Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 15 October 2011 11:11

ፕሬዚዳንት ግርማ በኑሮ ውድነት ምክንያት መንግስትን አልገሰፁም የዋጋ ንረቱ መንስኤ፤ የነዳጅ ዋጋ ነው?

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ነጋዴዎች ናቸው? ወይስ የመንግስት የብር ህትመት?
ፕሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ሰኞ እለት በፓርላማ ያደረጉት አመታዊ ንግግር፤ ያን ያህልም የዜጎችን ትኩረት የሚስብ አልነበረም። የንግግራቸው ቀዳሚ ርእሰ ጉዳይ፤ በአገራችን ከፍተኛ የኢኮኖሚ እድገት መመዝገቡን የሚያበስር ነው። አምና የአገራችን ኢኮኖሚ በ11.4 በመቶ እንዳደገ የገለፁት ፕ/ት ግርማ፤ እድገቱም የመንግስት ፖሊሲዎች ትክክለኛ እንደሆኑ አስመስክሯል ብለዋል። ለዚህም ሶስት ምክንያቶችን አቅርበዋል።

የመንግስት ፖሊሲዎችን ትክክለኛነት የሚያረጋግጥ ከፍተኛ እድገት!... መልካም ብስራት ነው። ታዲያ ለምን ብዙ ሰው ለፕሬዚዳንቱ ንግግር ትኩረት ሳይሰጥ ቀረ? “ከፍተኛ እድገት እንደሚመዘገብ ድሮም እናውቀዋለን” በማለት፤ የፕሬዚዳንቱን ንግግር በቸልታ የሚያዩ ሰዎች ካሉ፤ በጣም ተሳስተዋል። እድገቱ የእውነት ከሆነ፤ ነገሩን በቸልታ ከማለፍ ይልቅ ስኬትን እያከበሩ አብሮ መደሰት በተገባ ነበር - “እድገቱኮ በቁጥርና በመቶኛ ብቻ የሚገለፅ ሳይሆን፤ ኑሯችን ሲሻሻል እያየን ነው! “ በሚል ስሜት። 
ምን ያደርጋል? ኑሮ ሲሻሻል ማየት ከናፈቀን አመታት ተቆጠሩ። የብዙ ዜጎች ኑሮ ከአመት አመትና ከወር ወር በዋጋ ንረት እየተሸረሸረ ነው። ታዲያ፤ ኑሮ የተናጋባቸው ዜጎች፤ “በፕሬዚዳንቱ ጭምር ተደጋግሞ የሚነገርለት እድገት፤ ከኑሯችን ጋር ዝምድና የለውም” ብለው ትኩረት ቢነፍጉት ምን ይገርማል? ለነገሩ፤ ፓርላማውም ለፕሬዚዳንቱ ንግግር በቂ ትኩረት የሰጠ አይመስልም። በፕሬዚዳንቱ ንግግር ላይ ውይይት አልተካሄደም።
በእርግጥ፤ ከ547ቱ የፓርላማ አባላት መካከል፤ ከሁለቱ በስተቀር ሌሎቹ በሙሉ የኢህአዴግና የአጋር ደርጅት አባል ስለሆኑ፤ ውይይት መደረጉ ወይም አለመደረጉ ያን ያህልም ለውጥ አያመጣም ይባል ይሆናል። ያው፤ ገዢው ፓርቲና አጋሮቹ ፤”የፕሬዚዳንቱን ንግግር እንደግፋለን” የሚል የውሳኔ ሃሳብ በምስጋና ያቀርባሉ። በፓርላማው ውስጥ የሚገኘው ብቸኛ የተቃዋሚ ፓርቲ አባል፤ ... ምናልባት የፕሬዚዳንቱን ንግግር በመተቸትና ጉድለት እንዳለበት በመግለፅ ሌላ የውሳኔ ሃሳብ ያቀርብ ይሆናል። ከዚያስ?
