Saturday, 03 September 2011 12:14

ታሪክና ራስን የመውቀስ ጥበብ

Written by  ዓለማየሁ ገላጋይ alemayehugelagay@yahoo.com
Rate this item
(0 votes)

ማጥለያ፣ ማንጠሪያ፣ ማንፈሻ፣ ማበጠሪያ፣ ማንጠርጠሪያ፣     ማንገዋለያ... የታሪክ     ሙያተኞቻችን መሣሪያዎች ናቸው፡፡ ታሪክን ከተረትና ከአፈታሪክ የሚያጠሩበት አይደለም፡፡ እንዲያማ ቢሆን ደግ ነበር፡፡ ታሪካችን እንደጓጓላ፣ እንደትቢያ፣ እንደእብቅ፣ እንደ እንክርዳድና አሸክት አድርጐ የሚቆጥረው የራሱን የአንድ ወገን ገታዎችን ነው፡፡ ምሳሌ እንመስል፡፡ስለ አምስቱ አመት የጠላት ጊዜ ታሪክ ሲፃፍና ሲነገር አዝማሪ እንዳቆመ የመሸታ ቤት ፏላይ መስማት የምንፈልገው ሙገሳ-ሙገሳውን ብቻ ነው፡፡ ከጀግንነታችን፣ ከአይበገሬነታችንና እኒህን ከመሳሰሉት ውጭ ቅይጥ የክህደት ሆነ የፈሪነት እውነታዎች ተከድነው በሳዮች ናቸው፡፡

ጀግናው ደጃዝማች ባልቻ አባነፍሶ በ80 ዓመታቸው በአርበኝነት ተሰማርተው፣ በጠላት እጅ መሞታቸው የአደባባይ ቀረርቷችን ነው፡፡ ነገር ግን ለቄሳሩ መንግሥት ገብተው፣ የባንዳ ወታደር በሥራቸው አደራጅተው፣ አርበኞችን ሲወጉ የነበሩት ሌላው መኳንንታችን ራስ ኃይሉ ተክለኃይማኖት ታሪካቸው እንደ ጭንግፍ ለዘላለሙ ጓሮ የተቀበረ እንዲሆን ፈርደናል፡፡ ድርጊቱ በይቅርታ የተመለሰ፣ ሰውን ካለማውቀስ ሥነ-ምግባር ጋር ብቻ የሚያያዝ አይደለም፡፡ ለራሳችን የምናበጀው ሐሰተኛ ምሥል ላይ ሳንካ ስለሚሆን እንጂ፡፡ በሚያኮሩት ባለታሪኮቻችን የምንጀነነውን ያህል በሚያሳፍሩት የመኮስመን እዳ ስላለብንም ይህንን መጥፎ ስሜት ሽሽት የባንዳነት ትርኪ-ሚርኪዎችን ከፊታችን አንስተን የት እንደወሸቅናቸው እንኳን ልብ ማለት አንሻም፡
..ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያዊነቱን ነብር ዥንጉርጉርነቱን.. እንዲህ ያሉ ቅዠት መሰል አጠቃሎዎች ወደ ግብዝነት ንፍ ሳይመሩን አልቀሩም፡፡ ..ነብር ነብርነቱን ኢትዮጵያዊም ዥንጉርጉርነቱን.. ቢባል ምንኛ ከእውነታ ጋር በገጠመ ነበር፡፡ ከታሪክ ማሳ ላይ ባልቻ አባነፍሶን አድቀን ራስ ኃይሉ ተክለኃይማኖትን ለመንቀል አራሚና ኮትኳች ሆነንም ባልቀረን ነበር፡፡
ታሪክ የራስ አበበ አረጋይ፣ የበላይ ዘለቀ፣ የደጃዝማች ገረሱ ዱኪ... ብቻ መፏለያ አይደለም፡፡ የኢጣሊያ መንግሥት ደሞዝ የቆረጠላቸው ረዳቶቹ እነ ራስ ስዩም መንገሻ፣ እነ ራስ ጌታቸው አባተ፣ እነ ሼህ ሆጆሌ፣ እነ አቡነ አብርሃም፣ እነ ሱልጣን መሐመድ ሃንፋሪ፣ እነ አቡነ ይስሐቅ፣ እነ ሱልጣን አባ ጆቢር አብዱላሂ... ሁሉ አሉበት፡፡
