆን፣ ብሔራዊ ቡድኑም ቀጣይ ሁለት የሜዳው ጨዋታዎችን በግማሽ ተመልካች ብቻ እንዲጫወት አዟል።
በተጨማሪ በተጫዋቾችም ላይ ከባድ እገዳ የተጣለ ሲሆን፣ ሊሀንድሮ ፓሬዴስ የ10 ጨዋታዎች እገዳና የ90,000 ዶላር ቅጣት፣ ናኤል ሞሊና ደግሞ የ7 ጨዋታዎች እገዳና የ90,000 ዶላር ቅጣት ተላልፎባቸዋል።
በተመሳሳይ ቲያጎ አልማዳ እና ፓብሎ ማርቲን አንድ ጨዋታ ሲታገዱ፣ የአሰልጣኝ ቡድኑ አባል የሆኑት ሮቤርቶ አያላ ደግሞ የሦስት ጨዋታዎች እገዳ ተጥሎባቸዋል
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Read 627 times