የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሀገር ውስጥ የበረራ መዳረሻዎቹን በማስፋት ከጋምቤላ ወደ ደምቢዶሎ እና ከደምቢዶሎ ወደ ጋምቤላ የሚደረግ ቋሚ የበረራ አገልግሎት ከነሐሴ 06 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ።
አየር መንገዱ የህብረተሰቡን የትራንስፖርት ፍላጎት ለማሟላትና የሀገር ውስጥ ትስስርን ለማጠናከር የሚያደርገው እንቅስቃሴ አካል የሆነው ይህ አዲስ መስመር፣ የሁለቱን አካባቢዎች የትራንስፖርት እንግልት በእጅጉ እንደሚቀርፍ ተገልጿል።
አየር መንገዱ እንደገለጸው፤ በጋምቤላና በደምቢዶሎ ከተሞች መካከል የሚጀመረው ይህ አዲስ የበረራ መስመር በሁለቱ አካባቢዎች መካከል ያለውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል። ተቋሙ የሀገር ውስጥ የበረራ መዳረሻዎቹን አቅም በየጊዜው በማሳደግ የዜጎችን የእንቅስቃሴ ፍላጎት ለማሟላት በትጋት እንደሚሰራ አረጋግጧል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…

