በኢትዮጵያ የሴቶች የመሬት ባለቤትነት ሽፋን 60 በመቶ መድረሱ ተገለጸ፡፡
የሴቶችን የመሬት ባለቤትነት ለማረጋገጥ ከግብርና ሚኒስቴርና ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በቅንጅት እየተሠራ እንደሆነ የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ ተናግረዋል።
ሚኒስትሯ በግብርናው ዘርፍ የሴቶችን ተጠቃሚነት የሚያሳድግ ፕሮግራም በአዲሱ ዓመት ይፋ እንደሚደረግም አስታውቀዋል።
በጋምቤላ ክልል ሙከራው ተጀምሮ ወደ ሌሎች ክልሎች የሚስፋፋው ይህ ሮግራም፤ የአምስት ዓመት ቆይታ ይኖረዋል፡፡
ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ 90 በመቶ የሚሆኑ የገጠር ሴቶች ከቀበሌ ጀምሮ ባሉ አደረጃጀቶች የራሳቸውን ሃብት እያፈሩ እንደሆነም ለሀገር ውስጥ ሚዲያ መግለጻቸውን ስፑትኒክ ዘግቧል፡፡
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…


