በኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለሜጋ ኘሮጀክቶች በተሰጠው ትኩረት ከታላቁ ህዳሴ ግድብ በተጨማሪ 14 መካከለኛና ከፍተኛ ግድቦች በ2ዐዐ ቢሊዮን ብር ወጪ እየተሰሩ መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታውቀዋል፡፡
ጠ/ ሚኒስትሩ ትላንት ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎችና አስተያየቶች በሰጡት ማብራሪያ፤ በሀገሪቱ ሁሉም አካባቢዎች በ1 ነጥብ 5 ትሪሊየን ብር ወጪ 346 የመንገድ ኘሮጀክቶች በፌደራል መንግስት ግንባታቸው እየተከናወነ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የኤሌክትሪክ ኃይል በኢትዮጵያ ሁሉም አካባቢ ተደራሽ ለማድረግ በተሰራው ሥራም 11ዐ ቢሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት የመብራት ማስፋፊያ ኘሮጀክት ሥራ መጀመሩን ጠቁመዋል፡፡
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…