ለእኛ ታሪክ እውነት ሳይሆን የምንኳኳልበት የውበት ሳሎናችን ይመስለናል፡፡ በድርጊት የተበላሸውን ገታ በመጥረብና በመላግ ለማስተካከል ከንቱ ደካሚዎች ሆነናል፡፡ ሙገሳችንን ፍለጋ በግብዝነት የማንቆፍረው ከርሰ-ታሪክ፣ የማናስሰው ዘመን፣ የማናራግፈው የእምት ትቢያ፣ የማናንኳኳው ተረትና አፈታሪክ... የለም፡፡ ሆሜር ..ኦዲሴ.. በተሰኘ ጥንታዊ ሥራው ውስጥ “At earth’s two verges in sunset lands and lands of the rising sun” እንዳለን የምናስታውሰው አሁን ካለንበት ..የአየር ሁኔታ.. ጋር ያልተገናዘበ ሙቀት እየተሰማን ነው፡፡ ሔሮዱትስም |ኢትዮጵያውያን እስረኞቻቸውን ሁለ በወርቅ ሰንሰለት የሚያስሩበት ወህኒ አላቸው.. ስላለ ወደ ዋናው ቤታችን ..እንግዶች.. የመጋበዝ ወፈፌነት ይዳዳናል፡፡ ሔሮዱትስ ግን ስለ እኛ ይሄን ብቻ አልተናገረም፡፡ ልናነበው የማንፈልገውንም ፏል፡፡
..እነዚህ የጋራማንቴ ሰዎች በዋሻ ውስጥ የሚኖሩትን ኢትዮጵያውያን ለማደን በአራት ፈረስ ሠረገላ ይሄዳሉ (የምንታደነው ዝንጀሮ ነበር እንዴ?) በዋሻ ውስጥ የሚኖሩት የኢትዮጵያ ሰዎች ከሰማነው ሰው ሁሉ የበለጡ ሩዋጮች ናቸው፡፡ እነርሱም እባብ እንሽላሊትና እነዚህን የመሰሉ ተንፏቃቂ ነገሮች ይበላሉ፡፡ ይህን ይመስላል የሚባልም ቋንቋ አይናገሩም፡፡ ነገር ግን እንደ ሌሊት ወፍ ይጮኻሉ፡፡..
V.O. Klyuchevsky  MhùR “Aphorisms and Thoughts on History” በተሰኘ መሐፋቸው ላይ እንዲህ ይላሉ “History is power when it is good to people. They forget about it and ascribe their prosperity to themselves; when it becomes bad for them, they begin to feel its necessity and value its boons”  (..ታሪክ ሐይል ነው፡፡ ለህዝቦች ጥሩ እስከሆነላቸው ድረስ ስለምንነቱ በመዘንጋት ፍስሐነቱን ብቻ ለራሳቸው ለማስረዳት ይሞክራሉ፡፡ እንደፈለጉት ባልሆነ መንገድ ሲመጣና መጥፎ ሲሆንባቸው ግን አስፈላጊ አለመሆኑና አለመጥቀሙ ይሰማቸው ይጀምራል..) በሐበሾች ምድር የታሪክ ዕጣ ፈንታ ይሄ ነው፡፡ እንደ ጥጥ እርሻ ..ቡሉኮ.. እስከተሸመነበት ጊዜ ድረስ ነው የሚያስፈልገው፡፡ አራቋች፣ ገፋፊ፣ ገላቢ... ከመሰለን ወዲያውኑ አላስፈላጊነቱና ፋይዳቢስነቱ ይሰማናል፡፡
ጭ-ው ባለ የታሪክ በረሃ ላይ የምንሸላለምበትን ጥሪት ፍለጋ እጅግ ባዝነናል፡፡ ከባሪያ ፍንገላ ጋር ተነካክቶ ያነወረንን ጥቅል ታሪክ እየቆነፀልን፣ የራስ ምስላችንን ማጋጋጪያ ፈርጥ ፈልፍለን አውጥተናል፡፡ በ6ኛ ክ/ዘመን (ቅድመ ክርስቶስ) ታናሿ እሲያ ማዕከላዊ ቱርክ ውስጥ በባርነት ይኖር የነበረው ኤዞፕ፤ ከሁሉም በላይ ኢትዮጵያዊntÜ ጐልቶ እንዲታይ ብዙ ጥረናል፡፡ ደፋጣ አፍንጫውን፣ ከባዳ ከንፈሩንና ጥቁር መሆኑን ያዩት ግሪኮች ..ኤዞፕ.. ብለው እንደጠሩት ይታወቃል፡፡ ኤዞፕ ሲሉ ..ኢትዮጵ.. ማለታቸው እንደሆነ የቁስጥንጥንያው መነኩሴ ምሁር ከፕላንዮደስ መስክረዋልና ይሄንን እንደ ጭልፊት ሞጭልፈን ተመልሰናል፡፡ የኤዞፕ ባርነት ብቻ ሳይሆን ለሥራው እንኳ ደንታ ሰጥቶን ወደ ሥነ-ሁፋችን ለማካተት አልሞከርንም፡፡
