Wednesday, 19 August 2026 19:36

"ቡናዬ እስኪሰክን" ዝርጓ ጣፋጭ እንጎቻ!

Written by  ደረጀ በላይነህ
Rate this item
(1 Vote)

ይህቺን "ቡናዬ እስኪሰክን"የምትል መጽሐፍ አነበብኳት።በጣም ማራኪና ውብ ሆና አግኝታለሁ። መጽሐፏ ብዙ ነገሮቿ ዝርግ ሆነው ሲምቦሊክ ናቸው።ዘውጓ ግለታሪካዊ ልቦለድ ሆኖ ፣ነባሩና ዘመናዊው እውነታዊ ልቦለድ ውስጥ እንዲመደብ የሚያደርጉ ብዙ አላባውያን አሉ።

ጭብጡ የዘመን አሻራ ማኅተም ያረፈበት ጥልቅ ምልከታ ውስጥ አንድ የትራጀዲ ኪስ የተበጀለት፣ግን ደግሞ ሳቅ የተርከፈከፈበት በውበት ጸዳል ያጌጠና የተከፈፈ ነው።

ደራሲው ቤተማርያም ተሾመ ከተለያዩ ዘመናትና የታሪክ ጥጋጥግ የሰበሰባቸው በርካታ የጥበብ የፖለቲካና የማኅበራዊ ሕይወት ስልቶችን በፈረቃ የሚያጫውትበት ስልት ፈጥሯል።

Read 5025 times