ኬንያ ዜጎቿ ወደ ሩሲያ በግዳጅ እየተወሰዱ በዩክሬን ጦርነት ውስጥ እንዲሳተፉ ይደረጋሉ መባሉን ተከትሎ ምርመራ መጀመሯ ተሰምቷል፡፡
ምርመራው ኬንያዊው አትሌት ኢቫንስ ኪቤት፣ የሩሲያ ሰራዊትን እንድቀላቀል ተታልዬ ነበር ማለቱን ተከትሎ የመጣ ነው ተብሏል፡፡
የኬንያ ባለስልጣናት እውነታውን እንዲሁም የተጎጂዎችን ደህንነት ለማረጋገጥ፣ ከሩሲያና ከዩክሬን ባለስልጣናት ጋር እየተነጋገሩ መሆኑ ተዘግቧል፡፡
ይህ ሁኔታ በግጭት ቀጠና ውስጥ የውጭ ሀገር ዜጎችን ኢላማ ያደረገ ቅጥር ላይ ያለውን ስጋት አጉልቶ እንደሚያሳይ ተጠቁሟል፡፡
ኬንያ አንዳንድ ዜጎቿ ወደ ሩሲያ ጦር ሰራዊት በግዳጅ እንደገቡና አሁን በዩክሬን የጦር ምርኮኞች ሆነው እንደሚገኙ የሚገልጽ ዘገባ ከወጣ በኋላ ነው የማጣራት ምርመራውን የከፈተችው፡፡
ቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…