በ99አ.ም የወጣው የፓርላማ ደንብ እንደሚገልፀው ከሆነ፤ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ የመንግስትን አቋም ካቀረቡ በኋላ፤ የውሳኔ ሃሳቦች ላይ ፓርላማው ድምፅ ሲሰጥ ነው ውይይቱ የሚጠናቀቀው። በተቃዋሚ ፓርቲ የሚቀርብ የውሳኔ ሃሳብ ካለ ውድቅ ይሆናል። በገዢ ፓርቲና በአጋሮቹ የሚቀርብ የውሳኔ ሃሳብ ደግሞ ይፀድቃል። አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ አባል ብቻ በሚገኝበት ፓርላማ ውስጥ ውይይት መካሄዱና አለመካሄዱ ምን ለውጥ ያመጣል የሚል ጥያቄ የሚነሳውም በዚህ ምክንያት ነው።
ነገር ግን፤ ቢያንስ ቢያንስ ለስነስርአትና ለወግ (ለፎርም) ያህል፤ በፓርላማው ደንብ ላይ በተዘረዘረው መንገድ ውይይት ቢካሄድ፤ ከፓርላማ አሰራር ጋር ለመለማመድ ይጠቅማል። አስቸኳይ ጉዳይ ሲያጋጥም ወይም በሌላ ጉዳይ (ለምሳሌ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለስራ ውጭ አገር በመሄዳቸው ምክንያት) ውይይቱ ለሌላ ጊዜ የሚተላለፍ ከሆነም፤ ይህንኑን በመግለፅ መወሰን ይቻላል - በደንቡ መሰረት። የፕሬዚዳንቱን ንግግር አዳምጦ መሸኘትና ስለውይይት ሳያነሱ ወደ ሌላ ስራ መሻገር ግን፤ ከፓርላማው ደንብ ጋር የማይጣጣም ስህተት ነው።
“ባይጣጣምስ ምን ይመጣል?” እንደምትሉ እገምታለሁ። ስህተቶችን ለመተቸት የተዘጋጀ ተፎካካሪ ፓርቲ ከሌለ፤ ገዢው “እንዳልሳሳት” ብሎ በጥንቃቄ የመስራት አቅሙ እየሞተ እንደሚሄድ አያጠራጥርም። የፓርቲዎች ጠንካራ ፉክክር አለመኖሩኮ፤ እዚህ ላይ ነው ጉዳቱ። ለካ፤ ስልጡን የፓርላማ አሰራርን መለማመድ የሚቻለውም፤ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ሲኖሩ ነው።
የሆነ ሆኖ፤ የፕሬዚዳንቱ ንግግር በዚያው እለት በፓርላማ ውይይት ሳይካሄድበት መቅረቱና በብዙ ዜጎች ዘንድ ትኩረት ሳይሰጠው መታለፉ ለየቅል ናቸው። አንደኛው ከአገሪቱ የፖለቲካ ሁኔታ ጋር የተያያዘ ነው - የፓርቲዎች ፉክክር አለመኖሩ። ሌላኛው ግን ከኑሮ ጋር የተሳሰረ ነው - በየአመቱ ኑሮ እየተሸረሸረባቸው ዝቅ ዝቅ የሚሉ ዜጎች፤ በየአመቱ በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ ነው ከሚባለው ኢኮኖሚ ጋር ተራርቀው ስለማይገናኙ።
