Thursday, 30 October 2025 11:21

የትግራዩ ጦርነት 10. 8 ቢ. ዶላር ማህበራዊ ውድመት አድርሷል - ኮሚሽኑ

Written by 
Rate this item
(0 votes)
የትግራይ የዘር ማጥፋት ኮሚሽን፣ የትግራዩ ጦርነት ያስከተለው ማኅበራዊ ውድመትና ኪሳራ 10 ነጥብ 8 ቢሊዮን ዶላር እንደሚገመት በጥናት ማረጋገጡን አስታውቋል።
ኮሚሽኑ ጦርነቱ ከፍተኛውን ውድመት ያደረሰው በትምህርት ዘርፉ ላይ መኾኑን ይጠቅሳል።
ሪፖርቱ፣ የኤርትራ ሠራዊት በትምህርት፣ በጤና ሥርዓቶች፣ በቅርሶች፣ በታሪካዊ ሕንጻዎች፣ በእደ ጥበባትና በታሪካዊ ቁሳቁሶች ላይ ከ38 እስከ 56 በመቶ የሚደርስ ጉዳት አድርሷል ብሏል።
ባንጻሩ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ በቁጠባና ብድር ተቋማት፣ በኅብረት ሥራ ማኅበራት፣ በአነስተኛ ማኅበራዊ አገልግሎት ሠጪ ተቋማት ላይ የ27 ነጥብ 2 በመቶ ጉዳት ማድረሱን ኮሚሽኑ ገልጧል።
[ዋዜማ]
Read 1157 times