አንድ ታዋቂ ሰዓሊ የሰራውን ስዕል ሰዎች በሚበዙበት አደባባይ ላይ አስቀመጠ። ከስዕሉም ስር "እባካችሁ የተበላሸ ቦታ ካየችሁ በኤክስ (X) ምልክት አድርጉበት" የሚል ፅሁፍ ለጠፈ። በማግስቱ ተመልሶ ሲመጣ ስዕሉ ሙሉ በሙሉ በኤክስ (X) ምልክት ተሸፍኖና ተበላሽቶ አገኘው።
በነገሩ በጣም አዝኖ ለጓደኛው ነገረው። ጓደኛውም፡ "በዚህ ተስፋ አትቁረጥ! ያንኑ ስዕል ድገምና በተመሳሳይ ቦታ አስቀምጠው። ነገር ግን በዚህኛው ስር 'የተበላሸ ቦታ ካለ በቀለሙና በብሩሹ አስተካክሉት' ብለህ ጻፍ" አለው። ሰዓሊውም እንደተባለው አደረገ። በማግስቱ ተመልሶ ሲመጣ ስዕሉ አንድም ቦታ ሳይነካ እንዳለ አገኘው!
ብዙ ሰዎች የሰውን ስህተት ለመንቀስና "ተበላሽቷል" ለማለት በጣም ፈጣኖች ናቸው። ነገር ግን ነገሩን ለማስተካከልና የተሻለ ነገር ለመስራት ሲባል፤ እውቀቱ፣ ጊዜው፣ ጉልበቱ ወይም ፍላጎቱ ያላቸው በጣም ጥቂቶች ናቸው።
ስለዚህ የሰዎች ነቀፌታ ተስፋ እንዲያስቆርጥህ አትፍቀድ፤ ከመንቀስ ባሻገር መፍትሔ የሚሰጡ ሰዎችን ብቻ አዳምጥ!
ኤርሚያስ በጋሻው ገሰሰ
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas
See less

