Wednesday, 03 September 2025 18:25

ሆስፒታሉ የዓለም ጤና ድርጅትን ዕውቅና ማግኘቱን ገለጸ

Written by 
Rate this item
(0 votes)
"ላንድማርክ ኑሮውም ጉዞውም ከህብረተሰቡ ጋር ነው"
ላንድማርክ አጠቃላይ ሆስፒታል "የአዲስ ዓመት ስጦታ" በሚል ከነሃሴ 26 ቀን ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 1 ቀን 2017 የሚዘልቅ የነጻ የጤና ምርመራ መርሃ ግብር እያካሄደ መሆኑ ተገለጸ፡፡
የሆስፒታሉ አመራሮች ዛሬ ጠዋት ረፋዱ ላይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ በእነዚህ ቀናት ለ300 ያህል ሰዎች ነጻ የጤና ምርመራ እንደሚሰጥ አስታውቀዋል፡፡ በዚህ መርሃ ግብርም የደም ግፊት፣ የስኳር፣ የጡት ካንሰር፣ የኤችአይቪና የአባላዘር በሽታዎች ነጻ ምርመራ የሚሰጥ ሲሆን፤ ወጪው በገንዘብ ሲሰላ ሩብ ሚሊየን ብር እንደሚደርስ አመራሮቹ ጠቁመዋል፡፡
በሌላ በኩል፤ ላንድማርክ አጠቃላይ ሆስፒታል የዓለም ጤና ድርጅት "የታካሚ ደህንነትና ወገንተኝነት" መስፈርቶችን በማሟላት ዕውቅና እንደተሰጠው አመራሮቹ አስታውቀዋል፡፡
የሆስፒታሉ ዋና ሥራ አስኪያጅ ፕ/ር ከበደ ኦሊ በሰጡት ማብራሪያ፤ "ላንድማርክ በዓለም ጤና ድርጅት መስፈርት በአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ብቸኛ ሆስፒታል ነው" ብለዋል፡፡
"ላንድማርክ ኑሮውም ጉዞውም ከህብረተሰቡ ጋር ነው" ያሉት ዋና ሥራ አስኪያጁ፤ የሆስፒታሉ የማስፋፊያ ግንባታ የማጠናቀቂያ ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ በቅርቡም ተጠናቆ አገልግሎት እንደሚጀምር ተነግሯል፡፡
ላንድማርክ አጠቃላይ ሆስፒታል ላለፉት 17 ዓመታት የህክምና አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ የግል ተቋም መሆኑ ይታወቃል፡፡
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Read 579 times