Saturday, 20 August 2011 10:26

በዕውቀቱ እና ዕውቀቱ

Written by  ጌታሁን ሄራሞ (ኬሚካል መሐንዲስ)
Rate this item
(0 votes)

የምዕመናን ማህበራት በስሜት የነደደ ቁጣ መግለጫ ሲሰጡ መሰማቱ፤ የሲኖዶሱ ውሳኔ ከፓርላማው ውሳኔ የበለጠ ትኩረት መሳቡ ወዘተ፡፡ ሆኖም ግን የዝርዝር ማስረጃዎቹ ቀስት በቀጥታ የሚያመለክተቱት አትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙት የሃይማኖት ተቋማት ውስጥ አንዱ ወደ ሆነው ወደ ኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተቋም ብቻ ነው፡፡
በግጥሞቹና በአጫጭር መጣጥፎቹ ውስጥ መሳጭ መልዕክቶቹን ባጤንኩ ቁጥር የሞባይል ስልኬን አንስቼ አድናቆቴን ከምገልጽላቸው ገጣሚዎች ውስጥ አንዱ ነው፤ በዕውቀቱ ስዩም፡፡ በሰው ልጅ ተፈጥሮ ውስጥ ትኩረቴን ከሚስቡ እውነቶች ውስጥ አንዱም እያንዳንዳችን የተለያየ ክህሎት እንዲኖረን ተደርገን መፈጠራችን ነው፡፡ ሁሉም ክህሎቶች አንድ ጋ አልከተሙም፤አድራሻቸው እዚህና እዚያ ነው፡፡ ይህ ክስተት ደግሞ እርስ በእርስ እንድንደናነቅ መንስኤ ሆኗል..ጤናማና ሚዛናዊ አዕምሮ እስካለን ድረስ!

የ”cognitive science” ግኝትም የሚለው መግቢያው ላይ ካስቀመጥኩት የተለየ አይደለም፤የካሊፎርኒያው ዩኒቨርሲቲ የሥነ ዕይታ ዕውቀት (Visual intelligence) እና የፍልስፍና ፕሮፌሰር ዶናልድ ዲ. ሆፍማን በ1998 ዓ.ም (እ.ኤ.አ) ባሳተሙት (Visual intelligence) ድንቅ መጽሐፋቸው ውስጥ እንደዚህ ይላሉ፤ ”The only difference between genius and stupidity is that the genius is limited…This is precisely the finding of cognitive science. You are a genius at a few things like vision and language, whether or not you have a high IQ.”
ስለዚህም ማንኛውንም ሐሳብ በጽሑፍም ሆነ በሌላ መልክ ከማስተላለፋችን በፊት ውስንነታችንን ተረድተን አቅማችንን መፈተሽ አዋቂነት ነው፡፡ We are genius at a few things!! የራሳችንን ውስንነት ባለማወቅ ገደቡን ጥሰን ገደል እንድንገባ ከሚያደርጉን ምክንያቶች አንዱም ዝናችንን ተከትሎ የሚመጣውን የሌሎችን አድናቆት በተሳሳተ መንገድ ማስተናገድ ነው፡፡ እኔ እምነቴን የጣልኩበትና የምመራበት መጽሐፍ ቅዱስ ይህን በተመለከተ የሚለው እንደዚህ ነው፡፡ ብር በከውር ወርቅም በማቅለጫ ይፈተናል ፤ሰውም በሚያመሰግኑት ሰዎች አፍ ይፈተናል፡፡ (ምሳሌ 27፡1)፡፡ የሰዎች አድናቆት እና ሙገሳ ውስንነታችን አዘናግቶ ራሳችንን የሁሉም  ዕውቀቶች ማዕከል አድርገን እንድንቆጥር የማድረግ አቅም አለው፡፡ እናም እኔም ሰሞኑን በዕውቀቱ ጋ የሞባይል የጽሁፍ መልዕክቴን የላክሁት እንደወትሮው ላደንቀው አልነበረም፡፡ በሐምሌ 30, 2003 ዓ.