Wednesday, 01 October 2025 12:46

'ቦን -02' -የተሰበሩ አጥንቶችን በ3 ደቂቃ የሚገጥም ግኝት

Written by 
Rate this item
(0 votes)
የቻይና ተመራማሪዎች ከአጥንት ስብራት ለማገገም ወራት ይፈጅ የነበረውን ሂደት የሚቀይርና በ3 ደቂቃዎች ውስጥ የተሰበረ አጥንትን የሚገጥም ግኝት ይፋ ማድረጋቸው ተዘግቧል፡፡
'ቦን -02' የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ ግኝት፤ ተጨማሪ ቀዶ ጥገና ሳያስፈልግ የተሰበሩ አጥንቶችን የሚገጥም ነው፡፡
በሃንግዙ ሰር ሩን ሾው ሆስፒታል የአጥንት ሕክምና ባለሙያ የሆኑት ሊን ዢያንፌንግ እንደገለጹት፤ ሕክምናው በመርፌ መልክ የሚሰጥና የተሰበሩ አጥንቶችን በደቂቃዎች ውስጥ አንድ ላይ እንዲጣበቁ የሚያደርግ ነው።
'ቦን 02' በሰው አካል ውስጥ ከገባ በኋላ በተፈጥሮ መንገድ እንዲዋሃድ ተደርጎ መሰራቱም ተመላክቷል።
ከዚህ በፊት ይደረግ እንደነበረው ማጣበቂያውን ለማስወገድ ሁለተኛ ቀዶ ጥገና ባለማስፈለጉም የኢንፌክሽን አደጋን ይቀንሳል ነው የተባለው።
በ'ዠይጂያንግ' ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች በተሰራው በዚህ ግኝትም፣ ከ150 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ሕክምና በተሳካ ሁኔታ መካሄዱን ኦዲቲ ሴንትራልን ጠቅሶ ኢቢሲ መዝናኛ አስነብቧል፡፡
Read 371 times