በእርግጥ ፕሬዚዳንቱ፤ የኢኮኖሚ እድገትን በማድነቅና የመንግስትን ፖሊሲ ትክክለኛነት በመመስከር ንግግራቸውን ሲያሰሙ፤ የዋጋ ንረትንም መጥቀሳቸው አልቀረም። ነገር ግን፤ ለኢኮኖሚው እድገት፤ መንግስትን በማመስገን ሲናገሩ፤ ለዋጋ ንረቱ ግን መንግስትን ተጠያቂ በማድረግ አልወቀሱም። ለዘብ ያለ ተግሳፅ እንኳ አልሰነዘሩም። ከወዳጆች የሚመጣ ለዘብ ያለ ተግሳፅ ይጠቅም እንደሆነ እንጂ አይጎዳ! በጣም የሚያሳዝነው፤ የፕሬዚዳንቱ ንግግር ላለፉት አመታት ከመንግስት ስንሰማው ከነበረው ዲስኩር ብዙም የተለየ አይደለም።
የአለም የኢኮኖሚ ቀውስ አለመሻሻሉን የጠቀሱት ፕ/ት ግርማ፤ በአረብ አገራት ከተፈጠረው አመፅ ጋር ተዳምሮ፤ ነዳጅና ማዳበሪያ በመሳሰሉ ሸቀጦች ላይ የዋጋ ንረት ተከስቶ እንደነበር ተናግረዋል። ይህንንም ተከትሎ፤ አምና፤ በአገራችንም የሸቀጦች ዋጋ ከፍ ያለበት አመት ነበር ብለዋል - ፕሬዚዳንቱ።
እንግዲህ ተመልከቱ። ፕሬዚዳንቱ ስለ ዋጋ ንረት ሲናገሩ፤ ከሁሉም በፊት በቅድሚያ የጠቀሱት ምንን ነው? “የአለም የኢኮኖሚ ቀውስና የነዳጅ ዋጋ መናር”... ለአገራችን የዋጋ ንረት እንደ ቀዳሚ መንስኤ ሆነው ሲጠቀሱ የሰማነው፣ አሁን ብቻ አይደለም። ባለፉት አመታት ተመሳሳይ ንግግር ሰምተናል።
ግን አስቡት። ራሱ መንግስት፤ የነዳጅ የችርቻሮ ዋጋ ላይ ጭማሪ ባደረገ ቁጥር፤ በሌሎች ሸቀጦች ላይ ብዙም የዋጋ ለውጥ አያመጣም እያለ በተደጋጋሚ እያቃለለ ይነግረናል። ዞር ብሎ ደግሞ፤ የሸቀጦች የዋጋ ንረት የተፈጠረው፤ ከነዳጅ ዋጋ ጋር ተያይዞ እንደሆነ ሊያሳምነን ይሞክራል።
ደግሞስ፤ በአለም ደረጃ የነዳጅና የማዳበሪያ ዋጋ ሲጨምር፤ ከፍተኛ የዋጋ ንረት የሚከሰተው በኢትዮጵያ ብቻ ነው? ባለፉት አራት አመታትኮ፤ ኢትዮጵያ በዋጋ ንረት ከአለም አገራት ሁሉ በቀዳሚነት የምትጠቀስ ሆናለች። ኢኮኖሚያቸው ተቃውሷል በሚባሉት የአውሮፓ አገራትማ፤ “አመታዊ የዋጋ ንረት 3 በመቶ ደርሷል፤ ወይም ወደ 5 በመቶ ተጠግቷል” እየተባለ እንደ ጉድ ይወራል - እንደ ከፍተኛ ንረት። በብዙዎቹ የአፍሪካ አገራትም፤ የዋጋ ንረቱ ከ10 በመቶ አይበልጥም። በኢትዮጵያ ግን፤ ይሄው ከ40 በመቶ በላይ ነው። የአለም የኢኮኖሚ ቀውስና የነዳጅ ዋጋ፤ በተፈጥሮው ኢትዮጵያን ለይቶ የሚያጠቃ ሆኖ ነው? አይደለም።
ፕ/ት ግርማ፤ በሁለተኛ ደረጃ ለዋጋ ንረቱ መንስኤ ሆኗል ብለው የጠቀሱት ምክንያትስ አሳማኝ ነው? የአገሪቱ የንግድ ስርአት፤ ቅልጥፍና የጎደለው እንደሆነ ፕሬዚዳንቱ ጠቅሰው፤ ለኢፍትሃዊ አሰራር የተጋለጠ ነው በማለት ለዋጋ ንረት መንስኤ እንደሆነ ተናግረዋል። እንደተለመደው፤ ለዋጋ ንረቱ ነጋዴዎችን ተጠያቂ የሚያደርግ ሰበብ ነው። ፕሬዚዳንቱ፤ “አጭበርባሪ ነጋዴዎች፤ በዝባዥ ነጋዴዎች” ወደሚል ያፈጠጠ ስድብ አለመውረዳቸው መልካም ቢሆንም፤ “አልሸሹም፤ ዞር አሉ” ነው ነገሩ። ኢፍትሃዊ አሰራር ማለት በገዢው ፓርቲ ቋንቋ፤ በጥቅሉ “ሃብታም መሆን፤ አጭበርብሮ ማትረፍ፤ አላግባብ መክበር” ማለት ነዋ።