ም የአዲስ አድማስ ዕትም ላይ ..ፈሪሃ እግዚአብሄር ወይስ ዲሞክራሲ.. በሚለው ርዕስ ሥር የሰፈረው ሐሳብ በአብዛኛው  ገደብ የጣሰ መስሎ ስለታየኝ የበኩሌን ምላሽ እንደምሰጥ ላሳውቀው እንጂ! እርሱም ምላሼን በጨዋነት ለማስተናገድ ዝግጁነቱን ገልጾልኛልና ሳላመሳግነው አላልፍም፡፡  
ሆኖም አንባቢያን አንድ ነገር ልብ እንዲልሉኝ እፈልጋለሁ፡፡ የኔ ጉዳይ ከበዕውቀቱ ጋር ሳይሆን ከዕውቀቱ ጋር ነው፤ በተለይም የእምነትን ጉዳይ በተመለከተ የእኔን ዓይነት አቋም ለምን አልተከተለም የሚል ሙግትም የለኝም፡፡ የፈለገውን ማሰብና መናገር መብቱ ነው፡፡ የእኔ ሙግት ለሚያስበው ሃሳብም ሆነ ለሚያራምደው አመለካከት ሚዛን የሚደፋ ማስረጃ ማቅረብ አለበት የሚል ነው፡፡
የሐምሌ 30ውን የወዳጄን የበዕውቀቱን ጽሑፍ በማነብበት ወቅት በውስጤ የተፈጠረው የተዘበራረቀ ስሜት ነበር፡፡ ጽሁፉ የእርሱ ይሁን አይሁን ለማጣራት ደጋግሜ የፀሐፊውን ስም ተመልክቼአለሁ፡፡ ይህን ማለቴም ያለምክንያት አይደለም፡፡ በእኔ ዕይታ በጽሁፉ ውስጥ የተንፀባረቁትን ህፀፆች በሙሉ ነቅሶ ማውጣት (ከብዛታቸው አንፃር) እጅግ አድካሚና አሰልቺ ሆኖብኝ ነበር፡፡ በተለይም እንደእኔ በሽርፍራፊ ጊዜው ለሚጽፍ ሰው ሁሉንም እንከኖች ዘርዝሮ ማውጣት የሚታሰብ ባለመሆኑ ዋና ዋናዎቹን ሕፀፆች ብቻ እንደሚከተለው አቀርባለሁ፡፡
ደካማ አመክንዮ (weak reasoning)
በሐምሌ 30 ጽሁፉ በዕውቀቱ የተከተለው ሀሳብን የመግለጽ ስልት በአብዛኛው ከማጠቃለያ ተነስቶ ወደ ዝርዝር ማስረጃዎች የሚገባ ነው፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ የተስተዋለው ትልቁ ችግር ማስረጃዎቹ ማጠቃለያውን የማጠናከር አቅማቸው በጣም አናሳ ሆነው መገኘታቸው ነበር፡፡ ለምሳሌ ገና በጽሁፉ መጀመሪያ ላይ ..ሰሞኑን ሃይማኖት ፖለቲካን የተካ ይመስላል.. የሚል መደምደሚያ ተቀምጧል፡፡ ሃይማኖት ፖለቲካን ለመተካት መቃረቡን የሚያመለክቱ የበዕውቀቱ ማስረጃዎቹ ደግሞ እነዚህ ናቸው፡፡ በኑፋቄ የተጠረጠሩ ዲያቆናት ጉዳይ ሰፊ የህትመት ሚዲያ ሽፋን ማግኘታቸው፤ የምዕመናን ማህበራት በስሜት የነደደ ቁጣ መግለጫ ሲሰጡ መሰማቱ፤ የሲኖዶሱ ውሳኔ ከፓርላማው ውሳኔ የበለጠ ትኩረት መሳቡ ወዘተ፡፡ ሆኖም ግን የዝርዝር ማስረጃዎቹ ቀስት በቀጥታ የሚያመለክተቱት አትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙት የሃይማኖት ተቋማት ውስጥ አንዱ ወደ ሆነው ወደ ኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተቋም ብቻ ነው፡፡ በእኔ አተያይ በአንድ የእምነት ተቋም ውስጥ የሚከሰቱ ሰሞነኛ ሁኔታዎች በቀዳሚነት ትኩረት የሚያገኙት ከዚያው ከእምነቱ ተከታዮች እንጂ ከሁሉም ኢትየጵያዊ አይደለም፡፡ በእኔ እምነት በዕውቀቱ ሳይቸግረው ላስቀመጠው ግነት ለነገሰበት ማጠቃለያው፤ ከፍተኛ በሆነ የመረጃ እጥረት ቀውስ የተዘፈቀ ይመስላል፡፡
