Saturday, 22 August 2026 10:36

ምልዕቲ ኪሮስ አዲስ የግጥም መድበሏን ልታስመርቅ ነው

Written by 
Rate this item
(0 votes)
በኢትዮጵያ የኪነ-ጥበብ ዘርፍ በግጥም፣ በስክሪፕት ጽሑፍ፣ በሬዲዮ ፕሮዳክሽን እና በዘፈን ግጥም ደራሲነት የምትታወቀው ሁለገብ ባለሙያ ምልዕቲ ኪሮስ “ደምፀ ቃል” የተሰኘ አዲስ የግጥም መጽሐፏን ለአንባቢያን ልታበቃ ነው። ደራሲዋ ቀደም ሲል ለፍቅርአዲስ ነቃጥበብ፣ ለብስራት ሱራፌል፣ ለሄዋን ገብረወልድ፣ ለያሬድ ነጉ እና ለሌሎችም ታዋቂ ድምፃውያን የሙዚቃ ግጥሞችን በመጻፍ በሀገራችን የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ውስጥ ጉልህ አሻራ ማኖሯ ይታወቃል።
ቃልን ወደ ድምፅ፣ ስሜትን ወደ ግጥም፣ ግጥምን ደግሞ ወደ ትዝታ ያሸጋግራል የተባለለት የዚህ መጽሐፍ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 11:30 ጀምሮ በቅዱስ ያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት አሸናፊ ከበደ አዳራሽ ይካሄዳል። በዕለቱም የኪነ-ጥበብ አፍቃሪዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና አንባቢያን በተገኙበት መጽሐፉ በይፋ ተመርቆ ለንባብ እንደሚበቃ ታውቋል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Read 5233 times Last modified on Saturday, 22 August 2026 10:57