፩) ሎሚ የጉሮሮን ኢንፌክሽን ከሚከላከሉ ፍራፍሬዎች አንዱ ሲሆን የፀረ ባክቴሪያ ሀይል ስላለው በሻይ መልክ መጠጣት ከፍተኛ ጥቅም ይሠጣል።
፪) የሎሚ ጭማቂ የምግብ አለመፈጨትንና የሆድ ድርቀትን ይከላከላል።
፫) በምግብ ውስጥ ትንሽ ጠብታ ሎሚ ጨምሮ መጠቀም ደምን ያጣራል።
፬) ጥሩ የዕቃ ማፅጃ በመሆንም ያገለግላል።
፭) የሎሚ ጭማቂ በብርድ፣ በሳልና በትኩሳት ለሚሰቃዩ ሰዎች መድሀኒት ነው። እንዲሁም ትኩሳት በሚኖር ወቅት ቶሎ ቶሎ እንዲያልበን በማድረግ ያስታግስልናል።
፮) የጥርስ ህመም በሚያጋጥምበት ጊዜ የሎሚ ጭማቂ በህመሙ ቦታ ላይ በማድረግ እንደ ማስታገሻነት መጠቀም ይቻላል።
፯) በሎሚ ጭማቂ ድድን ማሸት ከድድ መድማት ችግርና ከመጥፎ የአፍ ጠረን ይታደጋል።
፰) ከውሀ ጋር የተቀላቀለ የሎሚ ጭማቂ መጠጣት ለኩላሊት ጠጠር እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው።
፱) የሎሚ ጭማቂ በተቃጠለው የሰውነታችን ቁስል ላይ በማድረግ ጠባሳ እንዳይኖር ለማድረግ ያስችላል።
፲) የሎሚ ጭማቂ ውስጣዊ መድማትን ይከላከላል። ምክንያቱ ሎሚ ፀረ ጀርምና ፀረ ባክቴሪያ ባህሪ ስላለው ነው። ስለሆነም የአፍንጫ መድማትን ለመከላከል በሎሚ ጭማቂ የተነከረ ጥጥ በአፍንጫ ቀዳዳ ውስጥ ከተው ለትንሽ ደቂቃዎች ማቆየት ይመከራል።
፲፩) ሎሚ ደምን የማጣራት አቅም ስላለው እንደ ወባና አተት ያሉ በሽታዎችን ይከላከላል።
፲፪) ሎሚ የፀረ ጀርምና ፀረ ባክቴሪያ ባህሪ ስላለው እርጅናን፣ የቆዳ መሸብሸብና ቆዳ ላይ ያሉ ትንንሽ ጥቁር ነጠብጣቦችን ያስወግዳል።
፲፫) የፀሀይ ጨረርን ለመከላከል የሎሚ ጭማቂ ፊትን መቀባት ጠቃሚ ነው።
፲፬) የሎሚ ጭማቂ ከማርና ውሀ ጋር በመቀላቀል መጠጣት ጥርት ያለ የፊት ቆዳ እንዲኖረን ያደርጋል።
፲፭) የሎሚ ጭማቂ የሰውነት ክብደትን ለመቀነስ ይረዳል።
፲፮) ሎሚ በቫይታሚን ሲ የበለፀገ ስለሆነ የአስምና የመተንፈሻ አካላት ችግር ላለባቸው ሰዎች በጣም ጠቃሚ ነው።
፲፯) ሎሚ በውስጡ ፖታሲየም ስላለው ጭማቂውን መጠጣት የልብ ህመምን ለማስታገስ ይጠቅማል።
፲፰) ከፍተኛ የደም ግፊትን፣ ማዞርና ማቅለሽለሽን በመቆጣጠር አእምሮና ሰውነታችን ዘና እንዲል ያደርጋል።
፲፱) የራስ ቆዳ አናትን የሎሚ ጭማቂ መቀባት እንደ ፎረፎር፣ የፀጉር መነቃቀልና ከራስ ቅል ጋር የተያያዙ ችግሮችን ለመከላከል ይጠቅማል። እንዲሁም ፀጉራችን አንጸባራቂ እንዲሆን ያደርጋል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
.