ወዳጄ አስቀድሞ ለደረሰበት መደምደሚያው በቂ ማስረጃ ማቅረብ ካልቻለ ወደ ማጠቃለያው የደረሰበት ሌላ ድብቅ አጀንዳ ይኖረዋል ብዬ እገምታለሁ፡፡ ለታሰሩ ጋዜጠኞቻችንም ሆነ የሚላስ የሚቀመስ ላጡ ወገኖቻችን ሁላችንም ከበዕውቀቱም ሆነ  ከአመለካከት ጓዶቹ ባልተናነሳ ሁኔታ እንቆረቆራለን፡፡ መቆርቆራችን ደግሞ ወደ ተግባር እንዲቀየር የሁሉም አትዮጵያዊ ምኞትና ፍላጎት ነው ብዬም አስባለሁ፡፡ እኔ ግን የእነ በዕውቀቱና የሐምሌ 23ቱ የ ..የሳይንስና የእምነት ክርክሩ ከሕይወታችን ጋር ይገናኛልን.. (ርዕስ ፀሐፊን ድብቁ አላማኝ (closet atheist)) መቆርቆር የማየው በጥርጣሬ ዓይን ነው፡፡ ነገሩ ሁሉ ጅብን ሲወጉ በአህያ ጥግ ሆኖ አባባል ዓይነት እየሆነብኝ ግራ ተጋብቼአለሁ፡፡ በገሃድ እንደሚታወቀው ቀደም ሲል በነበረው የደርግ ሥርዓት እምነት ነክ ጉዳዮች በማንኛውም ሚዲያ ሽፋን አያገኙም ነበር (ዶ/ር ፈቃዱም በነሐሴ 7ቱ ዕትም ይህን ጠቅሰውታል)፡፡ አሁን ደግሞ በዓለም አቀፍ ደረጃ በተለይም የኮሚኒዝም ፍልስፍና መንኮታኮትን ተከትሎ መንፈሳዊም ሆነ እምነት ነክ ጉዳዮች ትኩረት እያገኙ ነው፡፡ (የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲW የታሪክ ፕሮፌሰር የጻፉት “The Twilight of Atehism” መጽሐፍ ይዘት የሚያጠነጥነው በዚሁ ዙሪያ ነው፡፡) በሀገራችንም ቢሆን በ1994 ዓ.ም (እ.ኤ.አ) ከመቶኛ ሲሰላ ከ1% በታች የነበረው የአላማኞች ቁጥር በ2007 ዓ.ም(እ.ኤ.አ)  ከ0.4% በታች ወርዶአል፡፡
ይህ ሁኔታ ደግሞ የኛዎቹን ጨምሮ በእግዚአብሄር መኖር የማያምኑትን ቢያስቆጣቸው ያን ያህል አይደንቅም፡፡ እኔ በበኩሌ ደርግ ባዶ ካዝና አስረክቦን ነው የሄደው በሚለው ሀሳብ አልስማማም፤ ካዝናው ውስጥ የክህደትን ፍልስፍናንም አስቀምጦ ነው የሄደው! ዛሬም በድብቅም ይሁን በግልጽ ከመንግስት ባለስልጣናት እስከ ተራው ህዝብ ሃይማኖትን አጥብቀው የሚጠሉ (God Haters) ኃይለኛ አላማኞች (Militant atheists) አሉ፡፡ ደግነቱ ቁጥራቸው አነስተኛ ሆነ እንጂ! እነዚህ ትሩፋን እምነት ነክ ጉዳዮች ትኩረት አግኝተው በየሚዲያ ሲዘገቡና የእግዚአብሄርም ስም ከወትሮው በተለየ መልኩ በሬዲዮና ቴሌቪዥን ሲነሳ በሰሙ ቀጥር ካላቸው ፀረ-እምነት አቋማቸው አንጻር የደርግን ዘመን የሚናፍቁ ናቸው፡፡
