Wednesday, 05 August 2026 17:19

መከላከያ ሠራዊት ለመቄዶንያ ከ600 ሺህ ብር በላይ ድጋፍ አደረገ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት በየዓመቱ ሐምሌ 29 ቀን ከሚያከብረው የበጎ አድራጎት ቀን ጋር ተያይዞ፣ በመቄዶንያ ማዕከል ለሚገኙ አረጋውያን እና አቅመ ደካሞች ከ600,000 ብር በላይ የሚገመቱ የምግብ ፍጆታዎችን፣ የዊልቸር፣ የዋከር፣ የአልባሳት እና የፅዳት ቁሳቁሶችን ድጋፍ አድርጓል።
በመከላከያ ሚኒስቴር የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ዳይሬክተር ብርጋዴር ጄኔራል ሁሉሀገርሽ ድርስ አማካኝነት ለአረጋውያኑ ልዩ የምሳ ግብዥ የተደረገ ሲሆን፣ ሠራዊቱ የሀገርን ህልውና ከመጠበቅ ባሻገር ለወገኑ ቀዳሚ ደራሽ መሆኑን በማስመስከር ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጧል።
የማዕከሉ መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር ብንያም በለጠ ሠራዊቱ ሕይወቱን አሳልፎ ከመስጠት ባለፈ ወገኖቹን በፍቅር በመጎብኘቱ የላቀ ምስጋና አቅርበዋል፤ በማዕከሉ የሚገኙ አረጋውያንም ለሠራዊቱ ያላቸውን ፍቅር በምርቃት ገልጸዋል። በመጨረሻም የማዕከሉን የቀሩ የግንባታ ስራዎች በፍጥነት ለማጠናቀቅ ኅብረተሰቡ አሁንም ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀርቧል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Read 3538 times