በእርግጥ፤ ነጋዴዎች ላይ የሚሰነዘረው ውንጀላና ውግዘት፤ ከገዢው ፓርቲ ወይም ከመንግስት በኩል ብቻ የሚመጣ አይደለም። ቢዝነስን የሚያንቋሽሽ ኋላቀር ባህል፤ ቢዝነስን የሚጠላ የሶሻሊዝም አባዜ፤ እንዲሁም ስለንግድና ስለቢዝነስ ትክክለኛ ግንዛቤ የሌለው አላዋቂነት፤ በአገራችን ሞልቶ ተትረፍርፏል። የእነዚሁ ድምር ውጤት፤ በደርግ ዘመን ታይቷል - የዋጋ ተመን፣ናየሸቀጦች እጥረት፣ የሸማቾች ማህበርና የቀበሌ ሱቅ፤ የዘይት ራሽንና የዳቦ ወረፋ። አምና ከታህሳስ ወር መጨረሻ ጀምሮ ለአምስት ወራት ገበያውን ያተራመሰ የዋጋ ቁጥጥርና መዘዞቹንም ተመልክተናል።
ይሄው ዛሬም፤ የዋጋ ቁጥጥር በሚደረግባቸው የስንዴ እህል፣ የስንዴ ዱቄትና የዳቦ ምርቶች ሳቢያ፤ ምን ያህል እጥረትና ግርግር እየተፈጠረ እንደሆነ ታውቁታላችሁ። ለነገሩ፤ የዋጋ ቁጥጥሩ ውጤት እንዳላመጣ ፕ/ት ግርማም የሚክዱት አይደለም - ፍሬ አላስገኘም ብለዋልና። ነገር ግን የዋጋ ቁጥጥሩን አልነቀፉም - አደነቁት እንጂ። በመሰረታዊ ሸቀጦች ላይ ሚዛናዊ የዋጋ ተመን ለማውጣት በጎ ጥረት ቢደረግም ፍሬ አላስገኘም ብለዋል - ፕ/ት ግርማ። መሰረታዊ ሸቀጦች ተብለው ተመን ሲወጣላቸው ከነበሩት መካከል፤ የለስላሳና የቢራ መጠጦችም እንደተካተቱ ታስታውሳላችሁ። የዋጋ ቁጥጥሩ ካልጠቀመ፤ ከዚያስ?
የዋጋ ቁጥጥሩ፤ ፍሬ ባለማስገኘቱ፤ በዚህም ምክንያት አንዳንድ መሰረታዊ ሸቀጦች ራሱ መንግስት ለማቅረብና አዲስ የጅምላ ንግድ ስርአት ለመፍጠር ተንቀሳቅሷል በማለት ፕሬዚዳንቱ አወድሰዋል። ለምሳሌ ምን? ስንዴ? ዘይት?... እዚህም ላይ፤ መንግስት ነጋዴ ልሁን ሲል፤ ውሎ አድሮ ገበያውን መረበሹ እንደማይቀር እያየን ነው - የዳቦ ወረፋው ይመስክር። በተቃራኒው አትክልትና ፍራፍሬ፤ የዋጋ ቁጥጥር ሲደረግበት ከነበረበት ወቅት ይልቅ፤ ዛሬ ነጋዴዎች በውድድር መስራታቸውን ሲቀጥረሉ ዋጋው የተሻለ ሆኖ እንደሚገኝ የስታትስቲክስ ኤጀንሲ የመስከረም ወር ሪፖርት ያሳያል።
ዘይትስ? መንግስት ብቸኛው የዘይት አስመጪና አከፋፋይ ለመሆን ከወሰነ ወዲህ ምን ውጤት ተገኘ? የዘይት ዋጋ ቀንሷል? ሊቀንስ ቀርቶ አልተረጋጋም። ሰሞኑን በስታትስቲክስ ኤጀንሲ የቀረበው ወርሃዊ ሪፖርት እንደሚያሳየው፤ የዘይትና ቅባት ዋጋ ከአምናው ጋር ሲነፃፀር፤ በ70 በመቶ ንሯል። ምን ማለት ነው? አምና በመቶ ብር ስንገዛው የነበረ ዘይትና ቅባት፤ ዛሬ 170 ብር ይፈጅብናል። ታዲያ ይህን ሁሉ ካየን በኋላ፤ አሁንም ነጋዴዎችን (የንግድ ስርአቱን) ለዋጋ ንረት እንደሰበብ ማቅረብ ይቻላል?