የሌሎቹን የፕሬስ ሚዲያዎች የእምነት ነክ ዘገባ ለጊዜው እንተውና ስለአዲስ አድማሱ እንነጋገር፡፡ ለመሆኑ በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ የአማኝ-አላማኝ ክርክር የመጀመሪያውን ጥይት የተኮሰው ማን ነበር? የእምነት አቋማቸው ምን እንደሆነ ገና በውል ያልለየላቸው፤ አንዳንዴ የኖስቲክ ሃይማኖት ተከታይ ነኝ፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ አላማኝ ነኝ ሲሉን የነበሩ የጋዜጣው አምደኛ አቶ ሌሊሳ ግርማ አልነበሩምን (በሐምሌ 24 2002 ..የእግዜር ሮቦት.. በሚለው ጽሁፋቸው፡፡)  ስለዚህም ወዳጄ በዕውቀቱም ሆነ ስሙን የሰወረው የሐምሌ 23ቱ ፀሐፊ አንድ እውነት የዘነጋችሁ ይመስለኛል፡፡ እምነት ነክ ክርክሮች ትኩረት ለማግኘታቸው ምክንያት የሆነችው የመጀመሪያዋ ጥይት የተተኮሰችው ከዚያው ከእናንተ ካምፕ ከጎረቤታችሁ ነበር፡፡ ለተተኮሰብን ..ጥይት.. አፀፌታውን ስንመልስ ..ፖለቲካውን ተቆጣጠሩብን ትኩረታችን ወደ እምነት ጉዳይ አዘነበለ..ወዘተ..  ዓይነት ጩኸት ምነው በረከተ (ዛሬ የክርክሩ ዙር እየተካረረ ሲመጣ ምነው የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግና ርዕሰ ጉዳዩ ወደ ሌላ አቅጣጫ እንዲሆን አጥብቃችሁ ፈለጋችሁ? በዚሁ አጋጣሚ ምንም እንኳን ውሳኔኣቸው  በዕውቀቱንና መሰሎቹን የሚያስቆጭ ሆኖ ቢገኝም ሁሉንም አመላካከቶች ሚዛናዊ በሆነ መልኩ በማስተናገድ ሙያዊ ግዴታቸውን የተወጡትን የአዲስ አድማስ ጋዜጣ  አዘጋጆችን ሳላደንቃቸው አላልፍም፡፡
የበዕውቀቱ ደካማ አመክንዮ ቀውስ በዚህ ብቻ የሚያበቃ አይደለም፡፡ ለምሳሌ በጽሁፉ ላይ ..መራራውን ሀቅ ለመጋፈጥ የሚፈልግ ሰው ካለ ዳቦና ዲሞክራሲ ከእምነት ኃይሎች እንደማይፈልቁ ማወቅ አለበት..  ይለናል፡፡ መራራውን ሀቅ ያስደገፈው ግን በጠንካራ ሳይሆን በተራ አመክንዮ ላይ ነው፡፡ ..ያገራችን ገበሬ የሞፈር አቆራረጥንና የበሬ አጠማመድን ከቅዱሳት መጽሐፍት አልተማረውም.. በማለት!፡፡
እኔ የማምነው መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው የሞፈር አቆራረጥንና የበሬ አጠማመድን ሳይሆን ከዚያም ውስብስብ የሆኑ ሥራዎችን ማከናወን የሚችል ጥበብና አዕምሮ ከፈጣሪ እንደተለገሰኝ ነው፡፡ የሚገርመው በዕውቀቱ እራሱም ቢሆን ይህን አመለካከቱን የሚቃወም ሀሳብ በጽሁፉ ውስጥ አስፍሯል፡፡ ..የሀገራችን ችግር አንዱ ምንጭ የእግዜር እጥረት ሳይሆን የሰውን ድርሻ ለእግዜር አሳልፎ መስጠት ነው.. በማለት፡፡ ታዲያ የበሬን አጠማመድንና የሞፈር አቆራረጥን ከእግዜር ለመማር መፈለግ የሰውን ድርሻ ለእግዜር እንደመተው xYö«RM
2. የተበከለ ናሙናን በአስረጅነት ማቅረብ /Spoiled sample illustration
