Saturday, 01 April 2023 20:03

በአማራ ክልል ነባር ዳኞች በፈቃዳቸው ከሥራ እየለቀቁ ነው

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(0 votes)

በ6 ወራት ውስጥ ብቻ 103 ዳኞች ከሥራቸው ለቅቀዋል ፍርድ ቤቶች የአዳዲስ ዳኞች መለማመጃ ሆነዋል ተብሏል
                  

        በአማራ ክልል ለረዥም አመታት በዳኝነት ያገለገሉ ነባር ዳኞች፣ ስራቸውን እየለቀቁ መሆኑ ተነግሯል። የክልሉ ዳኞች ማኅበር ይፋ እንዳደረገው፤ ዳኞች ከተለያዩ ወገኖች በስራቸው ላይ በሚደርስባቸው ጫናዎች ሳቢያ ስራቸውን መስራት ባለመቻላቸው በፈቃዳቸው ከሥራቸው   6 ወራት ውስጥ ብቻ 103 ዳኞች ከሥራቸው በራሳቸው ፈቃድ መልቀቃቸውንም ማህበሩ ይፋ አድርጓል። ይህ ሁኔታም በዳኝነት ሙያ ከፍተኛ ልምድ ያላቸው ዳኞችን እያሳጣ መሆኑን ያመለከተው ማህበሩ፤ ፍርድ ቤቶች የአዳዲስ ዳኞች መለማመጃ መሆናቸውንም ጠቁሟል።ዳኞቹ በስራቸው ላይ ከተለያዩ አካላት የሚደርስባቸው ጫና ከአቅማቸው በላይ በመሆኑና የፍርድ ሂደቱን በአግባቡ ለማካሄድ በሚያስችል አሰራር ውስጥ ሆነው መስራት ባለመቻላቸው ስራቸውን ለመልቀቅ ተገደዋል ያለው ይኸው መረጃ፤ በአሁኑ ወቅት በክልሉ በስፋት የሚታየው የነባር ዳኞች ስራ መልቀቅ ሂደት በፍትህ ስርዓቱ ላይ ከፍተኛ ጫና እየፈጠረ እንደሆነ ገልጿል።
ይህ ሁኔታም በክልሉ ውስጥ በሚገኙ የመጀመሪያ ደረጃና ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ላይ ብቻ ተወስኖ የቀረ ጉዳይ አለመሆኑን ያመለከተው የማህበሩ መረጃ፤ በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውስጥ ከሚሰሩ ዳኞች መካከልም በውስጣዊና ውጫዊ ገፊት ምክንያቶች ሳቢያ ስራቸውን የለቀቁ አንዳንድ ዳኞችም እንደሚገኙ ተጠቁሟል፡፡በክልሉ ከዳኞች በተጨማሪ የዓቃቤ ህጎች ፍልሰት ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ  መጠን እየጨመረ ያመለከቱት መረጃዎች ዐቃቤ ህጎቹ ከስራቸው ጋር በተያያዘ ከሌላው አካል የሚደርስባቸው ጫና መቋቋም ሲያቅታቸው ስራቸውን ለመልቀቅ እንደሚገደዱ ተጠቅሷል፡፡
ይህ በክልሉ በሚገኙ ዳኞቹና ዐቃቤ ህጎቹ ላይ የሚታየው ከፍተኛ ፍልሰት ከፍተኛ ልምድ ያላቸው ባለሙያዎችን ማሣጣቱንና ፍርድ ቤቶች የአዳዲስ ዳኞችና ዐቃቤ ህጎች መለማመጃ እንዲሆኑ ማድረጉንና ይህም የፍርድ ሂደቱን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚጎዳው ተገልጿል፡፡ በአሁኑ ወቅት በክልሉ ለሚሠሩ ዳኞች ከቀድሞ የተሻለ ክፍያ አላቸው ቢባልም፣ ምቹ የስራ ሁኔታ ባለመኖሩ የዳኞችና የአቃቤያን ህግ ፍልሰቱ መበራከቱ ተጠቁሟል።


Read 1737 times