Wednesday, 05 August 2026 16:52

የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የኤር ኢንዲያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)
ኤር ኢንዲያ በአቪዬሽን ዘርፍ ሰፋ ያለ ልምድ ያላቸውን ኢትዮጵያዊውን አቶ ተወልደ ገብረማሪያም የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና ማኔጂንግ ዳይሬክተር አድርጎ መሾሙን አስታውቋል። አቶ ተወልደ በአዲሱ ኃላፊነታቸው አየር መንገዱ ያጋጠሙትን የፋይናንስ እና የአሠራር ፈታኝ ሁኔታዎች የመምራት እና የመወጣት ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል።
በፍቃዳቸው ኃላፊነታቸውን የለቀቁትን የኤር ኢንዲያ የቀድሞ ኃላፊ ካምፕቤል ዊልሰንን በመተካት፣ አቶ ተወልደ ከመጪው መስከረም መጨረሻ ጀምሮ አዲሱን ሥራቸውን ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
Read 3561 times