ሰዎች የክህደትን ፍልስፍና (atheism) የሚያራምዱት በተለያዩ ምክንያቶች ነው፤ ለአንዳንዶች ምክንያታቸው ሳይንሳዊ/ፍልስፍናዊ ነው፡፡ ከሳይንሳዊ ምርምሮች ጋር ካላቸው ቀረቤታ የተነሳ ሁሉንም ነገር በዚያው መልክ መረዳት ይፈልጋሉና፡፡ ሌሎች ደግሞ በአንዳንድ ሃይማኖት ተቋማት ከሚስተዋለው ኢ-ሞራላዊ ድርጊቶች የተነሳ በምሬት የክህደትን ፍልስፍና ሊያራምዱ ይችላሉ፡፡ በፈረንሳይ አብዮት ማግስት ዝቅተኛውና መካከለኛ መደብ በእግዚአብሄር ህልውና ላይ ጥያቄ ያነሳው የፈረንሳይ ቤተክርስቲያን የገዥውን መደብ በመወገኗ ነበር፡፡ በሦስተኛው ምድብ ያሉት ደግሞ በሰው ላይ ከሚደርሰው ሰው ሰራሽም ሆነ የተፈጥሮ አደጋ በመነሳት በእግዚአብሄር ህልውና ላይ ጥያቄ የሚያነሱ ናቸው፡፡
በአራተኛው ምድብ ያሉት ደግሞ በተለያዩ ኢ-ሥነ ምግባራዊ ልምዶች በመተብተባቸው የሚገጥማቸውን የህሊና ወቀሳ ..እግዚአብሄር የለም.. በሚል መሸሸጊያ ለማምለጥ የሚሞክሩ ናቸው፡፡ በእኔ አተያይ የአብዛኞቹ የሀገራችን አላማኞች አመለካከት በሳይንሳዊ ምርምሮች የተቃኘ መስሎ አይታየኝም፡፡ በሳይንሳዊ መስፈርት ሲታዩ ገና ለአቅመ ክህደት ያልደረሱ ብሶት ወለድ አላማኞች ናቸው፡፡ ለዚህ አባባል አስረጅነት ብዙም ርቀን መሄድ አያስፈልገንም፡፡ የበእውቀቱ ጽሁፍ በቂ ማስረጃ ነው፡፡ በዕውቀቱ የጽሁፉ መግቢያ እንዲሆንለት የመረጠው ግጥም ሶስተኛ ምድብ አላማኝ መሆኑን ሲያመላክት የኢድ አሚን ምሳሌው ደግሞ ሁለተኛ ምድብ አላማኝ መሆኑን ያመለክታል፡፡ ችግሩ የናሙናው ጤነኛ መሆን አለመሆን ሳይሆን ዋናውን ተወካይ የመወከል አቅሙ ላይ ነው፡፡     በነገራችን ላይ ግራ የሚያጋባ ሁኔታ በሚፈጠርበት ወቅት በጥያቄ መሞላት  አዲስ ግኝት አይደለም፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉ ነቢያትም በሚያዩት ነገር ግራ በተጋቡ ቁጥር የተሰማቸውን በገሃድ ጠይቀዋል፡፡ ለዚህም ነቢዩን ዕንባቆምን በአስረጅነት ማቅረብ ይቻላል፡፡ ..አቤቱ እኔ ስጮህ የማትሰማው እስከ መቼ ነው (ስለግፍ ወደ አንተ እጮኻለሁ አታድንም ፡፡በደልንስ ስለምን አሳየከኝ(ጠማምነትንስ ስለምን ትመለከታለህ (ጥፋትና ግፍ በፊቴ ነው፤ ጠብና ክርክር ይነሳሉ፡፡ ስለዚህ ሕግ ላልቶኣል፤ ፍርድም ድል ነስቶ አይወጣም ኃጢአተኛ ጻድቅን ይከብባልና ስለዚህ ፍርድ ጠማማ ሆኖ ይወጣል፡፡.. (ትን. ዕንባቆም 1፡3-4)
3. ታሪካዊ ሕፀፆች (historical fallacy)
በዕውቀቱ እነ ኢድ አሚንን ጨምሮ ለዓላማው ይጠቅሙኛል ብሎ ያሰባቸውን የተበከሉ ናሙናዎችን የመምዘዙን ያህል ከታሪክ ውስጥም የሚነግረን እየቆነጠረ ነው፡፡ በተለይም ስለአሜሪካêEÃN ፖለቲካ ከእነርሱ ከባለቤቶቹ የተሻለ መረጃ እንዳለው አድርጎ ለማቅረብ ሲሞክርም ተስተዉሎአል፡፡ ለምሳሌ በዕውቀቱ መጽሐፍ ቅዱስ በአሜሪካ የመሪነት ሳይንስ (Leadership science) ውስጥ ምንም ተጽዕኖ እንዳላሳረፈ በሚገርም መልኩ በሙሉ እርግጠኛነት ነግሮናል፡፡
