Saturday, 23 May 2026 18:10

አሜሪካ ከሌሎች ሀገራት ምን መማር አለባት?

Written by 
Rate this item
(0 votes)
በርካታ ሀገራት ቢሊየነሮች በገንዘባቸው ምርጫን እንዳይቆጣጠሩ ለማድረግ ህጎቻቸውን አጥብቀዋል። ለምሳሌ ፈረንሳይ የድርጅቶችን የፖለቲካ ልገሳ ሙሉ በሙሉ ስታግድ፣ ብራዚልም ከከፍተኛ የሙስና ቅሌቶች በኋላ ይህንኑ ውሳኔ አስተላልፋለች። ካናዳ በግለሰቦች የፖለቲካ ልገሳ ላይ ጥብቅ ገደብ ጥላለች። ቤልጂየምና እስራኤል ደግሞ የሜጋ-ለጋሾችን ተፅዕኖ ለመቀነስ የልገሳ ጣሪያ በመጣልና ለመንግስት የፖለቲካ ፓርቲዎች ህዝባዊ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ስርአቱን ይቆጣጠራሉ። ጃፓን ከኩባንያዎች እና ጥቅም አስከባሪ ቡድኖች የሚመጣን የፖለቲካ ልገሳ ስትገድብ፣ ኒውዚላንድ ደግሞ የውጭ ተፅዕኖን ለመግታት ከውጭ ሀገር የሚመጡ የፖለቲካ ልገሳዎችን አግግዳለች።
እነዚህ ሁሉ ሀገራት ሀብታሞች የመምረጥ መብት የላቸውም እያሉ አይደለም፤ ይልቁንም «ዲሞክራሲ በገንዘብ የሚገዛ ሸቀጥ መሆን የለበትም» እያሉ ነው። በአንፃሩ በአሜሪካ የፖለቲካ ስርአት ውስጥ ቢሊየነሮች በሱፐር ፓኮች፣ ድብቅ-ገንዘብ በሚያንቀሳቅሱ ቡድኖችና በተለያዩ መንገዶች እጅግ ግዙፍ መጠን ያለው ገንዘብ ማፍሰስ ይችላሉ። ደጋፊዎቹ ይህንን አሰራር "የሃሳብ ነፃነት" ሲሉት፣ ተቺዎች ግን "ህጋዊ የተደረገ ኢ-ፍትሃዊነት" ሲሉ ይጠሩታል። በመሆኑም ጥያቄው ቀላል ነው፦ ሌሎች ዲሞክራሲያዊ ሀገራት ቢሊየነሮች በምርጫ ላይ ያላቸውን ተፅዕኖ መገደብ ከቻሉ፣ አሜሪካስ ተመሳሳይ እርምጃ መውሰድ የለባትም?
Read 10358 times