Monday, 03 August 2026 00:00

የ«እናርጅና እናውጋ» ደራሲ አዲስ መጽሐፍ ለንባብ ሊያበቃ ነው

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በ“እናርጅና እናውጋ” መጽሐፉ የሚታወቀውና በ2016 ዓ.ም በክብር አዋርድ “የዓመቱ ምርጥ የግጥም መጽሐፍ” አሸናፊ የነበረው ጌራወርቅ ጥላዬ፣ “የቃል ሊቀ መኳስ” የተሰኘ አዲስ መጽሐፉን ከሕትመት አውጥቷል። 128 ገጾች ያሉትና በ300 ብር የጀርባ ዋጋ በ1,000 ኮፒ ታትሞ የወጣው ይህ መጽሐፍ፣ ለአንባቢያን ይፋ የሚሆንበት ትክክለኛ ቀን ግን ገና አልተወሰነም።

ደራሲው ከመጽሐፍት በተጨማሪ በሙዚቃ ግጥም ድርሰት የሚታወቅ ሲሆን፣ ለአብነትም በአፍሪማ አዋርድ እጩ የነበረውንና በዩጋንዳ በተካሄደው አይኮኒክ አዋርድ “የዓመቱ ምርጥ ዘፈን” ተብሎ የተሸለመውን የሃሌሉያ ተ/ጻዲቅን “የልቤ ቁምነገር” የተሰኘ ተወዳጅ ዘፈን የደረሰው እሱ ነው። ጌራወርቅ ከዚህ ቀደም “ሙሉ አካል ትዝታ” በሚል ርዕስ ልቦለድ መጽሐፍ እንደሚያሳትም መናገሩም ይታወሳል።

Read 2501 times