የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ የሶማሌላንድን የዕውቅና ጥያቄ ጉዳይ አስተዳደራቸው እየመረመረው እንደሆነ ተናገሩ።
ከሶማሊያ በመነጠል ነጻነቷን ያወጀችው ሶማሌላንድ ዓለማቀፍ ዕውቅና ለማግኘት ያቀረበችውን ጥያቄ አስተዳደራቸው እያጤነው እንደሚገኝ ትራምፕ ፍንጭ ሰጥተዋል።
የሶማሌላንድ የዕውቅና ጉዳይ የተነሳው ትላንት አርብ፣ በአሜሪካ አሸማጋይነት አርሜኒያና አዘርባጃን የሰላም ሥምምነት በተፈራረሙበት ወቅት ነበር፡፡
“በአሁኑ ወቅት ጉዳዩን እየመረመርነው እንገኛለን” ያሉት ትራምፕ፤ ጉዳዩ “ውስብስብ” እንደሆነ አልሸሸጉም፡፡
በቅርቡ ሶማሌላንድ ከአሜሪካ የአገርነት ዕውቅና የሚሰጣት ከሆነ፣ በልዋጩ የጦር ሰፈርና ማዕድናትን እንደምትሰጥ ቃል መግባቷ ይታወቃል፡፡
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…