ፕ/ት ግርማ፤ በሶስተኛ ደረጃ ለዋጋ ንረቱ የጠቀሱት መንስኤ፤ ከሚገባው በላይ የገንዘብ አቅርቦት በዝቷል የሚል ነው - መንግስት ወጪዎቹን ለመሸፈን ከብሄራዊ ባንክ ቀጥተኛ ብድር መውሰዱ። ይህን የተድበሰበ አባባል፤ ወደ ግልፅ ቋንቋ እንለውጠው። መንግስት በብሄራዊ ባንክ በኩል በገፍ የብር ኖት እያተመ መጠቀሙ፤ የዋጋ ንረትን አስከትሏል እንደማለት ነው። በእርግጥም፤ ዋነኛውና መሰረታዊው የዋጋ ንረት ምንጭ፤ ከልክ ያለፈ የብር ኖት ህትመት ነው - የብር መርከስ።
የብር ህትመትና የብር መርከስ በቀዳሚነት ሊጠቀስ የሚገባው ዋነኛ የዋጋ ንረት መንስኤ ቢሆንም፤ ፕ/ር ግርማ የመጨረሻ ደረጃ ሰጥተውታል - የመጀመሪያ ስህተታቸው። መንግስት፤ ከልክ ባለፈ የብር ህትመት አማካኝነት የዋጋ ንረትን መፍጠሩ ከፍተኛ ጥፋት እንደሆነ በመጥቀስ፤ ከእንግዲህ ከዚህ ጥፋት እንዲቆጠብ ፕሬዚዳንቱ የወዳጅ ተግሳፅ አለመሰንዘራቸው ደግሞ ሁለተኛውና ትልቁ ስህተታቸው ነው።ነጋዴዎች ናቸው? ወይስ የመንግስት የብር ህትመት?ነጋዴዎች ናቸው? ወይስ የመንግስት የብር ህትመት?

የብር ህትመትና የብር መርከስ በቀዳሚነት ሊጠቀስ የሚገባው ዋነኛ የዋጋ ንረት መንስኤ ቢሆንም፤ ፕ/ር ግርማ የመጨረሻ ደረጃ ሰጥተውታል - የመጀመሪያ ስህተታቸው። መንግስት፤ ከልክ ባለፈ የብር ህትመት አማካኝነት የዋጋ ንረትን መፍጠሩ ከፍተኛ ጥፋት እንደሆነ በመጥቀስ፤ ከእንግዲህ ከዚህ ጥፋት እንዲቆጠብ ፕሬዚዳንቱ የወዳጅ ተግሳፅ አለመሰንዘራቸው ደግሞ ሁለተኛውና ትልቁ ስህተታቸው ነው።

የብር ህትመትና የብር መርከስ በቀዳሚነት ሊጠቀስ የሚገባው ዋነኛ የዋጋ ንረት መንስኤ ቢሆንም፤ ፕ/ር ግርማ የመጨረሻ ደረጃ ሰጥተውታል - የመጀመሪያ ስህተታቸው። መንግስት፤ ከልክ ባለፈ የብር ህትመት አማካኝነት የዋጋ ንረትን መፍጠሩ ከፍተኛ ጥፋት እንደሆነ በመጥቀስ፤ ከእንግዲህ ከዚህ ጥፋት እንዲቆጠብ ፕሬዚዳንቱ የወዳጅ ተግሳፅ አለመሰንዘራቸው ደግሞ ሁለተኛውና ትልቁ ስህተታቸው ነው።ነጋዴዎች ናቸው? ወይስ የመንግስት የብር ህትመት?

Read 1850 times Last modified on Saturday, 15 October 2011 11:25

Latest from