Wednesday, 01 March 2023 00:00

ጥቂት ስለማህፀን በር ካንሰር

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

*የማህፀን በር ካንሰር ማለት በማህፀን ጫፍ ላይ ያልተለመደ የህዋስ እድገት ሲከሰትና ይህም በመላው የማህፀን ጫፍ አካባቢ ሲዛመት ነው፡፡
የማህፀን በር ካንሰር የሚያስከትላቸው ጉዳቶች
* የደም መርጋት
* የደም መፍሰስ
* ፊስቱላ
*  የሆድ ድርቀት
*  የመሽናት ችግር
* መካንነት
*  የውስጣዊ አካል ከጥቅም ውጪ መሆን
እነዚህንና የመሳሰሉትን ጉዳቶች በማምጣት የማህፀን በር ካንሰር እስከ ሞት ሊያደርስ የሚችል ህመም ነው፡፡
ለማህፀን በር ካንሰር ተጋላጭ የሚሆኑት እነማን ናቸው?
ማንኛውም የግብረ ስጋ ግንኙነት ፈጽማ የምታውቅ ሴት ሁሉ ለማህፀን በር ካንሰር የመጋለጥ አጋጣሚ ሊኖራት ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ፡-

*  በለጋነት ዕድሜ (ከ20 ዓመት እድሜ በታች) የግብረ ስጋ ግንኙነት የጀመሩ ሴቶች፣
* ከተለያዩ ወንዶች ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት የሚፈጽሙ ሴቶች፣
* በተለያዩ ምክንያቶች የሰውነት በሽታ የመከላከል አቅም መዳከም ያጋጠማቸው ሴቶች (ለምሳሌ ኤች አይ ቪ በደማቸው ውስጥ ያለ)፣ እንዲሁም
*  በአባላዘር በሽታ የተያዙ ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው፡፡
የማህፀን በር ካንሰር ዋና ዋና ምልክቶች
የማህፀን በር ካንሰር ምንም አይነት የህመም ስሜትና ምልክት ሳያሳይ ከ15 እስከ 20 ዓመት ሊቆይ ይችላል፡፡ በሽታው ከተባባሰ በኋላ ግን፡-
*  ከወር አበባ ወቅት ውጭ የማህጸን ደም መፍሰስ፣
*  የወር አበባ ጊዜ የተራዘመና ከባድ መሆን፣
*  የመውለጃ ጊዜ ወይም ዕድሜ ካለፈ በኋላም የደም መፍሰስ ማጋጠም፣
*  ያልተለመደ ወይም ለየት ያለ ጠረን ያለው የብልት ፈሳሽ፣
*  ድካም፣ የወገብ ህመም፣ ክሳት፣ የሆድ ህመም እና የመሳሰሉት ምልክቶች ሊታዩ ይችላሉ፡፡

የማህፀን በር ካንሰርን እንዴት መከላከል ይቻላል?

በየአምስት ዓመቱ አንድ ጊዜ የቅድመ ካንሰር ምርመራ ማድረግ፣ በተጨማሪም
*  ከ20 ዓመት ዕድሜ በታች የሚገኙ ሴቶች የማህጸን በራቸው ያልዳበረ በመሆኑ በለጋነት ዕድሜ የግብረ ስጋ ግንኙነት ያለመፈጸም፣
*  ኤች ፒ ቪ ክትባትን መከተብ፣
*  አንድ ለአንድ መወሰን፣
የማህፀን በር ካንሰር ማለት በማህፀን ጫፍ ላይ ያልተለመደ የህዋስ እድገት ሲከሰትና ይህም በመላው የማህፀን ጫፍ አካባቢ ሲዛመት ነው፡፡

*  የአባላዘር በሽታን መከላከል ዋነኞቹ የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ዘዴዎች ናቸው፡፡
የማህፀን በር ቅድመ ካንሰር ምርመራን በጤና ተቋም በማድረግ፣ የማህፀን በር ካንሰር ተጋላጭነትዎን ይቀንሱ!

የአባላዘር በሽታን መከላከል ዋነኞቹ የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ዘዴዎች ናቸው፡፡
የማህፀን በር ቅድመ ካንሰር ምርመራን በጤና ተቋም በማድረግ፣ የማህፀን በር ካንሰር ተጋላጭነትዎን ይቀንሱ!

Read 3030 times