Saturday, 11 July 2026 18:48

ከሩሲያ የኒውክሌር ተቋም በላቀ ውጤት የተመረቀው ወጣቱ ኢትዮጵያዊ ሳይንቲስት

Written by 
Rate this item
(0 votes)
በሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ የኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ ትምህርቱን የዩኒቨርሲቲው አንደኛ በመሆን ያጠናቀቀው ባለ ብሩህ አእምሮው ወጣት አማን ዘውዱ፣ በዓለም አቀፍ የዕውቀት መድረክ ላይ የኢትዮጵያን ስም በኩራት አስጠርቷል።
ይህ የማይበገር ጥንካሬ ባለቤት የሆነው ወጣት፣ ከ5 ዓመታት በፊት ባሳየው ድንቅ የትምህርት አፈፃፀም ምክንያት በሩሲያ ሀገር በሚገኘውና በዓለም ታዋቂ በሆነው ብሔራዊ የምርምር ኒውክሌር ዩኒቨርሲቲ (MEPhI) በኒውክሌር ሳይንስ ዘርፍ የነፃ ትምህርት ዕድል አግኝቶ ወደዚያው ማምራቱ ተጠቁሟል።
በሩሲያ ቆይታው ለዓመታት በትጋትና በጥንካሬ ሲማር የቆየው ወጣቱ ምሁር አማን፣ ዛሬ ላይ ትምህርቱን በከፍተኛ ውጤት አጠናቆ ለምርቃት በመብቃት የዚህ ታላቅ ድል ባለቤት መሆን ችሏል። ገና ከልጅነቱ ጀምሮ በትጋቱና በፈጣን አእምሮው የሚታወቀው አማን ዘውዱ፣ በኒውክሌር ቴክኖሎጂ ዘርፍ የቀሰመው እውቀት ለሀገሩ ለኢትዮጵያ አዲስ ተስፋና ትልቅ አቅም እንደሚሆን ይታመናል፡፡
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Read 10720 times Last modified on Saturday, 11 July 2026 18:51