Saturday, 22 April 2023 18:59

የከተማችን ግዙፍ ሆቴል ከሁለት ሳምንት በኋላ ስራ ይጀምራል

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

“ማንኛውም ሰው ንጹህ ውሃ በነጻ መውሰድ ይችላል” ይላል የሆቴሉ የውሃ ቧንቧ  ላይ ተለጥፎ ያየነው ማስታወቂያ ። ሆቴሉ በራሱ ወጪ አስቆፍሮ ያወጣውንና ለሆቴሉ አገልግሎት የሚጠቀምበትን የከርሠ ምድር ውሃ የአካባቢው ማህበረሰብ ለ 24 ሰዓት እንዲጠቀምበት ፈቅዷል ።በደቡብ አፍሪካ በስደት  የቆዩት ወ/ሮ ህይወት አየለ እና በባለቤታቸው አቶ ዳግማዊ መኮንን  የተገነባው ግዙፉ  ስቴይ ኢዚ ፕላስ ሆቴል ለእንጦጦ ቅርብ በሆነ አካባቢ ተገንብቷል ።
ስቴይ ኢዚ ፕላስ ሆቴል 103 የመኝታ  ክፍሎች፣ ከ15 እስከ 1,500 ሰዎችን  ማስተናገድ የሚችሉ  ስድስት የስብስባና፣ የሰርግ አዳራሾች እንዲሁም የኪነጥበብ  እና ሌሎች ዝግጅቶች የሚሆኑ ሰፋፊና ምቹ  አዳራሾች  አሉት።
ከእንጦጦ ፓርክና  ቦታኒክ ጋርደን  ለሚመጡ ጉብኚዎች እንዲሁም በእንጦጦ እና ሱልልታ  የሩጫ ልምምድ  ለሚያደርጉ አትሌቶች   በቅርብ የሚገኝ ደረጃውን የጠበቀ  ሆቴል እንደሆነ የተነገረለት ይኸው ሆቴል በግልና በቡድን ለሚመጡ የአገር ውስጥና የውጭ አገር አትሌቶች  ምቹና አስተማማኝ አገልግሎት ለመስጠት እንዲያስችል ሆኖ መዘጋጀቱም ተጠቁሟል ።
ሆቴሉ   በሰዓት ከ30,000 ሺ ዳቦ በላይ ማምረት የሚችል ዘመናዊ ማሽን ያሉት ሲሆን ለአካባቢው ማህበረሰብ ዳቦ በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ መዘጋጀቱም ተነግሯል ።   ከ 250  በላይ  ለሚሆኑ ዜጎችም  የስራ ዕድል መፍጠር ችሏል። ከመሀል ከተማ  ፒያሳ በመኪና  አስር ደቂቃ ብቻ የሚወስድ ሲሆን  ፀጥ ያለ እና ነፋሻማ  ስፍራ ላይ የሚገኝ ሆቴል  ነው።ሆቴሉ  በአጠቃላይ  የያዘው  ስፍራ  2,250 ሜትር ስኩዬር ሲሆን  በ1,700  ሰኩዬር  ላይ ሆቴሉ ተገንብቷል።
 የኤሌትሪክ መኪና ይዘው ለሚመጡ  ደንበኞቹ   ኤሌትሪክ ቻርጅ  ማድረጊያ  ቦታ ያለው ሲሆን  በቅርቡ በሚጠናቀቁት የማስፋፊያ ፕሮጀክቱ  ሰፖርት መስሪያ ጂም ፣የሴትና የወንድ ለየብቻ (በFloor)  ሳውና  እና ስቲም ባዝ  ፣ መዋኛ ገንዳ፣የዮጋ አዳራሽ በተጨማሪም  የባህል  ሬስቶራንትና   የሙዚቃ አዳራሽ  ይኖረዋል። በተጨማሪም እስቴ ኢዚ ፕላስ ሆቴል የከርሰ ምድር ውሃ ያለው ሲሆን በሰከንድ አምስት ሊትር ውሃ ማመንጨት የሚችል ሲሆን ለማህበረሰቡ ለ24 ሰዓት በነፃ እየሰጠ ማህበረሰባዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ የሚገኝ ሆቴል ነው፡፡
ስቴይ ኢዚ ፕላስ ሆቴል ከእዚህ በፊት 22 አካባቢ በነበረው ሆቴሉ አማካኝነት በበርካታ የበጎ አዶራጎት ስራውች ላይም በመሣተፍ ሀላፊነቱን ሲወጣ ቆይቷል።

Read 2116 times