እነርሱ አሜሪካዊያኑ የሚሉት ደግሞ ሌላ ነው፡፡ ለምሳሌ የመጀመሪያው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የነበሩ ጆርጅ ዋሽንግተን “It is impossible to rightly govern the world without God and the Bible” ያለ እግዚአብሄርና መጽሐፍ ቅዱስ ዓለምን በትክክል ማስተዳደር አይቻልም ማለታቸው መሰለኝ! 40ኛው የአሜሪካ መሪ የነበሩት ሮናልድ ሬገን ደግሞ አሜሪካን በመቅረጹ ሂደት መጽሐፍ ቅዱስ የነበረውን ወሳኝ ሚና ሲገልጹ ያሉት እንደዚህ ነበር  “Of the many influences that have shaped the United States into a distinctive nation and people, none may be said to be more fundamental and enduring than the Bible.” ሌሎቹ መሪዎች በተመሳሳይ ጉዳይ ላይ የተናገሩትን ዶ/ር ፈቃዱ አየለ ባለፈው ሳምንት ዕትም በሰፊው ስላስቀመጡት እዚህ ላይ መድገም አስፈላጊ መስሎ አይታየኝም፡፡   እንግዲህ የአሜሪካ መሪዎችና ተወላጆች ስለ ሀገራቸው፤ ስለእግዚአብሄርና ስለመጽሐፍ ቅዱስ የሚሉትና ወዳጄ በዕውቀቱ የሚለው ለየቅል መሆኑን መመልከት ይቻላል፡፡ እርሱ ያለው እንደዚህ ነበር ፤ ..የአሜሪካ ታላቅነት የመነጨው እጅግ ምርጥ ከሚባለው የፖለቲካ ሥርዓቷ ነው ፈሪሐ እግዚአብሔር የካህንነት እንጂ የመሪነት መስፈርት አለመሆኑን.... በዕውቀቱ ስለአሜሪካ kአሜሪካዊያኑ መሪዎች የበለጠ የሚያውቅ አይመስልም (ከሁሉም በላይ በቶማስ ጀፈርሰን አዕምሮ ላይ ተጽዕኖ ያሳደረበት ዮሐንስ ሎክ እንጂ ዮሐንስ ወንጌላዊው አይደለም በማለት በከፍተኛ እርግጠኛነት ወደ ድምዳሜ የደረሰበት ድፍረት በጣም አስደምሞኛል፡፡
ውድ ወዳጄ ፡- “Uncertanity” ህግና የ“Chaos” ንድፈ ሐሳብ ከፍተኛ ተቀባይነትን ባገኘበት በዚህ ዘመን እንደዚህ ዓይነት ፍጹም እርግጠኛነትን ማስወገድ ብልሕነት ነው፡፡ ለመሆኑ የዮሐንስ ወንጌል በጀፈርሰን አዕምሮ ላይ ተጸዕኖ ላለመፍጠሩ ምን ያህል እርግጠኛ ነህ? (ጀፈርሰን ዮሃንስ ወንጌልን ጨምሮ ከአራቱም ወንጌላት የተመሰጠበትን ሥነምግባራዊ እሴቶችን ሰብስቦ መፅሐፍ እንደጻፈስ መረጃው የለህምን (ዮሐንስ ሎክ እራሱስ ቢሆን የክርስትናን እውነት በተመለከተ “Reasonableness of Christianity “ ስለመጻፉስ? (ይህን የዮሐንስ ሎክ መጽሐፍ ከድረ ገጽ (The online library of liberty) ላይ በነጻ ማግኘት ይቻላል፡፡ Amazon.com ላይ ደግሞ ዋጋው 10 ዶላር ብቻ ነው፡፡   ሌላው በዕውቀቱ ታሪካዊ እውነታን ወግድ ብሎ መደምደሚያ ላይ የደረሰው የቅዱሳት መጽሐፍት ተጽዕኖ ከዘመናቸው ያልዘለለ እንደሆነ አድርጎ ያስቀመጠው ነው፡፡ ውድ ወዳጄ፡- ርዕሰ ጉዳያችን ምን ሆነና ነው እንደዚህ የምትለው (ዘመን ተሻጋሪ ተጽዕኖ ባይኖረው ኖሮ ዛሬ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ አንስተን እናወራ ነበር? (ዘመናችንን የማያውቁ ሰዎች የጻፉት ይህ መጽሐፍ ዛሬም የህትመት ክብረ ወሰኑን መያዙ እንዴት ተዘነጋ)   
ሌላው ወዳጄ የሰራው ታሪካዊ ህፀጽ የአሜሪካ ሳይሆን የኢትዮጵያን ታሪክ በተመለከተ ነው፡፡ በዕውቀቱ በምድረ ኢትዮጵያ አዲስ ትውልድ እንደተነሳ ነግሮናል፡፡ ይህም ትውልድ ..እግዜር ያልተረጋገጠ መላምት ነው.. የሚል ነው፡፡ b:Wq½:- በደርግ ዘመን ዕድሜህ ስንት ነበር? (ያኔ እኮ አሁን ከሚባለው የበለጠ በእግዜር ላይ ብዙ ተብሎ ነበር! እንደአሁኑ በሃሳብ ብቻ ሳይሆን በኃይል የሰውን እምነት ለማጥፋት ምን ያልተደረገ ነበር (እግዜር መላምት ነው የሚል ትውልድ ከሄደ ቆየ እኮ! የአሜሪካኖቹ ታሪክ የእኛ ስላልሆነ ብንሳሳትም አይፈረድብንም፡፡ የራሳችንን ለዚያውም የቅርብ ጊዜ ታሪካችንን አለማወቅ ግን ምን ይባላል)  በመጨረሻም እኔም ለበዕውቀቱ ምክር ቢጤ አስተላልፌ መልዕክቴን ልቋጭ፡፡ በዕውቀቱ የራሳችንን አመለካከት ለሌሎች በምናስተላልፍበት ወቅት ከቁጣ የፀዳን እንድንሆን አባታዊ የሚመስል ምክሩን ለግሶልናል፡፡ እኔ ደግሞ አንዳንድ የአላማኞች ምሁራን ለጓዶቻቸው ከሚሰጡት ምክር አንድ ሁለቱን ለበዕውቀቱ ልተውለት፡፡
እነዚህ ልምድ ያካበቱ አላማኞች የመጀመሪያው ምክራቸው የጠላትህን መሣርያ በተመለከተ በቂ መረጃ ይኑርህ የሚል ነው ....know the weapon of your enemy… ለምሳሌ የበዕውቀቱ ክርክር ከክርስትና እምነት ተከታዮች ጋር ከሆነ ስለመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ከመጥቀስ በዘለለ መልኩ በቂ መረጃ ሊኖረው ይገባል ማለት ነው፡፡
እነዚህ አላማኞች የሚሰጡት ሁለተኛው ምክር በተግባቦት ሳይንስ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ይህም የሌሎችን እምነት በማፌዝና በመቀለድ ለማሳመን አትሞክር የሚል፡፡ Just be a friendly atheist…  ለምሳሌ መሲሁን ለሚጠብቅ አማኝ ሁኔታውንና እምነቱን አውቶቡስ ከመጠበቅ ጋር አገናኝቶ ለማስረዳት መሞከሩን ልምድ ያካበቱ አላማኞች አይፈቅዱም፡፡ እንዲህ ዓይነት አካሄድ በአብዛኛው የሚስተዋለው አማተር አላማኞች ዘንድ ነው፡፡ ደግሞም የሳይኮሎጂው ሳይንስም ቢሆን እኮ እንደዚህ ዓይነቱን አቀራረብ በፍጹም አይደግፍም፡፡

 

Read 2660 times Last modified on Saturday, 20 August 2011 10:29