ሩሲያ "አቫታር 001" የተሰኘ እና በልዩ የምህንድስና አወቃቀሩ የተነሳ "የማይሰጥም" መሆኑ የተነገረለትን አዲስ የባሕር ላይ ድሮን ይፋ አደረገች። በቮልጎግራድ በሀገር ውስጥ ክፍሎች የተመረተው ይህ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ፤ እስከ 30 ኪሎ ሜትር የርቀት መቆጣጠሪያ ክልል፣ የ8 ሠዓታት የባትሪ ቆይታ እና እስከ 500 ኪሎ ግራም የጭነት የመሸከም አቅም እንዳለው ተገልጿል።
የአኳ-ቮልጋ ማምረቻ ተቋም ሥራ አስኪያጅ ዲሚትሪ ኮዝሎቭ እንደገለጹት፣ ድሮኑ የባሕር ገጽታ ቅኝት፣ የባሕር ላይ ጥበቃ እና የቁሳቁስ ማጓጓዝን ጨምሮ በርካታ ወሳኝ ተግባራትን የማከናወን አቅም አለው። 90 በመቶ ያህሉ በሀገር ውስጥ ግብአቶች የተመረተው ይህ ፈጠራ በዓለም አቀፍ መድረክ ከፍተኛ መነቃቃትን እየፈጠረ ይገኛል።

