የ2017 ዓ.ም አምስቱ የጳጉሜ ቀናት ስያሜዎችንና የአከባበር ሁኔታን አስመልክቶ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
ሚኒስትሩ በመግለጫቸው፤ የጳጉሜ ቀናት መታሰብ ዜጎች ለአዲስ ዓመት የግላቸውን መሻት እውን ለማድረግ ሲያቅዱ የመንግስት መነሳሳቶች፣ እቅድና አቅጣጫዎችን በእቅዳቸው ውስጥ እንዲያካትቱ ግንዛቤ ለመፍጠር ታስቦ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የተገባደደው ዓመት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ማጠናቀቅ፣ የኮሪደር ልማት፣ የኢንደስትሪዎች አምራችንትን ማጠናከር፣ የአረንጓዴ አሻራና ሌሎችም ታላላቅ ሥራዎች የተከናወኑበት መሆኑን ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል፡፡
በመጪው አዲስ ዓመትም እነዚህን እመርታዎች አጠናክሮ ለማስቀጠል ዋዜማ የሆኑትን የጳጉሜ አምስት ቀናት በተለያዩ ስያሜዎች ለማክበር ዝግጅት መጠናቀቁን አመላክተዋል፡፡ አምስቱ የጳጉሜ ቀናት የተሰጣቸው ስያሜና መሪ ቃል እነሆ፡-
ጳጉሜ 1- "የፅናት ቀን"
መሪ ቃሉ -"ፅኑ መሰረት ብርቱ ሀገር"
ጳጉሜ 2 - "የኅብር ቀን"
መሪ ቃሉ - “ብዝሃነት የኢትዮጵያ ጌጥ”
ጳጉሜ 3 - "የእምርታ ቀን"
መሪ ቃሉ - "እምርታ ለዘላቂ ከፍታ"
ጳጉሜ 4 - "የማንሰራራት ቀን"
መሪ ቃሉ - "ዘላቂ ልማት ለሀገራዊ ማንሰራራት"
ጳጉሜ 5 - "የነገው ቀን"
መሪ ቃሉ - "ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ማድረግ"