..ባርነቱን እርሺው ትልቅነቱን አንሺው.. ካልናቸው ሰዎች መካከል ሩሲያዊው አሌክሳንደር ፑሽኪን አንዱ ነው፡፡ የፑሽኪን ቅድመ አያት አብርሃም ሃኒባል የአንድ ኢትዮጵያዊ መስፍን ልጅ እንደነበር ሩሲያውያኑም መስክረዋል፡፡ ቱርኮች ሃኒባልን ማርከው ከወሰዱት በኋላ ለሩሲያው ቄሳር ለቀዳማዊ ጴጥሮስ በስጦታ ሥም አበረከቱት፡፡ አብርሃም ሃኒባል ስመጥሩ የጦር መሪ እንደነበር ተመስክሮለታል፡፡ ..ፑሽኪን በቅድመ አያቱ ኩራት ይሰማው ስለነበር የታላቁ ጴጥሮስ የጡት ልጅ በሚል ርእስ አንድ መሐፍ ፏል.. ይላሉ፡፡ ፑሽኪንም እንደ ኤዞፕ ሁሉ ጥላው እንጂ እሱነቱ አልተፈለገም፡፡ ክህሎቱም እንዲተላለፍ አልተሞከረም፡፡ ሐውልቱ ጥላ ሥር አረፍ ከማለት ውጭ የተረፈን የለም፡፡
ታሪክ ቁንፀላችን ከታላላቆቹ ኤዞፕ እና ፑሽኪን አልፎ ለቤት ሰራተኝነት የተፈነገለች ባሪያ ዘንድ እስከ ማጀት ይዘልቃል፡፡ ማኅቡባ ትባላለች፤ በ1837 ዓ.ም ከኢትዮጵያ ተፈንግላ ካይሮ ላይ ለአንድ ልዩ ጀርመናዊ ባላባት ተሸጠች፡፡ ልዑሉ ኸርማን ፓክለር ሙስካ በማህቡባ ፍቅር ተነደፈ፡፡ ማህቡባን እንድናስስ ያደረገን ይሄው ነው፡፡ ልዑሉ ..የማህቡባን ፍቅር ልቋቋመው ባልቻልኩት ኃይሉ ከባርነቷ አውጥቶ እመቤቴ አደረጋት.. አለ፡፡ ማህቡባን ባንዲራችን እንድትሆን የፈቀድነው ከማጀት ተነስታ ወደ አልጋ በመውጣቷ ብቻ ነው፡፡
ከማጀት እስከ አደባባይ የዘለቀው ታሪክ - ሐሳባችን አይቶ እንዳላየ እየረገጠ ያለፋቸው ብዙ ሥራዎች አለ፡፡ ‘MY ABYSSINIAN JOURNEY” በሚል እንግሊዛዊው ጆን ቦይስ አንድ የጉዞ ማስታወሻ ፏል፡፡ በአፄ ምኒልክ ዘመን ከኬንያ ተነስቶ በጅቡቲ ወደ አዲስ አበባ የገባው ይሄ ተጓዥ፤ ስለ ኢትዮጵያውያን ባህርይና ሁኔታ የፃፈው ጥቂት እራሳችንን እንድንፈትሽ የሚያደርግ ይመስላል፡፡ በጥቅሉ የማጭበርበር ባህርይ እንዳለን ይጠቁማል፡፡ በዘመኑ የጭነት ከብት ተደራድረው የሚሸጡት ኢትዮጵያውያን ሁለት ነገር ተስፋ ያደርጋሉ ይላል፡፡ አንዱ ከብቱ ከገዢው አምልጦ የሚመለስበትን ሁኔታ ተስፋ ያደርጋሉ፡፡ ካልሆነም ያልሸጠ ሌላ ሰው ከብቱን እንደተሰረቀ በመናገር በአምባጓሮ ከገዢው መንጠቅ ነው፡፡ ስለዚህ ወደ አካባቢው ሹም ቀርቦ በሁነኛ ምስክር ፊት ተመዝግቦ ካልሆነ በቀር እንዳይገዛ የእንግሊዝ ቆንስል ሠራተኛ ይመክረዋል፡፡
ተጓዡ ቦይስ በማጭበርበር የተለከፈ ህዝብ ናችሁ የሚለን ሌላም ምሳሌ በመጥቀስ ነው፡፡ ብዙ ለማኞች በየመንገድ ተኮልኩለው እንደማያሳልፉ፣ ሁሉም እጃቸው የተቆረጠ መሆኑን ይገልፃል፡፡ የሰዎቹ በተመሳሳይ እጃቸው መቆረጡ ግራ አጋብቶት ሲያጣራ በሌብነት እጃቸውን ያጡ እንደሆኑ ይነገረዋል፡፡ የሌብነት እጅ አቆራረጡን ሥርዓት ተከታትሎ ይፈዋል፡፡
..አክባሪ፣ እንግዳ ተቀባይ፣ ኩሩ..... የሚሉ ታጥበው የተቀሸሩት ታሪክ ፀሐፊዎች አደናግዘውን እነዚህን ለመቀበል አልሞከርንም፡፡ ይሄንኑ የሌብነት ርእሰ ጉዳይ አእኖት ሰጥቶ የፃፈው ሌላው ጀርመናዊው ባሮን ሮማን ፕሮቼስካ ነው ‘ABYSSINIA THE POWDER BARREL” በተሰኘ መሐፉ ላይ እንዲህ ይለናል “The chief traits of the moral character of the Abyssinians