Wednesday, 06 August 2025 15:25

ትራምፕ ለህንድ የ24 ሰዓታት ገደብ ሰጥተዋታል

Written by 
Rate this item
(0 votes)
• "ከፍተኛ" ታሪፍ እጥላለሁ ብለዋል
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በ24 ሰዓታት ውስጥ "ከፍተኛ" ያሉትን ታሪፍ በህንድ ላይ እንደሚጥሉ አስታወቁ።
የደልሂ ፖለቲከኞች ከሩሲያ የነዳጅ ምርት መግዛታቸው ያባሳጫቸው ትራምፕ፣ ህንድ ታማኝ የንግድ አጋር አልሆነችልንም በሚልም ወቅሰዋል።
ህንድ ኢኮኖሚዋን ለመታደግና ብሄራዊ ጥቅምን ታሳቢ በማድረግ፣ ከሞስኮ አሁንም ነዳጅ ማስገባት መቀጠል እንደምትችል ሊታወቅልኝ ይገባል ብላለች።
አውሮፓ ህብረትና አሜሪካ አመክንዮ የሌለው ክስ አቅርበውብኛል በሚልም ኒው ደልሂ ትከራከራለች።
"ባለከፍተኛ ታሪፍ አገር " በሚል ትራምፕ ህንድን ሲጠሩ፣ በ24 ሰዓታት ውስጥ ከ25 በመቶው በተጨማሪ ከፍተኛ የተባለ ታሪፍ ሊጥሉባት እንደሆነ ይጠቁማል።
“ብዙ ቢዝነስ ከእኛ ጋር ይሰራሉ። ነገር ግን አንፈልጋቸውም።" በሚልም እንዲሁ አጣጥለዋል ትራምፕ።
የሩሲያን ነዳጅ በመግዛት የሞስኮን የጦር መሳሪያ ካዝና እየሞላ ነው፤ ሲሉም የጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲን መንግስት መውቀሳቸውን ኤንቢሲ አስነብቧል፡፡
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Read 453 times