are indolence, drunkenness, irresponsibility, a high degree of dissoluteness, perfidy, a thieving tendency. Superstition, stupidly - proud selfishness, great skill in deception, ingratitude, impudence in demanding gratuities, and a degree of mendacity worthy of becoming proverbial” (ሥንፍና፣ ጠጪነት፣ ግዴለሽነት፣ ከሚገመት በላይ ከንቱነት፣ ሸፍጠኝነት፣ የስርቆት ዝንባሌ፣ ምልኪ፣ በድድብና እራስን መካብ፣ የማጭበርበር ከፍተኛ ክህሎት፣ ውለታ ቢስነት፣ ዓይን አውጣ ጉርሻ ጠያቂነት፣ ለተረት የሚበቃ ዋሾነት ለአቢሲኒያ ምግባራዊነት ከፍተኛ አደጋ ናቸው፡፡)
ፕሮቼስካ ለጠላትነት በቀረበ መልኩ ገመናችንን ከየመሐፉ በመልቀም ትክክለኛነቱን ለማስረገጥ ይጥራል፡፡ እንደ ወዳጃችን የምንቆጥረው ጀምስ ብሩስ እንኳን “for the most part great liars” እንዳለን ያወኩት ከእሱ ነው፡፡ በአፄ ቴዎድሮስ ዘመን ጠንቅቀው ያውቁን የነበሩት አቡነ ሠላማ (ቄስ አንድሮስ) እንዲህ ብለዋችኋል ይለናል፡፡
“The Abyssinians are a people without desire for knowledge or love of learning, and incapable of comprehending that what you are trying to do is for their good. What they want is a share of your possessions, and nothing else?” (አቢሲኒያዎች ለእውቀት ወይም ለመማር ፍቅር ቁብ የሌላቸው ህዝቦች ናቸው፡፡ ለእራሳቸው ስትሉ የምታደርጉትን መልካም ነገር የሚያመዛዝኑበት ችሎታውም የላቸውም፡፡ እነሱ የሚፈልጉት ከፀጋችሁ መካፈልን ብቻ ነው ገ 14)ፕሮቼስካ ከጠቃቀሳቸው ማስረጃዎች ውስጥ ከንጉሶቻችን አፍ የተቀዱም አሉበት፡፡ አፄ ሚኒልክ በሌቦች ላይ የሚፈፀመውን የጭካኔ ፍርድ እንዲተው ሲጠየቁ ..ህዝቤን የማውቅ እኔ ነኝ ብለዋል.. ይላል፡፡ ..ህዝቤ ምን እንደሚፈልግም አውቃለሁ.. (I know my people and I know what my people needs) ፀሐፊው የእሱን ማጠቃለያ የሚያክለው እንዲህ በማለት ነው፡፡ ..አቢሲኒያዎች ለነፃነት ሆነ እራሳቸውን ለማስተዳደር እንዳልበቁ (ሚኒልክ) ጠንቅቀው ተረድተውታል፡፡ የሌላውን መብት ሊያከብሩ የሚችሉት በተእኖና በከባድ ቅጣት ብቻ ነው፡፡..እራስን አጥርቶ ለመመልከት ከወዳጅ ሽንገላ ይልቅ የጠላት ስድብ ግሩም መስታወት ነው (ያውም እንዲህ ስላለን ፕሮቼዝካን እንደ ጠላት ካየነው ማለት ነው) ያም ሆነ ይህ ታሪካችንና የታሪክ ሰዎቻችን እንዲህ ያሉ መዛግብትን ..ማግለል ይቁም.. ልንል ይገባልም፡፡ ..ምርጥ ምርጡን ለህፃናት.. እንጂ ለህዝብ አይረባንም፡፡

 

Read 2766 times Last modified on Saturday, 03 September 2011 12:18